
13/09/2025
የፓስፖርት አገልግሎት የሚሰጥበት ሰዓት ተራዘመ
ገበያ ሚዲያ መስከረም 03/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት መስከረም 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የክልል ከተሞች በሚገኙ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እስከ ምሽት 4 ሰአት አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም በአዲስ አበባ ጎተራ እና ጥቁር አንበሳ ቢሮዎች ጨምሮ በሌሎች የክልል ከተሞች በሚገኙ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እስከ ምሽት 4 ሰአት የፓስፓርት አግልግሎት መስጠት መጀመሩን አገልግሎቱ ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ተቋሙ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እስከ ምሽት 4፡00 ድረስ እሁድ ደግሞ እስከ ማታ 12፡00 ሰአት አግልግሎት እንደሚሰጥ አክሏል።
በሌላ በኩል የፓስፓርት ፈላጊዎች በተቋሙ ትክክለኛ ድረ ገፆች ላይ የአስቸኳይ ፥ የእድሳት እና ሌሎች የፓስፓርት አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አመልክቷል።
የገበያ ሚዲያ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን
Telegram:https://t.me/gebeyanews
Youtube: https://youtube.com/
Facebook: https://web.facebook.com/gebeyapromotion
TikTok: https://www.tiktok.com/
Gebeya Media