Ethio News

Ethio News ቶሎ ቶሎ መረጃ እንዲደርሶ ፔጁን Like ያድርጉ Telgram Adders

01/08/2012
09/04/2020

01/08/2012

08/04/2020



ትላንት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለWHO የምትሰጠውን ከፍተኛ ገንዘብ እንደምታቅብ ተናገረዋል። የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን በጊዜ አልተናገረም ብለዋል ፕሬዘዳንቱ።

ድርጅቱ ይህን ያደርገው በሽታው ለተጀመረባት #ቻይና ሲል ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምት አዘል አነጋገር ተናግረዋል። "በጣም ቻይና ተኮር ይመስላሉ ፣ ይህን ማጤን ይኖርብናል' ሲሉ ተደምጠዋል ዶናልድ ትራምፕ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ባለበት በዚህ አይነት ሁኔታ ለጤናው ድርጅት /WHO/ የሚዋጣ ገንዘብ መከልከ ተገቢ ነው ወይ? ተብለው ከጋዜጠኛ የተጠየቁት ትራምፕ 'እኔ አንሰጥም አላልኩም፣ እናጤነዋለን ነው ያለኩት' ሲሉ መልሰዋል።

ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዛሬ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው ላይ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ፤ እሳቸው ግን ግድ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል። በማን ይህ ሊደረግ እንደቻለ ግን አልተናገሩም።

ከሁለት (2) እና ከሦስት (3) ወር በላይ #ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ 'ጥቁር ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም' ሲሉም ተደምጠዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

08/04/2020
08/04/2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል የ5 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ረፋድ ባካሄደው ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ስጋት እየጨመረ በመምጣቱ ለ5 ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውቅል።

እንደ ፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ መረጃ ከሆነ ይህ አዋጅ የሚከለክላቸው፣የሚፈቅዳቸው እና ሌሎች ዝርዝር አፈጻጸሞች በቀጣይ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋሉ።...

08/04/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ ሶስት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ። ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል ነው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር ሁለት እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

 የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።
08/04/2020



የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።

08/04/2020

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሮና ቫይረስ የባሰ የዓለማችን አስጊ ሰው መሆናቸውን ኢራን አስታወቀች።

የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሮና በበለጠ አደገኛ ሰው ናቸው ብለዋል፡፡

ባለስልጣናቱ ይህን ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ ኢራን እንዳይገቡ በመከልከላቸው ነው ተብሏል፡፡

ባለስልጣናቱ እንደተናገሩትም ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ የሕክምና ግብአቶች ለማገድ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ በሰው ልጆች ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

የኢራን የፀጥታው ምክር ቤት ሀላፊ አድሚራል አሊ ሻምካኒ ኢራን የኮሮና ቫይረስ ለመግታት በአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እርዳታ እንዳታገኝ የአሜሪካ መንግስትን ሴራ ተቃውመዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለኢራናዊን ያላቸውን ግልጽ የሆነ ጠላትነት ያሳያል ነው ያሉት ሀላፊው፡፡
በኢራን እስካሁን ድረስ 3 ሺህ 600 ያህል ዜጎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በዓለማችን ደግሞ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በዚሁ ቫይረስ ሲጠቁ 82 ሺህ 500 ሰዎች ሲሞቱ ከ302 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል።

መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም

07/04/2020

ስምንቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግለሰቦች፦

• ታማሚ 1 - የ9 ወር ህፃን ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 2 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 3 - የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 4 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት።

• ታማሚ 5 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበረው።

• ታማሚ 6 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበራት።

• ታማሚ 7 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ ምንም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 8 - የ30 ዓመት ኤርትራዊት ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ለንደን የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላት።

06/04/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።

ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።

መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

06/04/2020

ታክሲዎች የመጫን አቅማቸውን በግማሽ እንዲቀንሱ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ ከመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑና ተሳፋሪዎችም እጥፍ እንዲከፍሉ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የአንበሳ አውቶብስና ሸገር አውቶብስ ደግሞ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ 30 ሰው ብቻ እንዲጭኑም ተወስኗል፡፡

ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን ከሰዓታት በኃላ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎች የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

05/04/2020



በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሞት ተመዘገበ!

በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን በዛሬው እለት ሁለተኛ ሰው ህይወት ማለፉን ስገልጽ በከፍተኛ ሀዘን ነው። ታማሚው በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ ናቸው። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

(የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ)

05/04/2020

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ ለፉት 6 ቀናት በጽኑ ህክምና ክትትል ላይ የነበሩት የ60 ዓመት አዛውንት ህይወታቸው ማለፉን የኡትዮፕያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል።

የጤና ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና በሽታ (ኮቪድ-19) በቻይና ውሃን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ወደ ሀገራችን ቫይረሱ እንዳይገባ እንዲሁም ከገባ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቅስቀሳዎችን እያደረገና የተጠቂዎችን ቁጥርና የጤና ሁኔታቸው እያሳወቀ ነው፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share