SHEGER FM 102.1 RADIO

SHEGER FM 102.1 RADIO SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!
(2)

Hear us live on www.ShegerFM.com, dedicated phone numbers, and mobile Apps. ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡

ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡

፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (Information & Entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡

ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

 #ሸገርካፌ ‹‹በGICC ጥላ ሥር ሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብን ባለውለታዎች›› ከተለያዩ ሀገራት ባለሙያዎች ጋር የተደረገ ውይይት! - 5ኛ ሳምንት - መስከረም 4 /2018
14/09/2025

#ሸገርካፌ

‹‹በGICC ጥላ ሥር ሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብን ባለውለታዎች››

ከተለያዩ ሀገራት ባለሙያዎች ጋር የተደረገ ውይይት! - 5ኛ ሳምንት - መስከረም 4 /2018

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!Sheg...

 #ሸገርካፌ "አድዋ በሐገራችን ምን አዲስ ነገር ፈጠረ››? መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወ/ማርያም እና ዮናስ አሽኔ ጋር 13ኛ ሳምንት  -  መስከረም 4 2018
14/09/2025

#ሸገርካፌ

"አድዋ በሐገራችን ምን አዲስ ነገር ፈጠረ››?

መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወ/ማርያም እና ዮናስ አሽኔ ጋር 13ኛ ሳምንት - መስከረም 4 2018

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!Sheg...

መስከረም 4 2018የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና  ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል  8.4  ከመቶው  50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፣ 1,249 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላ...
14/09/2025

መስከረም 4 2018

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 8.4 ከመቶው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፣ 1,249 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም ተብሏል።

በ2017 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛው 591 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።

በዚህ ወቅት 2,384 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለጋዜጠኛች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ 888 ተማሪዎች፣ ኦሮሚያ 794 ተማሪዎች፣ አማራ ክልል 385 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አምጥተዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 585,000 ተማሪዎች የ12 ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን 8.4 ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ አምጥተዋል ተብሏል።

በ2016 ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ እንደነበሩ ይታወሳል።

የዘንድሮው ተፈተኞች ያመጡት አማካኝ ውጤት 31 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።

አዳሪ ትምህርትቤቶች 87 ከመቶ ያስፈተኑትን ተማሪ ያሳለፉ ሲሆን ኮሚኒቲ ትምህርት ቤቶች ደግሞ 86 በመቶ አሳልፈዋል።

የመንግስት ትምህርት ቤቶች 5 6 በመቶ ተማሪ አሳልፈዋል።

በዚህ ዓመት 50 ትምህርት ቤቶች በሙሉ ያስፈተኑትን ተማሪ ያሳለፉ ሲሆን፣1249 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ በዚህ አመት አላሳለፉም።

የዘንድሮው ውጤት ካለፉት ዓመታት
የተሻለ ለመሆኑ የወላጆች ክትትል ከፍ ማለቱ ፣ የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱ አንዱ ምክንያት ነው ተብሏል።

የዘንድሮ የ12 ተኛ ክፍል ተፈተኞች አዲሱ የፈተና አሰጣጥ ሲጀመር የ9ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ ተማሪዎች ናቸው።

አሁን ተማሪዎች የፈተና ስርቆት እንደማያዋጣ አውቀዋል የምንፈልገው ለውጥ እየመጣ መሆኑን እየተመለከትን ነው ብለዋል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ።

የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ጣራ ከዚህ በኋላ እየጨመረ ይመጣል የሚል ግምት እንዳላቸውም አብራርተዋል።

የፈተናው ውጤት እስከ ነገ ከሰዓት ድረስ ይለቀቃል ተብሏል።

በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

  የሩሲያ አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካላት(ድሮኖች) ወደ ፖላንድ ግዛት መዝለቃቸው ዋርሶን ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹን የአውሮፓ ኃያላንን ተቃውሞ አበርትቶታል፡፡ሞስኮ በፖላንድ የትኛውም ዒላማ ላይ ...
13/09/2025



የሩሲያ አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካላት(ድሮኖች) ወደ ፖላንድ ግዛት መዝለቃቸው ዋርሶን ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹን የአውሮፓ ኃያላንን ተቃውሞ አበርትቶታል፡፡

ሞስኮ በፖላንድ የትኛውም ዒላማ ላይ ድብደባ የመፈፀም ዓላማም ፍላጎትም የለኝም እያለች ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የድሮኖቹ ወደ ፖላንድ ግዛት መዝለቅ ስህተት ሊሆን ይችላል? ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

https://youtu.be/uU4P-1uIFlI

የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

 #የጨዋታእንግዳ የአቶ መንገሻ ከበደ ተሰማ ጨዋታ 5ኛ ሳምንት ክፍል 1 - መስከረም  3 2018
13/09/2025

#የጨዋታእንግዳ

የአቶ መንገሻ ከበደ ተሰማ ጨዋታ 5ኛ ሳምንት ክፍል 1 - መስከረም 3 2018

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!Sheg...

መስከረም 3 2018 ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የመጣው አንዱ ችግር ሁሉም ሰው አዋቂ እና ሁሉም ሰው ተንታኝ ሆኖ የመታየቱ ነገር ነው፡፡ሁሉ ፖለቲከኛ፣ ሁሉ አዋቂ፣ ሁሉ ምክር ሰ...
13/09/2025

መስከረም 3 2018

ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የመጣው አንዱ ችግር ሁሉም ሰው አዋቂ እና ሁሉም ሰው ተንታኝ ሆኖ የመታየቱ ነገር ነው፡፡

ሁሉ ፖለቲከኛ፣ ሁሉ አዋቂ፣ ሁሉ ምክር ሰጪ ወዘተ… በሆነበት በተለይም ሳይንሳዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉን አውቃለሁ ባይ ሀሳብ እና አስተያየት ሰጪ ሲበዛ ጉዳቱ ከፍተኛ እንደሆነ ይታሰባል፡፡

በዚህ ዙሪያ ባለሙያዎችን አነጋግረናል፡፡

https://youtu.be/iszz8ho_SOY

ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

መስከረም 3 2018 ላለፉት ዓመታት ግብፅ እና ሱዳን አንዴ ወደፊት አንዴ ወደ ኋላ እያሉ እና ሀሳባቸውን ደጋግመው እየቀያየሩ የኖሩበትን የህዳሴ ግድብን ኢትዮጵያ አስመርቃች፡፡በምርቃውም ላይ...
13/09/2025

መስከረም 3 2018

ላለፉት ዓመታት ግብፅ እና ሱዳን አንዴ ወደፊት አንዴ ወደ ኋላ እያሉ እና ሀሳባቸውን ደጋግመው እየቀያየሩ የኖሩበትን የህዳሴ ግድብን ኢትዮጵያ አስመርቃች፡፡

በምርቃውም ላይ እንግዶቿ እንዲሆኑ ግብፅና ሱዳን ጥሪ ቢደርሳቸውም ጥሪዋን ተቀብለው የደስታዋ ተካፋይና የጋራ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ አኩርፈው ቀርተዋል፡፡

በተለይም ግብፅ ማግስቱን ደብዳቤ ይዛ ለክስ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ሄዳለች፡፡

ባለቀና በተጠናቀቀ ግድብ ዙሪያ የፀጥታውን ም/ቤት ኢትዮጵያን ክሰሱልኝ ማለቱን ምን አመጣው?

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ግድቡን ጨረስኩ ብላ መተኛት ይኖርባት ይሆን? ወይስ ሌላ ስራ ይጠብቃታል?

https://youtu.be/XZTWVV7B9xc

ቴዎድሮስ ወርቁ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

መስከረም 3 2018 ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትቆጭበትና በዘፈን ብቻ ስታሞግሰው በኖረችው የአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ሰርታ ሀይልም አመንጭታ ወዳጅ ዘመዶቿን ጠርታ ከቀናት በፊት (ጳጉሜ 4/2017)...
13/09/2025

መስከረም 3 2018

ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትቆጭበትና በዘፈን ብቻ ስታሞግሰው በኖረችው የአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ሰርታ ሀይልም አመንጭታ ወዳጅ ዘመዶቿን ጠርታ ከቀናት በፊት (ጳጉሜ 4/2017) አስመርቃለች፡፡

ላለፉት 14 ዓመታት በልዩ ልዩ አለም አቀፍ ጫና እና ድካም ተሰርቶ ስለተመረቀው የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያን ምን ይላሉ?

https://youtu.be/Ls2XqgulVxA

ማርታ በቀለ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

  ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2018 በቅዳሜ ጨዋታ ዝግጅታችን እነዚህን መሰናዶዎች ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡ የቅዳሜ ጨዋታ ማስጀመሪያ የሆነው  #ማሟሻ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይጀመራል፡፡ በእሸቴ ...
13/09/2025



ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2018 በቅዳሜ ጨዋታ ዝግጅታችን እነዚህን መሰናዶዎች ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡

የቅዳሜ ጨዋታ ማስጀመሪያ የሆነው #ማሟሻ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይጀመራል፡፡

በእሸቴ አሰፋ የሚዘጋጀው የመቆያ መሰናዶም ከማሟሻ ይከተላል፤ በዚህ ዝግጅት ያለፈው ሀሙስ ስለተከበረው የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ እና ስለ #እንቁጣጣሽ በዓል እየሰማን እንቆያለን፡፡

ተፈሪ አለሙ በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ ስለ #ሶማሊላንድ ይነግረናል፡፡

በፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት አቶ ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደርጉት ቆይታ (የመጨረሻው እና 5ኛው ሳምንት)፤ በቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲል ይጀምራል፡፡

ድራማ እና ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

 #የጨዋታእንግዳ በፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት እና በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ  በተለያዩ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች  ያገለገሉት አቶ መንገሻ ከበደ ተሰማ ናቸው፡፡ 5ኛ ሳምንት ...
12/09/2025

#የጨዋታእንግዳ

በፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት እና በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ በተለያዩ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት አቶ መንገሻ ከበደ ተሰማ ናቸው፡፡

5ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 3 /2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እንዲሁም እሑድ መስከረም 4 /2018 ከሞሽቱ 1፡00 በድጋሚ እንድታደምጡ እንጋብዛችኃለን::

ሸገር የእናንተ ነው!

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!Sheg...

መስከረም 2 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ብሪታንያበአሜሪካ ሴቶችን የወሲብ ባሮቹ በማድረግ ሲገለገልባቸው ነበር ከተባለው ጄፍሪ ኤፒስተን ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉት በአሜሪካ የብሪ...
12/09/2025

መስከረም 2 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

#ብሪታንያ

በአሜሪካ ሴቶችን የወሲብ ባሮቹ በማድረግ ሲገለገልባቸው ነበር ከተባለው ጄፍሪ ኤፒስተን ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉት በአሜሪካ የብሪታንያው አምባሳደር ፒተር ማንዴልሰን ከሀላፊነታቸው ተባረሩ፡፡

አምባሳደሩ ከሀላፊነት የተባረሩት በቀደመውጊዜ ለኤፒስተን የፃፉት የኢሜይል መልዕክት ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ኤፒስተን ተይዞ በታሰረበት እስር ቤት በአወዛጋቢ ሁኔታ ሕይወቱ ያለፈው ከ6 አመታት በፊት ነው፡፡

የሰውየው ህይወት ቢያልፍም ወንጀሉ ብዙ ዝነኞችን በማነካካቱ አሁንም አነጋጋሪነቱ አልሰከነም፡፡

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም በጄፍሪ ኤፒስተን ጉዳይ አሁንም ስማቸው ተያይዞ እየተነሳ ነው፡፡

ትራምፕ በቀደመው ጊዜ ለግለሰቡ ፅፈውታል የተባለ የልደት ማስታወሻ በኮንግረሱ ይፋ ተደርጓል ቢባልም ዋይት ሐውስ ማስታወሻው በትራምፕ የተፃፈ እንዳልሆነ በማስተባበል መጠመዱ ይነገራል፡፡

ከሀላፊነት የተባረሩት ማንዴልሰን በአሜሪካ የብሪታንያ አምባሳደርነቴ ታላቅ ስኬቴ ነበር ማለታቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

#ኢንዶኔዥያ

በኢንዶኔዥያዋ የቱሪስቶች መዝናኛ ደሴት ባሊ በከባድ የጎርፍ አደጋ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ታወጀ፡፡

በደሴቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ የታወጀው በዚያ ከባድ ጎርፍ ያስከተለው አደጋ 14 ሰዎችን ከገደለ በኋላ እንደሆነ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡

በባሊ ከባድ ጎርፍ የደረሰው ባለፈው ሳምንት ሲጥል በሰነበተውዶፍ ዝናብ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ዶፍ ዝናብ መጣሉ ቢያቆምም ጎርፍ እና የውሃ ሙላ ሰፊ አካባቢን ማዳረሱ ታውቋል፡፡

በጎርፍ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሌላ የደረሱበት የጠፋም እንዳሉ ተጠቅሷልል፡፡

መጠነ ሰፊ የነፍስ አድን ጥረት እየተዳረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ባለ ከኢንዶኔዥያ ግዛቶች ሁሉ በውጭ ቱሪስቶች መስህብነቷ የሚደርስባት እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡

#አሜሪካ

አሜሪካ በየመን ሁቲዎች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለችባቸው ተባለ፡፡

ታላቋ አገር በሁቲዎቹ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ የጣለችባቸው ከእስራኤል ጋር ክፉኛ እየተጋጩ መምጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡

አዲሱ የአሜሪካ ማዕቀብ 32 የሁቲዎቹን ሹሞች እና 4 መርከቦቻቸውን የተመለከተ ነው ተብሏል፡፡

አሜሪካ በሁቲዎቹ ላይ የጣለችው ማዕቀብ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያቸውን እንደሚያሰናክልባቸው ተጠቅሷል፡፡

ሁቲዎቹ እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች አንስቶ ለፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት ከእስራኤል ጋር ነገር እየተፈላለጉ ነው፡፡

የየመንን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የጦር እና የፖለቲካ ሸሪኮች መሆናቸው ይነገራል፡፡



የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻር በብርቱ ብርቱ ወንጀሎች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻር በወንጀል የተከሰሱት በተለምዶ ዋይት አርሚ የተሰኘው የኑዌር ወጣቶች ታጣቂ ቡድን በአፐር ናይል ግዛት ናሲር ከተማ በሚገኝ የመንግስት የጦር ሰፈር ላይ አድርሶታል በተባለ ጥቃት ምክንያት እንደሆነ TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡

በዚያ ጥቃት 250 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ከማቻር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው ይባላል፡፡

በዚሁ ምክንያት ማቻር ካለፈው መጋቢት ወር አንስቶ በቁም እስር ሆነው መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት ለናሲሩ ጥቃት ከማቻር ራስ አልወርድም እያለ ነው፡፡

ከማቻር ጋርም አባሪ ተባባሪዎቻቸው ናቸው የተባሉ 8 የቀድሞ ሹሞችም ክስ እንደተመሰረተባቸው ተሰምቷል፡፡

የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

ሸገር ሼልፍ - ማራኪ የመስከረም  ትረካዎች  - መስከረም 2 2018
12/09/2025

ሸገር ሼልፍ - ማራኪ የመስከረም ትረካዎች - መስከረም 2 2018

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our ...

Address

Addis Ababa Bahirdar Road
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00
Tuesday 08:00 - 00:00
Wednesday 08:00 - 00:00
Thursday 08:00 - 00:00
Friday 08:00 - 00:00
Saturday 08:00 - 01:00
Sunday 08:00 - 00:00

Telephone

+251111272754

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SHEGER FM 102.1 RADIO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SHEGER FM 102.1 RADIO:

Share

Category