ማዕድ maed ethiopia

ማዕድ maed ethiopia የአለማችን ፈጣን የመረጃ ምንጭ
Follow for up-to-date info.

የሁሉንም ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳ እና ነጋዴዎችን አሳትፏል የተባለ ልዑክ መቐሌ ገባ።በኢትዮጵያ ከ12 ክልሎችና ከሁለት ከተሞች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳ እና ነጋዴ...
28/07/2025

የሁሉንም ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳ እና ነጋዴዎችን አሳትፏል የተባለ ልዑክ መቐሌ ገባ።

በኢትዮጵያ ከ12 ክልሎችና ከሁለት ከተሞች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳ እና ነጋዴዎች ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎችን ያቀፈ ልዑክ መቐሌ መግባታቸው ተነግሯል።

እንደ ክልሉ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ልዑኩ ከጊዚያዊ አስተዳደር፣ ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሲቪክ ማህበራት ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

በትግራይ ኃይሎች እና የፌደራል መንግስት መካከል እየተካረረ የመጣ አለመግባባት ለመፍታት አስታራቂ አካላት ወደ ትግራይ ሲያቀኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
@ማለዳ ሚዲያ

26/07/2025

በትግራይ ክልል አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ የክልሉ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተገለጸ

ሐምሌ 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የፖለቲካ አለመግባባት ስጋት በመፍጠሩና ለጦርነት አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ፤ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑን ለአሐዱ አስታውቀዋል።

"እኛ ጦርነት አንፈልግም" ያሉት ወጣቶቹ፤ "ከየትኛውም በኩል ኢትዮጵያዊነታችንን ለመግፋት የሚደረግ ጫና ተቀባይነት የለም" ብለዋል፡፡ "ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ስጋት ስላሳደረብን፤ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለቀን እየወጣን ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

"በክልሉ እስር፣ ግድያና ማስፈራራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን የሚባባስ እየሆነ በመሄዱ ስጋት እየተፈጠረብን ነው። በዚህም ምክንያት ሕይወታችንን ለመታደግ ስደትን እየመረጥን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"እኛ በአሁኑ ወቅት ወደ ጦርነት የሚያስገባን ጉዳይ የለንም። ከሆነም በንግግር መፍታት ነው የምንፈልገው" ያሉም ሲሆን፤ "ሆኖም ይህንን እንድናደርግ ዕድል የሚሰጠን ባለማግኘታችን በቂ ገንዘብ ያላቸው ጓዳኞቻችን ተመቻችቶላቸው ከሀገር አስቀድመው ወጥተዋል" ብለዋል።

አሐዱም ስለጉዳዩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማናገር ያደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ አልተሳካም።

ነገር ግን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሕዝቦች (ኢህአፓ) ፓርቲ ዋና ሥራ አስኪያጅና የትግራይ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ወኪል ይሳቅ ወልዳይን እና የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃንን አነጋግሯል።

የኢሕአፓ ዋና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባሉና የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ በሰጡት ምላሽ፤ ህወሓትና የፌደራሉ መንግሥት ወደ ጦርነት በመግባታቸው የትግራይ ወጣት ከኢትዮጵያዊን ወንድም እና እህቶቹ ጋር እንዲዋጋ ሆኗል" ሲሉ አስታውሰዋል።

"እንደ በፊቱ የትግራይ ወጣት ጦርነት አይፈልግም" ያሉት የሥራ አስፈፃሚ አባሉ፤ "አሁን የሚፈልገው ስደት ሳይሆን መማር እና መስራት ወደቀደመው ሕይወቱ መመለስ ነው" ብለዋል።

"የትግራይ ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት ለስራ አጥነት፣ ለከፋ ችግር፣ ለጦርነት እና ለግጭት በመጋለጡ ስደትን እየመረጠ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃነ በሰጡት ምላሽ፤ "በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ አመራሮችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል በተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠትም ተግዳሮት ሆኗል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ወጣቱ ትውልድ በአሁኑ ወቅት ወደ ሳዑዲ አረቢያና በሌሎች ሀገራት በባህር እየተሰደደ ነው፡፡ ይህን ደግሞ እልባት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

"አሁን ላይ የክልሉ ሕዝብ የሚፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰብዓዊ አቅርቦት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ለአሐዱ ቅሬታቸውን የገለጸት የትግራይ ክልል ወጣቶች በበኩላቸው፤ "የሚመለከተው አካል በሀገራችን በሰላማዊ መንገድ ሰርተን የምንቀየርበትን መንገድ እንዲፈጥርልን እንጠይቃለን" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሐዱ

የቀብር ስነ-ሥርዓቱ ነገ ይፈፀማል  | አንጋፋውና ታዋቂው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ  2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።ሥርዓተ...
25/07/2025

የቀብር ስነ-ሥርዓቱ ነገ ይፈፀማል

| አንጋፋውና ታዋቂው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ቤተሰቡ እና ወዳጆቹ በተገኙበት አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል::

ቤተሰቦቹ

ነፍስን በአፀደ ገነት ያኑራት🙏🙏🙏

ፈረንሳይ ለእስራኤል ጀርባ ሰጠችፈረንሳይ ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና ልትሰጥ መሆኑን አስታወቀች።ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣  በመስከረሙ የመንግስታቱ ...
25/07/2025

ፈረንሳይ ለእስራኤል ጀርባ ሰጠች

ፈረንሳይ ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና ልትሰጥ መሆኑን አስታወቀች።

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ በመስከረሙ የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና እሰጣለሁ በሚል አረጋግጠዋል።

“በአሁኑ ሰዓት አስቸኳዩ ጉዳይ ንጹሃንን ማዳን እና የጋዛውን ጦርነት ማስቆም ነው” ሲሉም ጽፈዋል ማክሮን።

በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ፈረንሳይ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና እንድትሰጥ ወስኛለሁም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

ፈረንሳይ እውቅና ስትሰጥ አውሮፓ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገራት መካከል ግንባር ቀደም ያደርጋታል።

ኖርዌይ፣ አየርላንድ እና ስፔን ተመሳሳይ ሂደት ውስጥ እንደሚገቡም ምልክት ሰጥተዋል።

ቢያንስ 142 አገራት ከ193 የመንግስታቱ ድርጅት ዓባላት ውስጥ ለፍልስጤም እውቅና ሰጥተዋል አሊያም እውቅና የመስጠት ሂደት ላይ ናቸው።

እስራኤል የማክሮንን ውሳኔ በጽኑ እንደምትቃወመውም ይፋ አድርጋለች።

ዘገባው የ CNN ነው።

በነዳጅ ዘይት የበለፀገው የሱዳን ኮርዶፋን አካባቢ በጦር ኃይሉ እና በተቀናቃኞቹ ወታደራዊ ኃይሎች መካከል በሚካሄደው ጦርነት ወደ ግጭት ማዕከልነት ተቀይሯል።ላለፉት ሁለት ዓመታት ሁለቱ ተፋላ...
25/07/2025

በነዳጅ ዘይት የበለፀገው የሱዳን ኮርዶፋን አካባቢ በጦር ኃይሉ እና በተቀናቃኞቹ ወታደራዊ ኃይሎች መካከል በሚካሄደው ጦርነት ወደ ግጭት ማዕከልነት ተቀይሯል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ሁለቱ ተፋላማዊ ወገኖች የበላይነት ለማግኘት በሚያደርጉት ከባድ ውጊያ ሰፊዋ ሱዳን ከፍተኛ ውድመትን አስተናግዳለች።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን የገደሉ ጥቃቶች መድረሳቸውን ተከትሎ ትኩረቶች በዚህ የአገሪቱ ክፍል ላይ ወደሚደረገው ውጊያ ሆኗል።
"ኮርዶፋንን የሚቆጣጠር የአገሪቱን የነዳጅ ዘይት አቅርቦት እና ከፍተኛ መጠን ያለው የሱዳንን ነዳጅ በብቃት ይቆጣጠራል" ሲሉ የኦሲስ ፖሊሲ አማካሪ አሚር አሚን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቀሲስ በላይ ይግባኝ አቅርበው የእስር ቅጣታቸው ወደ 3 ዓመት ከሰባት ወር ተቀነሰበሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር በሙስና ወንጀል ...
25/07/2025

ቀሲስ በላይ ይግባኝ አቅርበው የእስር ቅጣታቸው ወደ 3 ዓመት ከሰባት ወር ተቀነሰ

በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር በሙስና ወንጀል እስር እና የገንዘብ ቅጣት የተፈረደባቸው ቀሲስ በላይ መኮንን የእስር ቅጣታቸው መቀነሱ ተገለጸ።

በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ተብለው አምስት ዓመት እና 10 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ቀሲስ በላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለታቸውን ተከትሎ የእስር ቅጣታቸው እንዲቀነስ መወሰኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ረቡዕ፣ ሐምሌ 16/ 2017 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት የቀሲስ በላይን ቅጣት ወደ ሦስት ዓመት ከሰባት ወር እስር እንዲቀነስ መወሰኑን ጠበቃቸው አቶ ገብሩ ማህተም ገልጸዋል።

ከቀሲስ በላይ ጋር በተመሳሳይ ክስ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ተከሳሾች እስራቸው ወደ ሦስት ዓመት ዝቅ እንዲል ፍርድ ቤቱ ብይን ማስተላለፉን አቶ ገብሩ አክለዋል።

ቀሲስ በላይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያስገቡት ይግባኝ ለስር ፍርድ ቤት በርካታ የቅጣት ማቅለያ መረጃዎች ቢያርቡም የተያዘላቸው አነስተኛ መሆኑን በመግለጽ ነው።

ጠበቃ ገብሩ እንደሚሉት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቀሲስ በላይ ያቀረቡትን ምክንያት ተቀብሎ ተጨማሪ ሁለት የቅጣት ማቃለያዎችን በመያዝ የእስር ቅጣታቸውን ቀንሶታል።

ወደ 23 የሚሆኑ የቅጣት ማቅለያዎችን ደንበኛቸው እንዳቀረቡ የሚናገሩት ጠበቃው፤ ከእነዚህም መካከል በማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ያላቸው ተሳትፎ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው፣ የጤና ጉዳይ፣ ከዚህ በፊት በወንጀል ተሳትፎ የሌላቸው መሆኑ፣ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የነበራቸው ተሳትፎ የሚሉ ተካተውበታል።

የስር ፍርድ ቤቱ ግን እነዚህን በአምስት "እንደጨመቃቸው" የሚናገሩት ጠበቃው እነዚህ ማቅለያዎች ቢያንስ ወደ ሰባት የሚመነዘሩ ናቸው በሚል ሁለት ተጨማሪ ማቅለያዎችን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንደያዘላቸው ያስረዳሉ።

ፍርድ ቤቱ ሁለት ተጨማሪ ማቅለያዎችን በመያዝም ቅጣቱን መቀነሱን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የቅጣት ውሳኔ የተላለፈው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ መድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጥር 22/2017 ዓ.ም. ነበር።

ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች ዐቃቤ ሕግ ክስ የቀረበባቸው የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ተላልፈዋል በሚል ነበር።

ግለሰቦቹ ላይ የተመሠረተው ክስ በአፍሪካ ኅብረት ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በኅብረቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስድስት ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት ሞክረዋል በሚል ነው።

ጠበቃ ገብሩ እንደሚሉት ከጥፋተኝነት ጋር ተያይዞ፣ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ የተባሉበትን ድንጋጌ የእሳቸውን ተሳትፎ የተጠቀሰባቸውን አዋጅ በተመለከተ እንዲሁም ሌሎች የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን አንስተው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያቀረቧቸው ቅሬታዎች ውድቅ መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።

ከቅጣት ጋር ተያይዞ ሁለት ቅሬታዎችን ማቅረባቸውን የሚናገሩት ጠበቃ ገብሩ የመጀመሪያው ቅሬታ የቅጣት መጠኑ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የቀሲስ በላይ የቅጣት ደረጃ ሲያዝ የእሳቸው ተለይቶ መካከለኛ በሚል እና የሌሎቹ በቀላል መያዙን በመጥቀስ፤ መካከለኛ ተብሎ መያዙ አግባብ አይደለም በሚል ተከራክረዋል።

ሌላኛው ደግሞ ካለባቸው የጤና እክል እና ከነበራቸው ማኅበራዊ አስተዋጽኦ አንጻር በማስጠንቀቂያ በሚል የገደብ ጥያቄን ቢያቀርቡም ሁለቱም ውድቅ መደረጉን ያስረዳሉ።

“ወደ ማዶ” የተሰኘ አለም አቀፍ የቲያትር ጉዞ ሊያካሂድ ነውሐምሌ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የቲያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ወደ ማዶ...
25/07/2025

“ወደ ማዶ” የተሰኘ አለም አቀፍ የቲያትር ጉዞ ሊያካሂድ ነው

ሐምሌ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የቲያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ወደ ማዶ የተሰኘ ቲያትር አለም አቀፍ የቲያትር ጉዞ ሊያካሂድ መሆኑን ዋካ ኢቨንትና ፕርሞሽን አስታውቋል።

በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ሀገራት በ30 መድረኮች ይታያል የተባለው “ወደ ማዶ” ቲያትር ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ከማዝናናትም ባለፈ ከዝግጅቱ የሚገኘው ገቢ ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል እንደሚውል አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ይህንኑ በጎ አላማ ለማሳካትም ከመርጃ ማእከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተከናውኗል።

ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ፣ ሀረገወይን አሰፋና የኋላሸት ዘሪሁን የሚተውኑበት በሶስት ሰው የሚቀርብ ቲያትር መሆኑ የተገልጸ ሲሆን በአፍሪካ ካሁን ቀደም ባልተካሄደባቸው ሀገራትና ብዙ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበታል በሚባሉ ሀገራት በቅድመ ጥናት እንደተመረጠም ተገልጿል።

ቲያትሩ ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ለሁሉም ኢትዮጵያውን በሃሳብም በዘውግም ቅርብ እንደሚሆን ዋካ ፕሮሞሽን እና ኢቨንት አስትውቋል።

ወደ ማዶ የተሰኘው ቲያትር በመጪው ነሐሴ ወር ይፋዊ የመክፈቻ መርሃግብር የተለያዩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት እንደሚከናውንም ዛሬ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ዋካ ኢቨንትና ፕሮሞሽን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

“በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱ ሰዎች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” -ፌደራል ፖሊስየፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው...
25/07/2025

“በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱ ሰዎች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” -ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ የሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱት ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል ሲል አስታወቀ።ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ለሕግ የማቅረብ ሥራን አጠናክሬ እቀጥላለሁም ብሏል።

“በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ እንዲሁም በሁሉም መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ አሰሳና ፍተሻ እንደሚካሄድ ገልጿል፤ ዋነኛ ትኩረቴ “በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ” ነው ሲል አስታውቋል።ፌደራል ፖሊስ ይህንን ያስታወቀው በቀጣይ ሦስት ወራት (ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በተዘጋጀ የፀጥታ ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ውይይቱን በመሩበት ወቅት በቀጣይ ሀገራችን ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የምታስተናግዳቸውን ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲከናወኑ ከእንግዳ አቀባበል ጀምሮ ስምሪቱን በተደራጀ መልኩ መምራትና ማስተባበር እንደሚያስፈልግ መናገራቸውንም መረጃው አካቷል።

“ፍየሎቼን አስረገጥክብኝ” በሚል የ14 ዓመት ታዳጊ ላይ ግድያ ወንጀል የፈፀመው በ12 ዓመት እስር ተቀጣ።በመተማ ከተማ ፍየሎቼን በከብቶችህ አስረገጥክብኝ በማለት የ14 አመት ታዳጊን ህይወት...
21/06/2025

“ፍየሎቼን አስረገጥክብኝ” በሚል የ14 ዓመት ታዳጊ ላይ ግድያ ወንጀል የፈፀመው በ12 ዓመት እስር ተቀጣ።

በመተማ ከተማ ፍየሎቼን በከብቶችህ አስረገጥክብኝ በማለት የ14 አመት ታዳጊን ህይወት ያጠፋ ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት አስታውቋል።

ተከሳሽ ጋሻው ካሴ የሰውን ለመግደል በማሠብ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 እና 01 መካከል በሚገኝና ልዩ ስሙ ማንጎ አትክልት ቦታ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ላይ እድሜው 14 አመት የሆነውን ታዳጊ ሟች ተመስገን ጋሻው ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅሟል።

ተከሳሹ "ለምን በከብቶች ፍየሎቼን ታስረግጥብኛለህ" በማለት ከሟች ጋር ተጣልተው ከተገላገሉ በኋላ ይዞት በነበረው ፈራድ 2 ጊዜ ጭንቅላቱን በመምታት የግድያ ወንጀል መፈፀሙ ነው የተገለጸው።

በተከሳሹ ላይ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ዐቃቤ ህግ በከባድ የግድያ ወንጀለ ክስ የመሰረተ ሲሆንፍርድ ቤቱ የከሳሽን ማስረጃ ከሠማ በኋላ በተራ የሰው መግደል ወንጀል ክሱን በመቀየር እንዲከላከል ብይን በመስጠት የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ቢነገረውም ሊያቀርብ ካለመቻሉም በተጨማሪ ምስክር ማቅረብ አልፈልግም በማለት ፈርሞ ያስገባ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችን መሰል ድርጊት ከመፈፀም ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ12 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉንም ነው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የገለፀው።

የሃያት ሪልስቴት ግንባታ ፈርሶ ሰዎች ሞቱ!በተከታታይ ባለፉት ሁለት ቀናት በአደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱበት በግባታ የሚገኝ የአያት ሪልስቴት ህንፃ ዛሬም አደጋ ደርሶበት ሁለት ሰዎች መቱ ። በተ...
21/06/2025

የሃያት ሪልስቴት ግንባታ ፈርሶ ሰዎች ሞቱ!

በተከታታይ ባለፉት ሁለት ቀናት በአደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱበት በግባታ የሚገኝ የአያት ሪልስቴት ህንፃ ዛሬም አደጋ ደርሶበት ሁለት ሰዎች መቱ ።

በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት ሁለት እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ ወድቀው ሕይወታቸው ማለፋ ተነግሯል

በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል።

በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።

የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል።

እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ አክለውም፤ ሪል እስቴቱ በሠራተኞች ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

20/06/2025
ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ለ10ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን  ኮ...
20/06/2025

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ለ10ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ኮንፈረንስ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ኮንፈረንሱን አስመልክተው የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር ) እንደተናገሩት የአፍሪካ የመንግስት አገልግሎት ኮንፈረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን አገራት ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት በሚኖራቸው ዝግጁነት ደረጃ እየተወዳደሩ የሚያዘጋጁት በመሆኑ ኢትዮጵያም በ9ኛ ዙር በዚምባብዌ በተካሄደው ኮንፈረንስ ተወዳድራ የወሰደችው ተራ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካ የመንግስት አገልግሎት ኮንፈረንስ አንዱ ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ነው ሁለተኛው በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ቀጠናዊ ፎረም በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ኢኖቬሽን በሚል የሚካሄድ ፎረም ነው፡፡

የመንግስት ተቋማት ተለዋዋጭ ከባቢያዊ ሁኔታዎች እንዲቋቋሙና ተንከባለው የመጡ ለብዙ ጊዜ የተከማቹና ከአገልግሎት ጋር የተያያዙ ፈተናዎች በፍጥነት ስለመቅረፍ ትኩረት የሚያደርግ ኮንፈረንስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዋናው የኮንፈረንሱ ዓላማ በአፍሪካ የተከማቹ የአገልግሎት አቅርቦት ችግሮች በመፍታት አካታች ፣ ዘላቂ ልማት የሚያመጣ ፣ ተጠያቂነት የሚያሰፍን ፣ የሰብዓዊ መብት የሚያከብር፣ የህዝቦች ትስስር የሚያጠናክር ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር የጠንካራ ተቋም አስፈላጊነት ወሳኝ መሆኑ ላይ መወያየትና መግባባት፤
እንዲሁም አፍሪካ የተከማቹ ችግሮቿን ለመፍታትና የመጪውን ጊዜ ያለመ ተልዕኮ ለመፈጸም ጠንካራ የሰው ኃብትና የመንግስት አስተዳደር የሚያስፈልጋት በመሆኑ በዚህ እና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመረጃ ተደራሽነትና ተጠያቂነት ማስፈን አስፈላጊ በመሆኑ ላይ መወያየትና ተሞክሮ መቀያየር የጋራ መግባባት በመፍጠር ወደ የተግባር ዕቅድ መቀየር የሚያሰችሉ ሥራዎች በተመለከተ መግባባት ላይ መድረስ የሚያስችል ኮንፈረንስ እንደሚካሄድ አክለው ገልፀዋል፡፡

ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር የባለሚናዎችና የህዝባዊ አደረጃጀት ተሳትፎዎች ማጠናከር ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን ለመገንዘብ ፣የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ችግሮቻቸውን በመፍታት ያካበቱትን መልካም ልምድ መቀያየርና መማማር እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ እና፣
ፈጠራ በታከለበት አግባብ ሰው - ተኮር አገልግሎት ስለሚቀርብበት ሁኔታ ለመነጋገር፣ የአፍሪካ አገራት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያቀርቡ የሚያስችል አቅም የሚገነባበት ስትራቴጂ ለመንደፍ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዬች በኮፍረሱ እንደሚካሄዱ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡

አክለውም ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩ ከሰራተኛ ቅነሳ ጋር የተያያዙ ሀሰተኛ መረጃዎች እንደሆኑ ገልፀው በዚህ አሁን መንግስት በጀመረው ሪፎርም የመንግስት ሰራተኛውን የማብቃት ፣የማዘመን አገር የመለወጥ አጀንዳ እንጂ የመንግስት ሰራተኛውን የሚያፈናቅል አንድም አዋጅ፣ ፖሊሲም ሆነ ፍኖተ ካርታ በየትኛውም ገፅ ላይ እንዳልተፀፈ ይህንንም ማንም ሰው ማየት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ሰራተኛው ከእንዲህ ካለ አሉባልታ ራሱን ቆጥቦ የተጀመረው ሪፎርም እንዲሰካ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በተለይ የመንግስት ሰራተኛው ላይ ያለው ጫና በበቂ ሁኔታ ችግሩን እንደሚረዱት ገልፀው ይህን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ከሪፎርሙ ጋር በተያያዘ አጀንዳ አድርጎ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኮፈረንሱ ከሰኔ 14 እስከ 16 ቀን 2017 ዓ.ም.

Address

Yeka32467
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማዕድ maed ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share