23/10/2025
ዘማሪ ዓለማየሁ ገ/መስቀል #ወደ #ጌታ ተሰበሰቡ፡፡
ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስተው መጽሐፍ ቅዱስን በዝማሬ እየገለጡ በጽናት ሲያገለልሉ የቆዩት ዘማሪ አለማየሁ በስደት ዘመናት ሳይቀር በጌታ ጸንተው የቆሙ ወንድም እንደነበሩ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡
ዘማሪ ዓለማየሁ ግጥም እና ዜማ ራሳቸው እያዘጋጁ በኦሮምኛ፣ በአማርኛና በጌዴዎፋ ባቀረቧቸው ዝማሬዎች ብዙዎችን ያጽናኑና ያስተማሩ አገልጋይ ነበሩ፡፡
አገልጋዩ በትጋት፣ በጽናትና በመሰጠት ባገለገሉት ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተቀባይነት እንደነበራቸው የደቡብ ቀጣና አመራሮች ተናግረዋል።
ዘማሪ ዓለማየሁ ገ/መስቀል ባደረባቸው ሕመም ለሕክምና ወደ ሐዋሳ ያኔት ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተገልጿል።
የዘማሪው የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የቤተ ክርስቲያን አባላት በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ እንደሚፈጸም በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የደቡብ ቀጣና ጸሐፊ የሆኑት አቶ ጥላሁን መኮንን አስታውቀዋል፡፡
The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል።