
02/12/2024
የባይደን የመሪነት ዘመን ሊጠቃለል በቀሩት 50 ቀናት ውስጥ የዩክሬንን የጦር መሳሪያ ክምችት ለማሳደግ ይሰራል ተባለ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን፤ የባይደን የመሪነት ዘመን ሊጠቃለል በቀረው የ50 ቀን እድሜ አሜሪካ የዩክሬንን የጦር መሳሪያ ክምችትን ለማሳደግ ትሰራለች ብለዋል።
በእነዚህ 50 ቀናት ውስጥ ዩክሬን በጦር ሜዳ አቋሟን ለማጠናከር የሚረዱ ሁሉንም መሳሪያዎች ለማቅረብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሚደረገዉ የመሳሪያ ድጋፍ ዩክሬን በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን በድርድር ጠረጴዛው ላይም የበለጠ ጠንካራ እንድትሆን ይረዳታል ብለዋል፡፡
አማካሪዉ አክለውም፤በፕሬዝዳንት ባይደን ከፍተኛ ወታደራዊ አቅርቦትን እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸዉም ተናግረዋል፡፡
ባይደን ስልጣናቸዉን እስኪያስረክቡ ድረስም ወደ ዩክሬን የሚደረጉ እያንዳንዱ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፎች በኮንግረንሱ ፈቃድ ማግኘታቸዉንም አማካሪዉ ገልጸዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም