Arts Tv World

  • Home
  • Arts Tv World

Arts Tv World Arts Tv World - Digital Media and Satellite Television Service
(2)

41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር  በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና ሀዋሳ ዛሬ ተከናውኗል ።በወንዶች ማራቶን ውድድር ገመቹ ያደሳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ...
06/07/2025

41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና ሀዋሳ ዛሬ ተከናውኗል ።

በወንዶች ማራቶን ውድድር ገመቹ ያደሳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ ጋዲሳ አጀበ እና አሰፋ ተፈሪ ከመቻል እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል ።

በሴቶች ዘርፍ በተደረገው የማራቶን ውድድር መሠረት ገብሬ ከኦሮሚያ ክልል በአንደኝነት ስታጠናቀቅ አሹማር ዘመናይ እና አዝመሬ በየነ ከመቻል ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመውጣት የሜዳልያ እና የገንዘብ ተሸላሚ መሆን ችለዋል ።

ውድድሩ በታላቅ ድምቀት ብዙ እንግዶች በተገኙበት ሲጠናቀቅ ለሀገር ተስፋ የሚጣልባቸው ተተኪ አትሌቶች እንደታዩበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል ።

ዮናሰ ግርማ ከሀዋሳ

አሪፍ ቡና በልዩ ቅናሽ !!
05/07/2025

አሪፍ ቡና በልዩ ቅናሽ !!

የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራማችን ሶስት የተመረጡ ኮፊ ሃውሶች በመገኘት የአሪፍ ፔይ ኪዋር ኮድን ስካን ላደረጉ የተያዩ ደንበኞችን በአሪፍ ቅናሽ ቡና በነፃ ጋ...

"ሁሉ ስፖርት" BYD SEGUAL መኪና ሸለመ። የዘንድሮውን ክረምት ምክንያት በማድረግም ለስፖርቱ መነቃቃት ያግዛል ያለውን የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ን እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ...
05/07/2025

"ሁሉ ስፖርት" BYD SEGUAL መኪና ሸለመ።

የዘንድሮውን ክረምት ምክንያት በማድረግም ለስፖርቱ መነቃቃት ያግዛል ያለውን የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ን እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡን አስታውቋል፤ ይህ የክረምት የስፖርት ፕሮጀክት በተለያዩ ክልል ከተሞች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚከናወን ስለመሆኑም የሁለገብ ሶፍትዌር ሶሉሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክብሮም ገብረመስቀል ገልፀዋል።

ድርጅቱ አገልግሎቱን በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የማስፋፋት እቅድ ስለመያዙም አቶ ክብሮም ጠቁመዋል።

ከዚህም መካከል
አዎንታዊ ማህበራዊ ተፅዕኖን ለሚፈጥሩ የሀገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዓመታዊ ልገሳ እንደሚደረግ፤

የስፖርት ማልያና ቁሳቁስ ማቅረብ የወጣቶችን ልማት እንደሚደግፍ፤
የመንግስት ሀላፊዎች፣ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ሚድያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ የሆነው አዲስ ዌብሳይትም ይፋ ተደርጓል።

ሁለገብ online solution ከስምንት አመት በፊት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራ መተግበሪያን በመፍጠር ብቸኛ መሆን የቻለ ነው።

የብሩህ ማይንድስ 5ኛው ዓመታዊ ልዩ ምልከታ አውደ ርዕይ የመዝጊያ ፕሮግራም በተፈሪ መኮንን ኮሌጅ ተከናወነ።ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ...
05/07/2025

የብሩህ ማይንድስ 5ኛው ዓመታዊ ልዩ ምልከታ አውደ ርዕይ የመዝጊያ ፕሮግራም በተፈሪ መኮንን ኮሌጅ ተከናወነ።

ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘው አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

መድረኩ የወጣቶችን የፋይናንስ ተደራሽነት በማስፋት ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት የሚያስችል አገልግሎት እንዲኖር ፤ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ መላ ሥራዎቻቸውን ለማበልፀግ እንዲችሉ የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሏል።

ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ጥናትና ምርምር፣ ሥልጠናዎችንና የንግድ ልማት አገልግሎት የሚያከናውን የአማካሪዎች ተቋም ነው።

ተቋሙ የሥራ ፈጠራና ወጣቶች ልማት ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ብዙ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከነዚህ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሥራ ዕድልና የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ባለ ድርሻ አካላት በቅርበት በመወያየት የተሻለ ከባቢ እንዲፈጠር “ልዩ ምልከታ” የተባለ መድረክ አዘጋጅቶ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያከናውን መቆየቱን ለአብነት ጠቅሷል።

“ልዩ ምልከታ” በተለያያ የትምህርት መስክ የሰለጠኑ ምሁራንና ባለሞያዎችን አንድ ላይ በማምጣት የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚያካሂድ ሲሆን፣ ቁልፍ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች፣ የክልል መንግስታት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ፣ የምርምርና አካዳሚክ ተቋማት፣ የወጣቶችና የሴቶች ቡድኖች ከፕሮግራሙ ተሳታፊዎች መካከል ይገኙበታል።

በቃልኪዳን ይጥና

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለትከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ...
05/07/2025

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለት

ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ይኸ በሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ በአማርኛ "የኃይሌ ኃይሎች"በእንግሊዝኛ "Dissecting Haile" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቶታል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያዊውን የረጅም ርቀት አትሌት እና ስራ ፈጣሪ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእረኝነት ዘመኑ አንስቶ ያለውን ድንቅ ሕይወት፣መርሆች እና ዘላቂ ትሩፋት የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር ከኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ደራሲዋ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግራለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ኃይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጻለች።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለማሰናዳት አንድ ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።

መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም "Dissecting Haile" መጽሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በይፋ ለአንባቢያን የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ማስጀመሪያ ዝግጅት፣ በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በአማዞን፣ በቴሌብር፣ በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና እንዲሁም መጽሐፍት መሸጫ መደብሮች መፅሀፉ በኤሌክትሮኒክ አማራጮችና በሀርድ ኮፒ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በትዕዛዝ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ናትናኤል ደበና

አርትስ ቴሌቭዥን እና ኖቫ ኮኔክሽንስ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እንደዚሁም የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአብሮነት ለማዘጋጀት ስምምነት ተፈራረሙ። አርትስ ቴሌቭዥንን በመወከ...
04/07/2025

አርትስ ቴሌቭዥን እና ኖቫ ኮኔክሽንስ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እንደዚሁም የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአብሮነት ለማዘጋጀት ስምምነት ተፈራረሙ።

አርትስ ቴሌቭዥንን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የአርትስ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ራፋቶኤል ወርቁ እንደተናገሩት አርትስ ቴሌቭዥን ኖቫ ኮኔክሽንስ የሚያዘጋጃቸው የነዚህ መርሃግብሮች አጋር የሆነው ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ዓለም ሁሉ አብሮ እየተገኘ የአፍሪካን ሕዳሴ ለማብሰር ከተነሳበት ዓላማ ጋር በእጅጉ ስለተቆራኘ ነው።

የኖቫ ኮኔክሽንስ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አብዛ በበኩላቸው ኖቫ ኮኔክሽንስ በሚያዘጋጃቸው መርሃ-ግብሮች ላይ አርትስ ቴሌቭዥን በተሻለ ዓላማው ከኛጋ የተጣጣመ አጋር ሆኖ መስራት የሚችል ተቋም በመሆኑ ነው ብለዋል።

ስምምነቱ አርትስ ቴሌቭዥን ከኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር በመተባበር በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአሜሪካ ዋሺንግተን ከተማ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እና የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድ እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የስምምነቱ መፈረም መርሃግብሮቹ በአርትስ ቴሌቭዥን በኩል በሰሜን አሜሪካ ለሚገኘው የዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

በቃልኪዳን ይጥና

የአርሰናሉ ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር ተከሰሰአማካዩ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ከአርሰናል በተለያየ በቀናት ልዩነት ውስጥ ነው።ቶማስ ፓርቴ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አን...
04/07/2025

የአርሰናሉ ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር ተከሰሰ

አማካዩ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ከአርሰናል በተለያየ በቀናት ልዩነት ውስጥ ነው።

ቶማስ ፓርቴ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል በመፈጸም ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል።

ተጫዋቹ የቀረበበት ክስ ሶስት የተለያዩ ሴቶች ሪፖርት ያደረጉት በ 2021 እና 2022 መካከል የተፈጠረ ክስተት መሆኑ ተነግሯል።

በቅርቡ ከአርሰናል ጋር የተለያየው ቶማስ ፓርቴ ከ 2022 ጀምሮ ምርመራ ላይ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ነሐሴ ወር ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል።

ገናዊው ተጫዋች ጥፍተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 25 ዓመት ድርስ በእስራት ሊቀጣ ይችላል ተብሏል።

በሷሊህ መሐመድ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arts Tv World posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Arts Tv World:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share