አምባዬ EOTC MEDIA

አምባዬ EOTC MEDIA የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን። የአምባዬ ቲዩብ የዩቱዩብ ቻናል SUBSCRIBE እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት

ቦታው ቤተ ክርስቲያን ነው ዝናብ እየዘነበ ነውወይ ሚስቱ ወይ እኅቱ ወይም ቅርብ ጓደኛው ነች ዝናብ ጸጉሯን እንዳያገኛት እርሱን ዝናብ እየመታው ወንበር እንደ ጃንጥላ ተሸክሞላት ቆሟልምናልባት...
09/06/2025

ቦታው ቤተ ክርስቲያን ነው
ዝናብ እየዘነበ ነው
ወይ ሚስቱ ወይ እኅቱ ወይም ቅርብ ጓደኛው ነች ዝናብ ጸጉሯን እንዳያገኛት እርሱን ዝናብ እየመታው ወንበር እንደ ጃንጥላ ተሸክሞላት ቆሟል
ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ቦታው ላይ ሆነን ስናይ አይ ወንድ ልጅ ሲያፈቅር ምናምን ብለን በተጣመመ መልኩ ልናየው እንችል ይሆናል ሴት ልጅን ሊጎዱ ከሚችሉ ነገሮች እንዴት ማዳን እንዳለብን እንዴትና በምን አይነት ዘዴ ልንከባከባትና ክብር ልንሰጣት እንደሚገባን የሚያሳይ ነው

እርገጠኛ ነኝ እንዴት ወንበር ተሸክሞ አያስጠልለኝም የሚል ሐሳብ አእምሮዋ ውስጥ አይመጣም ነበር ለምን ወንበር አልዘረጋልኝም የሚል ወቀሳም አትሰነዝርበትም ነበር ግን እርሷን ለማዳን ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሣ ይህ ሐሳብ ብልጭ አለለትና ለእርሷ ካለው ጥንቃቄ የተነሣ አጠገቡ ያለውን ነገር እርሷን ለማዳን ተጠቀመበት
እንዲያው እርሷን ሆነን ስናስበው ደግሞ ማንም ሊያስበው የማይችለውን ይሄንን ተግባር እርሷ ብቻ ተጠልላበት ስታይ ምን ያህል በቅን ሐሳቡ ትደመም ይሆን?
እኔ እራሱ በወንበር ስር መጠለል መኖሩን ያወኩት ገና ከዚህ ሰው ነው😍

ለሰዎች እንክብካቤ ማድረግ ያለብን ሰዎች በሚጠብቁትና በሚያስቡት ወይም በተለመደ ነገር ብቻ አይተንና ባናደርግላቸው ይታዘቡናል ብለን ሳይሆን ለእነርሱ ማድረግ በምንችለው አቅማችን ሁሉ መሆን አለበት
ለሰዎች የምናደርገው እንክብካቤ ቅን ሐሳባችንን የሚጠይቅ እንጂ የግድ ብዙ ወጭና ውድ ማቴሪያል በማዘጋጀት አይደለም

#ማርያም #መዝሙር #መስቀል

29/05/2025
 #እናመሰግናለን🙏 የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ  የጉባኤ ውሎ አስመልክቶ የብፁዓን አባቶች አስተምሮ በተመለከ...
28/05/2025

#እናመሰግናለን🙏

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ የጉባኤ ውሎ
አስመልክቶ የብፁዓን አባቶች አስተምሮ በተመለከተ ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የሊቃውንት ጉባኤ በሦስት ብፁዓን አባቶች ማለትም በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ ; በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሊቀ ጳጳስ በተላለፉ ትምህርቶች ላይ ያቀረበውን የስህተት ትምህርት የሚያሳይ አስተያየት እና የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል። ምልዓተ ጉባኤውም የሦስቱን አባቶች አስተያየት አዳምጦ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል ።
በሦስቱ ብፁዓን አባቶች ማለትም በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ ; በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ጳጳስ ጥፋታቸውን አምነው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ይቅርታ በመጠየቅ ;በሊቃውንት ጉባኤ የቀረበው እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሚያምኑ እና የሚያስተምሩ መሆኑን በመግለጽ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቀዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ይቅርታቸውን በመቀበል ያስተላለፉትን የስህተት ትምህርት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ( ) ቀርበው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል አስተምህሯቸውን አርመውና አስተካክለው እንዲያስተላልፉ መመሪያ ሰጥቷል።
ወደፊትም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና መምህራን የሃይማኖት ትምህርት ሳይሸራረፍ ለትውልድ ለማስተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና በአከራካሪ ጉዳዮች በግለሰብ ደረጃ ምላሽ እንዳይሰጥ ጉባዔው ወስኗል ።

ዘገባው የ 👉 📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥 ነው

ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታሰሩ ‼️በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስብከት አገልግሎቱ፣በተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ስልጠና በመስጠት፣በተለይም ተሃድሶውያንን በመዋጋት የምናውቀው ዲያቆን ...
18/05/2025

ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታሰሩ ‼️

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስብከት አገልግሎቱ፣በተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ስልጠና በመስጠት፣በተለይም ተሃድሶውያንን በመዋጋት የምናውቀው ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ተሰማ።

እንደሚታወቀው የቅዱስ ሶኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅላይቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሚመረጥበት ግዜ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ይታገላሉ የሚባሉ ወንድሞች እና እህቶች ይታሰራሉ፡፡ ዛሬም ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታስሯል።

የቅዱስ ሲኖዶስን ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅን መምረጥ የመንፈስ ቅዱስ እና የብፁዓን አባቶች ድርሻ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚታሰር አንዳችም ሰው መኖር የለበትም ።ወንድማችንን እንድትፈቱት እንጠይቃለን ።

🌺 ታህሳስ 3   #በዓታ ለማርያም 🌺☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️      እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት(ባዕታ ለማርያም) በሰላም አደረሰን አደረሳ...
12/12/2024

🌺 ታህሳስ 3 #በዓታ ለማርያም 🌺
☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️🌺🌹☘️
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት(ባዕታ ለማርያም) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
"ማርያም ሆይ የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል፡፡"
የጭንቄ ደራሽ ነሽ የፅድቄ መገኛ
አንገቱን ለደፋ ሆንሽለት መፅናኛ
በሰላም ወጥቼ በጤና መግባቴ
አንቺ ስላለሽ ነዉ ድንግል እመቤቴ።
እናቴ ባዕታ ለማርያም ያስጨነችሁን ነገር ሁሉ ለበጎ ታድርግላችሁ ።በስደት ያሉትን የስደት ፍፃሜያቸውን ታሳምርልን። እንደ ወጡ ከመቅረት ትሰውረን፣ በመንገዳችን ሁሉ ትከተለን።
ከሚወራው ከሚሰማው ክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን።

ለ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው ወርሃዊ መታሰቢያ ዕለት እንኳን አደረሳችሁ የተዋህዶ ልጆች 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃ዑራኤል ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው፡፡ቅዱስ ዑ...
29/06/2024

ለ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው ወርሃዊ መታሰቢያ ዕለት እንኳን አደረሳችሁ የተዋህዶ ልጆች
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
ዑራኤል ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ዑራኤል ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡
~~
እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

የቅዱስ ዑራኤል መልአክ ጥበቃው አይለየን ረድኤት እና በረከቱ ከሁላችንም ጋር ይሁን በምልጃው ዋስ ጠበቃ ይሁነን አሜን!

“ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ።” መዝ ፵፭፦፬    ሰኔ 21 ቀን ለመጀመርያ ጊዜ በእመቤታችን ስም በአራቱም ማዕዘን ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት እና በልጇ መቃብር በጎልጎታ (ሰኔ ጎልጎታ) የጸለ...
27/06/2024

“ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ።
” መዝ ፵፭፦፬

ሰኔ 21 ቀን ለመጀመርያ ጊዜ በእመቤታችን ስም በአራቱም ማዕዘን ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት እና በልጇ መቃብር በጎልጎታ (ሰኔ ጎልጎታ) የጸለየችበት ቃል ኪዳንም የተቀበለችበት ቀን ነው።

የብርሃን እናት፣ የፍቅር እናት፣ የሕይወት እናት፣ የአምላክ እናት… ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ በዕለተ ቀኗ ሁላችንን ትባርከን ።

መጋቢት ፯ ቀን.Highlight Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)FastMereja.com
15/03/2024

መጋቢት ፯ ቀን.

Highlight Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)FastMereja.com

--◈◈  ◈◈ የካቲት 17/2016  --  ◈◈--     --◈◈--ቅዱስ እስጢፋኖስ --◈◈--◈ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በሰማእቱ ስ...
25/02/2024

--◈◈ ◈◈ የካቲት 17/2016 -- ◈◈--
--◈◈--ቅዱስ እስጢፋኖስ --◈◈--

◈ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

◈ ጸሎቱና በረከቱ በህዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር እና ወር በገባ በ 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም #አክሊል ማለት ነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር

◈ ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል ከእነዚህ መካከል ቅዱስ #እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሆኖ ተሹሟል ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር

◈ ተዐምራትን የማድረግ ፀጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ

◈ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት #ምሕረትን ለመነ ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው በመጨረሻም ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ነፍሱን ሰጠ

◈ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር

◈ ተንበርክኮም ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ይህንም ብሎ አንቀላፋ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር ሐዋ ሥራ 7፥58—60

◈ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱስ #እስጢፋኖስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ምልጃው ፀሎቱ አይለየን ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን የተባረከ የተቀደሰ ይሁንልን "አሜን"

ቻናላችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በTelegram https://t.me/ambayepost

በYouTube https://www.youtube.com/

በFacebook https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
◈ አምባዬ EOTC MEDIA 👉

--  ◈◈  --የካቲት 13/2016 --  ◈◈  --  --  ◈◈  --  እግዚአብሔር አብ  --  ◈◈  ----  ◈◈  --  ቅዱስ ሩፋኤል  --  ◈◈  ----  ◈◈  --  አቡነ ዘርዐ...
20/02/2024

-- ◈◈ --የካቲት 13/2016 -- ◈◈ --
-- ◈◈ -- እግዚአብሔር አብ -- ◈◈ --
-- ◈◈ -- ቅዱስ ሩፋኤል -- ◈◈ --
-- ◈◈ -- አቡነ ዘርዐ ብሩክ -- ◈◈ --


◈ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
➥ አምላካችን እግዚአብሔር አብን ለምናመሰግንበት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃዉ እንዳይለየን ለምንማፀንበት ለፃድቁ*አቡነ ዘርዐ ብሩክ ወርሐዊ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን

➥ ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)

➥ ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው

➥ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል

➥ በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል

◈ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረት አይኑ ይመልከተን "አሜን"

የካቲት 07/2016አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ እንኳን አደረሳችሁ /አደረሰን።      🔷 ሚስጥረ ሥላሴ◈ ሚስጥረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ሚስጥር ማለት ነዉ። ይኸዉም አብ ወልድ ...
15/02/2024

የካቲት 07/2016
አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ
እንኳን አደረሳችሁ /አደረሰን።

🔷 ሚስጥረ ሥላሴ

◈ ሚስጥረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ሚስጥር ማለት ነዉ። ይኸዉም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባህሪ፣ በሕልዉና ፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸዉ። እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት ፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና ፤ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅና በሰዉ አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ሚስጥር ይባላል።

◈ የሰዉ ልጅ ሁሉን የመመርመርና ሁሉን የመረዳት መብትና ስልጣን ከአምላኩ የተሰጠዉ መሆኑ ቢታወቅም የፈጣሪ ባህሪና ፀባዮችን ለመገንዘብ ዉስን ከሆነዉ አቅሙ በላይ ስለሚሆንበት በእምነት ከመቀበል በቀር ሌላ አማራጭ ሊኖረዉ አይችልም ።
◈ ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት በማድረግና ከቅዱሳን አባቶች በተላለፈልን ትምህርት መሠረት ኃያሉ እግዚአብሔርን በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን። እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፤ ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑን ቅዱሳት መጽሐፍት ያስረዳሉ።

◈ የእግዚአብሔርን አንድነት የምናምነዉ ፦ በፈጣሪነት፣ በአምላክነት ፣ በአገዛዝ ፣በፈቃድ ፣ በስልጣን እነዚህን በመሳሰሉት የመለኮት ባህሪያት ነዉ። / መለኮት ወይም ማለኹት/ በዕብራይጥስ ቋንቋ መንግስት ማለት ነዉ። በግዕዝ ግን ባህሪ ፣ አገዛዝ ፣ ስልጣን ማለት ነዉ። ሦስትነቱን የምናምነዉ ደግሞ በስም ፣ በግብር/በኩነት/ ፣በአካል ነዉ።

> እንዳለ/ ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቂሳሪያ /።

የአብርሃሙ ቅድስት ሥላሴ ከክፉ ሁሉ ይሰዉረን !

አምባዬ EOTC Media
ቻናላችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በTelegram https://t.me/ambayepost

በYouTube https://www.youtube.com/

በFacebook https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

አምባዬ EOTC MEDIA ,

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አምባዬ EOTC MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share