Every Day Amhara

Every Day Amhara information is a power!.

የሌባ አይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ነው ነገሩ።
13/09/2026

የሌባ አይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ነው ነገሩ።

ጀግናማ ካለበት ላይ አለ፤ ከጀግና ጋር የዋለ ሁሉ ጀግና የሆነ ይመስለዋል። ዶ/ር ሲሳይ አወግቸው  #7ለ70
10/09/2026

ጀግናማ ካለበት ላይ አለ፤ ከጀግና ጋር የዋለ ሁሉ ጀግና የሆነ ይመስለዋል።

ዶ/ር ሲሳይ አወግቸው
#7ለ70

10/09/2026


በዛሬው ዕለት በርካታ ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ በምህረት ከእስር እንደሚፈቱ ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች።
ታሳሪዎቹን ለማስፈታት የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮምሽን ላለፉት ወራት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ነበር። በሂደቱ መንግስት ያቀረበውን "የይቅርታ ስነድ" እንፈርምም ያሉ 28 ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ግን አሁን ከሚፈቱት ታሳሪዎች ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። [ዋዜማ]

09/09/2026

ድሮም ከሃዲ ከሃዲ ነው። አስመሳይ

ይችን ዘገባ አስታወሳችኋት? ማን ማንን እንደካደ 🤭
09/09/2026

ይችን ዘገባ አስታወሳችኋት? ማን ማንን እንደካደ 🤭



መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ ደርሷታል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ( )

መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡

ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡-

1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ
5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ
6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው
7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ
8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ
11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
12. አቶ አለልኝ ምህረት
13. አቶ መንበር አለሙ
14. አቶ ማይክ መላክ
15. አቶ አሳምነው ታደሠ
16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ
17. አቶ እሱባለው በለጠ
18. አቶ እስክንድር ሽፈራው
19. አቶ መሰለ ቸሩ
20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ
21. አቶ ጫኔ ዘየደ
22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ
23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ
24. አቶ ሲሳይ መልካሙ
25. አቶ ታደሰ ወዳይነው
26. አቶ በላይ ሲሳይ
27. አቶ ያሬድ ግርማ
28. አቶ ማረው ስለሺ
29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ
30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ

ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡-

“በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት
ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ያመላክታል፡፡

ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡

አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA

08/09/2026

እንደ አማራ ገበሬ የሚያሳዝን የለም፤ ከጠላት በላይ ልጆቹ ጠላት ሆኑበት። እንዳይንከባከብ እና እንዳይሰበሰብ አደረጉት።

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Every Day Amhara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share