16/04/2026
አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ዘይት ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ ቻይና ዉድቅ አደረገች
ቻይና ሐሙስ ዕለት አሜሪካ በሁለት የቻይና ባንኮች ላይ ሁለተኛ ማዕቀብ ለመጣል የሰነዘረችውን ዛቻ በማውገዝ እነዚህን እርምጃዎች “ሕገወጥ” በማለት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፈቃድ የላቸውም ስትል አስታዉቃለች።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን በቤጂንግ መደበኛ የዜና መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ቻይና ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፈቃድ ውጭ ህገ-ወጥ የአንድ ወገን ማዕቀቦችን ትቃወማለች ሲሉ ተደምጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሁለት የቻይና ባንኮች ደብዳቤ ልካለች፣ “በሂሳባችሁ ውስጥ የኢራን ገንዘብ እንዳለ ካረጋገጥን ሁለተኛ ማዕቀብ ለመጣል እንገደዳለን” ብለዋል ።ቤሴንት በተጨማሪም ቻይና ከ90 በመቶ በላይ የኢራን ነዳጅ ዘይት ትገዛ እንደነበር በማንሳት ይህም ከቻይና የኃይል ፍላጎት 8 በመቶ ያህሉ ነዉ።
በተጨማሪም ዋሽንግተንን በሆርሙዝ የባህር ዳርቻ ላይ የአሜሪካ እገዳ በመጣል "የቻይንን ግዢ ማቋረጥ ይሆናል" የሚል እምነታቸዉን ገልጸዋል፡፡በሳምንቱ መጨረሻ በፓኪስታን በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረገ ያልተለመደ ቀጥተኛ ውይይት የካቲት 28 የጀመረውን ነገር ግን ስምምነት ላይ መድረስ ያልቻለውን ጦርነት ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ወደቦች ላይ የባህር ኃይል እገዳ ጥላለች።