
16/06/2022
የ60 ሚሊዮን ብር መኪና ስጦታ ተበረከተላቸው‼
=================================
✍ በአሁኑ ወቅት በሃገረ ሳዑዲ የሚገኙት እውቁ ባለሃብትና ኢትዮጵያዊው ቢሊዬነር ሸይኽ ሙሐመድ ሑሴን አል-አሙዲ አዲስ ለተተኩት የመጅሊሱ አመራሮች እና ዑለማዎች ዘመናዊ መኪናዎችን በስጦታነት አበርክተዋል።
አል-አሙዲ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከሃገረ ጃፓን ያዛዟቸውን እያንዳንዳቸው ከ20, 000, 000 ብር በላይ የሚሆኑ ③ የ2022 ሞዴል NISSAN መኪኖች አዲስ ለተመረጡት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ለሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ለቀድሞ የመጅሊስ ዋና ፕሬዝዳንት ለ"ሐጂ" ዑመር ኢድሪስ እና ለቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ለዶ/ር ጄይላን ኸዽር በስጦታ አበርክተዋል። የቀድሞ የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ስጦታው ከተሰጣቸው ዋል አደር ብሏል።
ስጦታው የተበረከተላቸው የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በማስጠበቅ ለህዝበ ሙስሊሙ እየለፉ ያለውን ጥረት ለማበረታት መሆኑ ታውቋል።
ስጦታውንም የሚድሮክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማልን ጨምሮ በርካታ ኡስታዞች፣ የፌደራል መጅሊሱ የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በመጅሊሱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መኖሪያ ቤት በመገኘት አበርክተዋል።
ስጦታው ከተበረከተላቸው አካላት መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የመጅሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀይላን ኸድር በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲህ ማለታቸው ተነግሯል፦
«እኔ ለሙስሊሙ አንድነት ስል ያለምንም ቅሬታ ከቦታዬ እንደተነሳሁት ሁሉ፣ እንዲሁም የቀድሞ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ለሰላም ሲሉ ይህንኑ እንዳደረጉት ሁሉ፣ "ሐጂ" ዑመር ኢድሪስ የሙስሊሙን አንድነት ለማስጠበቅ ሲሉ ለአዲሱ አመራር ስልጣናቸውን በሰላም እንዲያስረክቡ ጥሪዬን አስተላልፋለሁኝ።»
[ዶ/ር ጀይላን ኸዽር ዛሬ በሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዚያራ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት]
ማሻ አላህ ብለናል። የተጣለባቸውን አማና በአግባቡ እንዲወጡ አደራ እንላለን። አላህ ይገዛቸው። የህዝብ ንብረት ከመዝረፍ ወይ ሠርቶ ወይ ተሰጥቶ ማግኘት ይበልጣል።
||
t.me/MuradTadesse
twitter.com/MuradTadesse