Desalegn Daricho Gospel Singer

Desalegn Daricho Gospel Singer We Trust in God.God is good all time.

08/02/2026
08/02/2026

08/01/2026

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ኢትዮጵያን ጉብኝት ያደርጉ ዘንድ ግብዣ እና የጸሎት ጥሪ ቀረበ

| ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ባሳለፍነው ሰኔ ወር በቅድስት መንበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጋር ባደረጉት የካርዲናሎች ጉባኤ ለቅዱስነታቸው የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በየአመቱ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚደረገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞ የአፍሪካ ቀንድ ዋና ማዕከል ወደሆነችው ኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደቀረበላቸው በመግለጽ ምዕመናን ለዚህ ምኞት መሳካት እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የዘመናት የታሪክ ባለቤት የሆነች፣ የአማኞች ሀገር፣ የአፍሪካ ማዕከል እና በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027 ለሚዘጋጀው 32ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በአዘጋጅነት የተመረጠች ሀገር በመሆኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በቀጣይ ዓመት ለሚኖራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን ማካተት እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል።

ከሐምሌ 11-19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኬንያ ናይሮቢ በተካሔደው 21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤም ይህ ጥሪ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሌዎ 14ኛ መቅረቡ ተገልጿል።

ይህም ታላቅ እና የዘመናት የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ምኞት ምላሽ ይገኝ ዘንድ መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Desalegn Daricho Chanter

07/26/2026

Address

New York, NY
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Desalegn Daricho Gospel Singer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Desalegn Daricho Gospel Singer:

Shortcuts

Share