Natan press

Natan press news

ለኔ ጀዋር ልክ ነዉ...🤔ለሞን...? በለኛ እሱ እንደ  ጨለማው ደሴት ሊቀ ጠበብነቱ የብርሃን  ከተማ ከንቲባዋን ሊመርጥ አይችልምና!!የጨለማው  ደሴት ነጋሪው፦ለጥፋት አጀንዳው መፅዎች  የሆ...
24/05/2025

ለኔ ጀዋር ልክ ነዉ...🤔

ለሞን...? በለኛ እሱ እንደ ጨለማው ደሴት ሊቀ ጠበብነቱ የብርሃን ከተማ ከንቲባዋን ሊመርጥ አይችልምና!!

የጨለማው ደሴት ነጋሪው፦

ለጥፋት አጀንዳው መፅዎች የሆኑ ሌቦችን መንጥራ እያፀዳች ውብ ከተማ የምትፈጥር ከንቲባ ሊወድልክ ነው??

ከሌቦች መዳፍ ነጥቃ ለተማሪዎች ምገባ አዉላ ማህበራዊ ፍትህ ለማንገስ እና ሀገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ በማፍራት ትዉልዱን ሀገርን የምትገነባ ከንቲባ እንድትመቸዉማ አትጠብቅ።

የበጎነት መንደር እየገነባች የደሀ እንባ የምታብስ ከንቲባ መቸም አስለቃሽ የጨለማ ደሴት የጎበዝ አለቆች በሷ ሰላም ሊያገኙ አይችሉ ።

22የምገባ ማዕከል ገንብታ የምትመግብ ከተማ እየፈጠረች ተልዕኮ ተቀባይ ያሳጣችን ከንቲባማ አይፈልጉም እነሱ።

ስማ እንጅ እጅ ከወርች አስረዉት የነበረዉን የከተማ ገቢ ከ 35ቢልየን ወደ 238ቢልየን በ 4አመት በማስገባት ምርጧን ዉብ አፍሪካዊት ከተማ እየገነባች ያለች ጨለማን አሸናፊ አብሪ ኮከብ ሆና ሴራቸዉን የምታከሽፍባቸዉን አዴ አዳነችን ዝም ሊሏት አትሸወድ ከመሠረቱ ቦታ እንዳይኖራቸዉ ህፃናት ላይ ትኩረት በማድረግ አፍሪካዊት ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧን ከተማ እዉን ለማድረግ ደፉ ቀና እያለች አይደክሜዋን ከንቲባማ እንዴትስ እኩያን ሊወዷት።

ለእናቶች እረፍት በየተቋሙ የህፃናት ማቆያ፣ እንጀራ መጋገሪያ ፣የሴቶች ስብዕና መገንቢያ እና ማበልፀግያ እየገነባች ለሴቶች ደራሿ ከንቲባ ለጨለማዉ ደሴት አስለቃሾች የሬት ታክል ትመራቸዉ እንጅ ሰላም አትሰጣቸዉ ብርሃን ከጨለማ ጋር ህብረት የለዉምና።

ህዝቡን የሰላም አርበኛ አድርጋ ያሰቡትን እያከሽፊች ሰላምን በከተማዋ ያመጣችን ከንቲባማ
፦የጥላቻ ሰባኪዎች
፦በተከበብን ሰዉ ያስጨረሱ
አፍራሾች እንዲደግፏት አትጠብቅ ባይሆን ሰሞኑን የበግ ለምድ ለብሰዉ ደሞዝ! ህዝባችን! እያሉ ከች ብለዋል ግን ከንቲባዋ አይመቹም ደግሞ🤔 ከተማዋ እስታንዳርድ የጠበቀች ትሁን ብለዉ በኮሪደር ልማት በየ ቦታዉ ካሜራ ገጥመዋል፤

ህዝቡም ባኗል🤔 የሚሰራለትን አዉቆ ነቄ ብሏል!!

አሁንስ ማልቀስ ይሻላል😭
ነዉስ ማስለቀስ😭😭

2ቱም አይሻልም በብርሃን ብቻ ተደመር!!

13/06/2024
21/05/2024
21/05/2024

በልጆቿ ትጋት የደመቀች ከተማ :- አዲስ አበባ

ብልጽግና በትልቁ የሚያስብ ፤ ያሰበውን በጥራትና በጊዜ የሚፈጽም ፤ ዛሬ ላይ ነገን ጭምር የሚገነባ ፤ ተሻጋሪ ሀሳብ ያለው የትውልድ ፓርቲ ነው። በዚህም የትጋትና የልህቀት ዕሳቤ እንችላለን ብለን ብቻ ሳይሆን ችለንንና ሰርተን አጠናቀን ሪቫኖችን በመቁረጥ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራን ማስቀመጥ ችለናል።

አዲስ አበባ በህብረብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ሰላሟን ያጸናች፣ የመደመር ዕሳቤን አንግበው ቀን ከለሊት ለብልጽግናዋ በሚተጉ ልጆቿ አንደስሟ እየደመቀች ያለች አፍሪካዊት የተሞክሮ ማዕከል እየሆነች የምትገኝ ውብ ከተማ በመሆን ላይ ነች።

የፓርቲያችን ዓላማ ሁለንተናዊ ብልፅግናን በሚያረጋግጥ አካታች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሁለንተናዊ ተምሳሌት መሆን ነው። አድስ አበባ የዜጎችን ማህበራዊ መስተጋብር የሚያስተሳስርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት
የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በላቀ ትጋት በማከናወን ቃልን በተግባር የሚያስመሰክር ዘላቂ የሆነን ሁለንተናዊ የብልጽግና ተምሳሌትነትን የሚያበስር የኮሪደር ልማት ስራ በፍጥነትና ጥራት እየተሰራ ይገኛል።

ብልጽግና ባስቀመጠው ግልጽ ራዕይ መሰረት የከተማዋን ታሪክና ስም የሚመጥን ከፍታ ላይ በማድረስ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚያፀና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ፣ የዲፕሎማሲ ስበት ማዕከል ለማድረግ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ሰውተኮር ልማቶች ተከናውነዋል።

አሁን በፍጥነትና በጥራት በነዋሪዎቿም ትብብር በመሰራት ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማችን አዲስ አበባ የሚመጥናትም የሚገባትም ብልፅግና መሆኑን ያስመሰከረና አጠቃላይ ገፅታን በመቀር ለነዋሪዎቿ ምቹና ፅዱ የሚያደርጋት ይሆናል።




Prosperity Party Yeka Branch - ብልጽግና

21/05/2024
21/05/2024

አዲስ አበባ በትጉህ ዕጆች እየለማች፣ በታታሪ ነዋሪዎቿ ሰላሟን በማፅናት ለትውልድ በሚሻገር ምንዳ ሀገራዊ የመደመር ውጤትና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች!!

ትጋት ፣ ቁርጠኝነት ፣ ህብረትና ፣ ትውልድ ተሻጋሪነት የፓርቲያችን የመደመር እና የብልፅግናችን የስኬት ጉዞ መገለጫዎች ናቸው። ብልጽግና የትውልድ ፓርቲ በመሆኑ በመደመር መርህ በትውልድ ቅብብሎሽ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ያፀናል። በዚህም በከተማችን እየተተገበሩ የሚገኙ የልማት ስራዎች ዛሬን ከነገ ጋር የሚያስተሳስሩና የትውልድን አሻራ ለዘመናት የሚያሸጋግሩ ጥራትና ፍጥነትን ያማከሉ ናቸው።

ነገን ታሳቢ ያደረጉ የከተማዋ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች፣ ጽዱና ውብ የሆኑ የትራፊክ ፍሰትን የሚያሳልጡ አደባባዮቿ ፣ ታላላቅ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ፣ የሳይንስናቴክኖሎጂ የምርምር ተቋማት ፣ የታሪክና ባህል ሙዚየሞች ፣ መናፈሻዎች ፣ በመሪዎቿ ድንቅ ዕሳቤና ትጋት እየተተገበሩ የሚገኙት የጫካ ፕሮጀክትና የኮሪደር ልማት እውነትም ቃልን በተግባር የሚያፀና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የመሆን ግስጋሴያችንን የሚያረጋግጡ የፓርቲያችን የአስተሳሰብና የተግባር ውጤት ማሳያ ናቸው።

በመደመር የትጋት ዕጆች እያበበችና እየደመቀች የመትገኘዋ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት በሚያሻሻል መልኩ ስሟንና ታሪኳን በሚገልጽ ከፍታ ተዋዳዳሪና የትኩረት ማዕከል መሆን ችላለች።

በዚህም የነበረውን የስራ ባህል በመለወጥ 7/24 የነቃችና በስራ ላይ ያለች ከተማ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮችን በማሳለጥ ተደጋጋሚ የሆኑ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናንና ሽልማቶችን ወስዳለች።

በአጠቃላይ በህብረ ብሔራዊነት የፍቅርና የሰላም ከተማ የሆነችዋ ከተማችን የአፍሪካ መዲና እና የዓለም ዲፕሎማቲክ የስበት ማዕከል መሆኗን የሚያጎሉ ስራዎች ላይ ነች። አዲስ አበባ በልጆቿ ደምቃ፣ በትጉህ ዕጆች እየለማች፣ በታታሪ ነዋሪዎቿ ሰላሟን በማፅናት ለትውልድ የሚሻገር ምንዳን በማስቀመጥ የወል እውነት የሆኑ ልማቶቿን አሳልጣ ሀገራዊ የመደመር ውጤትና አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች።




Prosperity Party Yeka Branch - ብልጽግና

Address

Addis Ababa
NATAN

Telephone

+251921387265

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Natan press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share