
06/08/2025
በየመን የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ አሰቃቂ የጀልባ መስጠም አደጋ "ከ68 በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወት" ማለፉን ተከትሎ፣ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገለፀ፣
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳስታወቀው፣ 154 ኢትዮጵያውያንን የጫነች ጀልባ እሁድ ማለዳ ስትሰጥም፣ 68ቱ ህይወታቸው አልፏል፣ 74ቱ የውሃ ሲሳይ ሆነዋል፣ 12ቱ ብቻ ከሞት ተርፈዋል።
ይህ አሰቃቂ ክስተት፣ በሀገሪቱ አሁንም በርካታ ዜጎች በስደት በባህር ለስራ ፍለጋ ወደተለያዩ ሀገራት ዜጎች እንደሚሰደዱ የሚያሳይ ነው በመሆኑም መንግስት አሁንም ዜጎች በሀገራቸው የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መፍጠር እንዳለበት እናሳስባለን።
የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፣ ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።
መንግስት የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መፍትሄ እንዲያበጅ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ዜጎች በህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሳይታለሉ በህጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።
ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ!
✍✍ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ቴሌግራም ቻናላችን ☞☞☞
https://t.me/+_956ZXyo_ak4NTc8y
የአባልነት መመዝገቢያ ቅጽ (አማርኛ)
https://forms.gle/hxVzqzMDbuJmLBsC8