Addis Ababa Universty Comunity Radio FM 99.4

Addis Ababa Universty Comunity Radio FM 99.4 የሀገራችን አንጋፋውና ቀዳሚው የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ድምፅ
Morning 12:30- 8:00 local time, tune your radio! FM 99.4

20/09/2025
አንጋፋው እና ስመጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስዳችሁ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ መስፈር...
15/09/2025

አንጋፋው እና ስመጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስዳችሁ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ መስፈርት ላሟላችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።

ዩኒቨርሲቲያችን በ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 5 እስከ መስከረም 9፣ 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ፖርታል አማካኝነት መመዝገብ እንደምትችሉ በደስታ እንገልጻለን።

በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ቀን፣ ሰዓት እና ማዕከላትን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ መገናኛ ገፆች እንዲሁም በይፋዊ ድህረገጻችን የምናሳውቀው መሆኑን እንገልፃለን።

#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የተፅዕኖ ፈጣሪዎች ቤት

#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ : ህልሞን ያሳኩ

Website: https://www.aau.edu.et/

መስከረም 5, 2018
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

 #ልዩ የስኮላርሺፕ እድል ለመምህራን ትምህርት አንጋፋው እና ስመጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን የትምህርት ጥራት እና ተገቢነት ለማረጋገጥ የሚሰራውን ስራ ለመደገፍ...
13/09/2025

#ልዩ የስኮላርሺፕ እድል ለመምህራን ትምህርት

አንጋፋው እና ስመጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን የትምህርት ጥራት እና ተገቢነት ለማረጋገጥ የሚሰራውን ስራ ለመደገፍ እንደ ወትሮው ሀገራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተያየዘ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን ልዩ የስኮላርሽፕ እድል አዘጋጅቷል።

የስኮላርሺፑ ተጠቃሚ ሁሉንም መመዘኛ ያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና በብቃት ያለፉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የዚህ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች

- በተፈጥሮ እና ኮምፕዩቴሽናል ሳይንስ የትምህርት መስክ በፊዚክስ ፣ በኬምስትሪ ፣ በባዮሎጂ እና በሂሳብ እንዲሁም
- በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ፤ በእንግሊዘኛ ፣ በኢኮኖሚክስ ፣ በታሪክ፣ በጂኦግራፊ እና በሌሎችም የመምህርነት ትምህርት የሚከታተሉ ይሆናሉ።

የዚህ ስኮላርሽፕ ተጠቃሚዎች
- ሙሉ ነፃ የትምህርት እድል
- መጠነኛ የኪስ ገንዘብ
- ከአጋር ተቋማት ጋር በሚኖር ትብብር ተጨማሪ የስልጠና እድሎችን የሚያገኙ ይሆናል።

በመሆኑም የዚህ ልዩ እድል ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉና ከምርቃት በኋላ በመምህርነት ለማገልገል የምትሹ ሁሉ ከቅበላ በኋላ ዉል ፈርማችሁ ትምህርታችሁን መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የተፅዕኖ ፈጣሪዎች ቤት

# አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ : ህልሞን ያሳኩ

መስከረም 03፣2018 ዓም

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ በድጋሚ እንኳን ለ2018  ዓ.ም በሰላም  አደረሳችሁ የሚለው  አንጋፋው እና ስመ ጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በመጀመርያ ድግሪ በተለያ...
11/09/2025

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ በድጋሚ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ የሚለው አንጋፋው እና ስመ ጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በመጀመርያ ድግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለመቀላቀል ፍላጎት ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ አስቀድመን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን።

በመሆኑም በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ዩኒቨርሲቲው ላዘጋጀው የቅበላ ፈተና እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች በተመለከተ በሁሉም የዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም ድህረገጽ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፅዕኖ ፈጣሪዎች ቤት!!
#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ ህልሞን ያሳኩ

 #መልካም አዲስ ዓመት!  .4
11/09/2025

#መልካም አዲስ ዓመት!

.4

 #ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምሁራን በእውቀታቸው የተሟገቱለት የአብሮነት ማሳያ ትዕምርት ነው ፡፡ ዛሬ ላይ ለምረቃ የበቃው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከመነሻው...
09/09/2025

#ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምሁራን በእውቀታቸው የተሟገቱለት የአብሮነት ማሳያ ትዕምርት ነው ፡፡

ዛሬ ላይ ለምረቃ የበቃው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከመነሻው ጀምሮ ምሁራዊ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በአለም መድረክ የተሟገቱለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ህዝቦቿ መቀነታቸውን ፈተው ከዛሬ አሻግረው ለመጪው ትውልድ ብሩህ አሻራን ያሳረፉበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለምረቃ ምዕራፍ በቅቷል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የአይችሉም ትርክትን የቀለበሰ እርስ በእርስ በመደጋገፍና በአብሮነት ከህዝብ የራስ ሀብት የተገነባ የመቻል ትዕምርት ምሳሌ ነው ፡፡

የአባይ ወንዝ ለኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚነት እንዲውል ምሁራን በዓለም መድረክ በእውቀታቸው የተሟገቱበት የታላቅ ድል ስኬት ማብሰሪያ ነው፡፡

የአ.አ.ዩ ለአመታት በአባይ ግድብ ግንባታ ላይ ምሁራዊ አጀንዳዎችን እያፈለቀ ጥናትና ምርምሮችን እያበረከተ በጋራ ዘልቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽን እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ራሄል አርጋው ሀገሪቱ በጋራ ሀብቷ የገነባችው ዕውቀት እና ጉልበቷን የገበረችበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለዛሬዋ የምረቃ ዕለት መብቃቱ የሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች የመቻል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

መላ ኢትዮጵያውያን በላባቸው፣ በገንዘባቸው እና በጉልበታቸው ለገነቡት የኢትዩጵያ የህዳሴ ግድብ በዓል ምረቃ ዕለት በመብቃቱ ደስታቸውን የገለፁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒዮቲሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቢቂላ ወርቅነህ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ምሁራዊ አበርክቶ ፍሬያማነት ምሳሌ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የህዳሴ ግድቡ ከመነሻ ጥንስሱ አንስቶ የአካባቢና የማህበረሰብ ግምገማ ግኝቶችን በማካሄድ ሰፊ አበርክቶ እንደነበረው ይታወሳል፡፡ የዛሬው የድል ስኬትም የሁሉንም የእውቀት ትብብር ያሳየ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዋ በቂ የውሀ አቅርቦትና የኤሌክትሪክ ሀይል ያላገኘባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ብሩህ ተስፋን የፈነጠቀበት ነው፡፡ ይህን ተጠቃሚነት በማስጠበቅ ሂደት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ተጠቃሚነት መፃኢ እድልን ያማከለ ፍትሃዊ አሰራርን ኢትዮጵያ እንደምትከተል ዶ/ር ቢቂላ ይመሰክራሉ፡፡

ህዳሴ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እንቅፋት ሳይሆን በሰጥቶ መቀበል መርህ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የጋራ ተጠቃሚነት ማሳያ ነው፡፡

09/09/2025



 #ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሁሉን አቀፍና ሰላማዊ ማህበረሰብን ለመቅረጽ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ 15ተኛው የምስራቅ አፍሪካ የኮምዩኒኬሽን ማህበር ጉባኤ "ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ለአፍሪካ ትስስ...
27/08/2025

#ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሁሉን አቀፍና ሰላማዊ ማህበረሰብን ለመቅረጽ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

15ተኛው የምስራቅ አፍሪካ የኮምዩኒኬሽን ማህበር ጉባኤ "ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ለአፍሪካ ትስስር"በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡

ቀጠናዊ እና አህጉራዊ መግባባትና ውህደትን ለማጠናከር ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሚናቸው የጎላ ነው ሲሉ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ገልፀዋል፡፡

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስተሩ የጋራ ማንነትን በመገንባት እና የወደፊት እጣ ፈንታን ለማሳየትና የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ስራ አይተኬ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

አክለውም ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን የመረጃ ማሰራጫዎች ብቻ ሳይሆኑ እንደ መግባቢያ ድልድይነት በማገልገል ሁሉን አቀፍና ሰላማዊ ማህበረሰብን ለመቅረጽ ምሰሶዎችም ናቸው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው በፈጣን የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ውስጥ የተሳሳቱ መረጃዎች፤ ተግዳሮት በሆኑበት በዚህ ዘመን ኮምዩኒክሽን ይህንን ችግር በመቅረፍ የተባበረች እና የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ከሀያ በላይ ሀገራት በተሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ በአዲሱ የሚዲያ አውድ በተለይም በዲጂታል ሚዲያ እየተፈጠረ ያለውን ቀውስ በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍ የሚያስችሉ ምክረ ሀሳቦች የሚነሱበት እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ትምህርት ቤት ሃላፊ ዶ/ር አብዱላዚዝ ዲኖ ተናግረዋል፡፡

ከአፍሪካ ጋር የተያያዙ ጥናታዊ ፅሁፎች በሚቀርቡበት በዚህ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራትን ለማቀራረብና ለማስተሳሰር እንዲሁም አፍሪካዊ የሆኑ ትርክቶች በሚዲያው እንዲመረቱና እንዲሰራጩ የሚያስችሉ ግብዓት የሚሆኑ የጥናት ስራዎች የሚወጡበት እንደሆነም ሃላፊው አንስተዋል፡፡

ጉባኤውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የምስራቅ አፍሪካ የኮምዩኒኬሽን ማህበር በጋራ በመሆን አዘጋጅተውታል፡፡

16/08/2025
 #የቀድሞ አርበኞችን ታሪክ መሰነድ የነገውንም መንገድ ማበጀት  ነው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አብረው መስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ የስራ...
14/08/2025

#የቀድሞ አርበኞችን ታሪክ መሰነድ የነገውንም መንገድ ማበጀት ነው፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አብረው መስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ውል በተፈራረሙበት ወቅት ነው ይህ የተነገረው፡፡

ስምምነቱም በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ዘመን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ሀገር ያቀኑና ለነጻነት የተዋደቁ አርበኞች እውነተኛ ማንነታቸውን የሚገልጽ ኢንሳይክሎፒዲያ ወይም መድብለ እውቀት ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው፡፡

በአርበኞቻችን ደምና ልፋት የቆየ ማንነት፣ ፅሁፍ፣ ባህል እና የራሳችን የሆነ የቀንና የሰዓት አቆጣጠር ቢኖረንም የአርበኞቹ ተጋድሎ ባለመጠናቱና በተበጣጠሰ መልኩ መቀመጡ ላልተገባ ትርክት ስለዳረገን በተገቢው መጠናትና መሰነድ አለበት ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በፊርማ ስነ-ስርዓት መርሀ-ግብሩ ወቅት ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የዚህ ዘመን ትውልድ ዘመኑን የሚመጥን የአርበኝነት መንፈስ እንዲላበስና አቅጣጫውን ቀይሮ የመጣውን ወረራ የሚከላከልበት እና ኢትዮጵያና ኢትዮጲያዊነትን የሚያዘልቅበት እና የሚያቆይበት አቅም እንዲኖረው የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ ጥናት ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የተደበቁ አርበኞቻችንን ማንሳት ኢትዮጵያን ማንሳት ነው ያሉት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በበኩላቸው በሀገራችን አንጋፋ በሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ተመራማሪዎች ጥናቱ መካሄዱ በየጊዜውና በየቦታው የሚነሱ የውሸት ትርክቶችን ለማስቀረት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው ሲሉ አንስተዋል፡፡

ይህንኑ ጥናት በዋነኛነት የሚያካሂደው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ አድገህ የቀድሞ አርበኞቻችንን መዘከር ማለት የትላንት ታሪክችንን መዘከር ብቻ ሳይሆን የነገውንም መንገድ ማበጀት እንደሆነ ተናግረው፡፡

ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ የሚዘጋጀው ይኸው ኢንሳይክሎፒዲያ ወይም መድብለ እውቀት ወጣቱን ትውልድ በትክክለኛው መንገድ እንዲራመድ ከማስቻሉም ባሻገር ለሀገራችን ሰላምና እድገት ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተፈራርመዋል፡፡

 #የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር  እሸቱ ወንጨቆ አረፉ።ፕሮፌሰር እሸቱ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አ...
11/08/2025

#የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር እሸቱ ወንጨቆ አረፉ።

ፕሮፌሰር እሸቱ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀድሞ ፕሬዝዳንቱ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

የፕሮፌሰር እሸቱ ወንጨቆ የቀብር ስነ ስርዓት ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን ሲሆን ፤ በዕለቱ ከቀኑ 7-8:30 ሰዓት ባስተማሩበትና በሰሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ራስ መኰንን አዳራሽ የስንበት ስነ-ስርዓትም ይከናወናል።

በድጋሚ ለቤተሰባቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ከልብ እንመኛለን።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

 #የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሚያጠኑትን የትምህርት መስክ በመረጃ ላይ ተመርኩዘው ሊመርጡ ይገባል ተባለ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎችና ወላጆች ያዘጋጀው የዩኒቨርሲቲ...
11/08/2025

#የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሚያጠኑትን የትምህርት መስክ በመረጃ ላይ ተመርኩዘው ሊመርጡ ይገባል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎችና ወላጆች ያዘጋጀው የዩኒቨርሲቲ መረጃ ሳምንት በይፋ ተከፈተ ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ከፀደቀ በኋላ በ2017 ዓ.ም የት/ት ዘመን የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች በራሱ መስፈርት ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡

በመጪው የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም ለሚቀበላቸው አዲስ የቅድመና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ይረዳ ዘንድ የመረጃ ሳምንት አዘጋጅቷል፡፡

መድረኩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ከፍተውታል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል በወቅቱ ባድረጉት ንግግር ተማሪዎች ወደውና ፈቅደው ተቋሙን እንዲቀላቀሉና ውሳኔያቸው የተሟላ መረጃ ላይ እንዲወሰን የመረጃ ሳምንቱ አስተዋጾ ከፍ ያለ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተመራጭነቱን፣ አንጋፋነቱን እንዲሁም ተመራጭ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቀጥልና የተሻለ ተማሪን ለማግኘት የመረጃ ሳምንቱ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡

ይህ የመረጃ ሳምንት የተዘጋጀበት አላማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚቀበለው በውድድር በመሆኑ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ሙሉ መራጃ እንዲኖራቸው ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን የነገሩን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ናቸው፡፡

በዚህ የመረጃ ሳምንት ሁሉም ኮሌጆች ስለሚሠጧቸው አገልግሎቶች መረጃዎችን አጠናክረው ተገኝተዋል፡፡

ታዲያ ይህ መድረክ መዘጋጀቱ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተቋሙ ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው ሲል ጣቢያችን ካነጋገራቸው መካከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ኃላፊ ዶ/ር አደይ ፈለቀ እንደገለፁት ተቋሙን ለመቀላቀል የሚመጡ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ትክክለኛ መረጃ የማግኘት ችግር እንደነበረባቸው አስታውሰው ፤ ይህ መድረክ ትክክለኛ መረጃ ከማድረስ ባሻገር በምዝገባ ጊዜ የሚኖሩ እንግልቶችን ይቀንሳል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመጡ ተማሪዎች የሚያጠኑትን የት/ት መስክ በመረጃ ላይ የተመረኮዘ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል፡፡

ሌላው ጣቢያችን ያነጋገራቸው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ዶ/ር ሀብታሙ እንድሪስ ይህን አይነት መድረክ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲያዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አንስተው ተማሪዎች የሚፈልጉትን የት/ት ክፍል በተመለከተ የተሟላ መረጃ የሚሠጥና ተቋሙም የሚፈልገውን የተማሪ ቁጥርና ጥራት እንዲያገኝ እንደሚረዳው ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የት/ት ዘመን ባሉት 7 ኮሌጆች እና የህግ ት/ት ቤት ስር በሚገኙ 353 የድህረ ምረቃና 66 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

Address

Sidist Killo
Addis Ababa
1176

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Universty Comunity Radio FM 99.4 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Addis Ababa Universty Comunity Radio FM 99.4:

Share

Category