BBC Ethiopia

BBC Ethiopia we provide fact based information in Ethiopia

በአዋሽ አካባቢ በ11 ቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት 5:12 ደቂ አዳማ ፣ በደብረዘይት ፣ በአዲስ አበባ ፣ ጀሞ ፣ መካኒሳ ፣ አያት ፣ 22...
17/10/2024

በአዋሽ አካባቢ በ11 ቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት 5:12 ደቂ አዳማ ፣ በደብረዘይት ፣ በአዲስ አበባ ፣ ጀሞ ፣ መካኒሳ ፣ አያት ፣ 22 ፣ ሸጎሌ ... ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰምቷል፡፡

በአዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት፤ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከአዋሽ ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተው የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ላይ የተመዘገበ እንደነበር መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል። በዚሁ አካባቢ ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ብቻ ሰባት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን መረጃዎች ያሳያሉ።

ባለፈው እሁድ በተመሳሳይ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ ነበር። ከዚህ ክስተት አንድ ሳምንት አስቀድሞ መስከረም 26፤ 2017 ምሽት በዚያው ስፍራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 የደረሰ ነበር።

መስከረም 16፤ 2017 ለአርብ አጥቢያ ከሌሊቱ 6:36 አካባቢ በአዋሽ፣ ፈንታሌ እና ዶፈን አካባቢ ተመሳሳይ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል። በዚሁ ዕለት ከሁለት ሰዓታት ቆይታ በኋላ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.5 ገደማ የተመዘገበ እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዘርፉ ባለሙያዎች በወቅቱ መግለጻቸው አይዘነጋም።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ  እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት ታገደ  ababa | ዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን፣ አሰያየምን፣ እና አጠቃቀምን በተመ...
05/04/2024

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት ታገደ

ababa | ዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን፣ አሰያየምን፣ እና አጠቃቀምን በተመለከተ የተሟላ የአካሄድ መረጃ የሚሰጥ መመሪያ ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ተገለፆል ።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው ::

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የክብር ዶክትሬት ሽልማትን በተመለከተ ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ባቀረቡት ሰፊ የጥናት ፅሑፍ የክብር ዶ/ር ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም:: እንዲሁም ረ/ፕ ወይም ተ/ፕ የሚለውም ስያሜም ለመጠራያነት አይውልም በማለት ተናግረዋል::

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት ዲግሪን አሰጣጥ በተመለከተ መመርያ ማውጣት እንደሚገባው ፕ/ር ማስረሻ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብዙ የዶክትሬት ትምህርት ተማሪዎች ያሉ ቢሆንም ለትምህርቱ የሚያስፈልገው ግብዓት አለመሟላት እና በቂ ዝግጅት አለመኖር ተግዳሮት መሆኑን በማንሳት ይህን ያገናዘበ የትምህርት ፕሮግራም መዘጋጀት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ግልፅ የሆነ መመርያ እስኪያወጣ ድረስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዳይሰጥ በጊዝያዊነት መታገዱን ገልፀዋል፡፡

ንግድ ባንክን ምን አጋጠመው? ከትናንት ለሊት ጀምሮ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየደረሱኝ ነበር፣ መልዕክቶቹም "በርካታ ሰዎች፣ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከንግድ ባንክ ከኤቲኤም እና ከኦንላይን...
16/03/2024

ንግድ ባንክን ምን አጋጠመው?
ከትናንት ለሊት ጀምሮ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየደረሱኝ ነበር፣ መልዕክቶቹም "በርካታ ሰዎች፣ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከንግድ ባንክ ከኤቲኤም እና ከኦንላይን ትራንስፈር በነፃ ገንዘብ ወስደዋል ወይም ትራንስፈር አርገዋል" የሚል ነው።
አንድ ተማሪ እንደጠቆመኝ "እኛ ጋር ጓደኞቻችን ከ100 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሰሩ አሉ። 435ሺ ብር የሰራ ተማሪ አለ በዛች ቅፅበት ምክንያቱም ለሊት ላይ ንግድ ባንክ የፃፍክለትን ብር ያወጣ ነበር። ይህ የሆነው ለሊት ከ6 ሰአት እስከ 9 ሰአት አከባቢ ነበር።"
ሌላ ተማሪ ሲያስረዳ "ለምሳሌ እኔ ጋር 500 ብር ቢኖረኝ ዝም ብዬ ወደ አንተ 50,000 ብር ፅፌ በሞባይል ባንክ ብልክ ዝም ብሎ ይልክ ነበር" ብሏል። ወደ ኢ-ብር የላኩት ልጆች ግን አካውንታቸው ወዲያው እንደታገደባቸው ታውቋል።

አንድ መምህር ደግሞ "እኔ በምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ለሊቱን ሙሉ በዛ ያለ ገንዘብ በኤቲኤምና በትራንስፈር ገንዘብ ሲያስተላልፉ እንደነበር ሰምቻለሁ። ይህም ነገር በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንደነበር ስለሰማሁ ጥቆማ ልስጥህ በሚል ነው የጻፍኩልክ" ብለዋል።
ይህን ተከትሎ ባንኩ "በሲስተም ችግር ምክንያት" አገልግሎቶቹ ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል ብሏል።
የባንኩን የስራ ሀላፊዎች በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም፣ ባንኩ ግን ምን እንደተከሰተ ዝርዝር መረጃ ለህዝብ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Via Elias Meseret

15/03/2024

ሞቃዲሾ :-
ሶማሊያ ርዕሰ ከተማ ሞቃዲሾ ዉስጥ የሚገኝ አንድ ሆቴልን ትናንት የወረሩት ታጣቂዎች በሙሉ መገደላቸዉን የሐገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአ-ሸባብ አባላት ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ስየል የተባለዉን ሆቴል ወርረዉ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ተኩስ ገጥመዉ ነበር።አንድ የፖሊስ ቃል አቀባይ ዛሬ እንዳስታወቀዉ በተኩስ ልዉዉጡ 3 ሰዎች ተገድለዋል፤ ሌሎች 27 ሰዎች ቆስለዋል።ስየል ሆቴል በሶማሊያ ባለስልጣናት የሚዘወተር ሆቴል ነዉ።በተኩስ ልዉዉጡ የተገደሉና የቆሰሉት ሰዎች ማንነት ግን አልተገለጠም።የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያም ታጣቂዎቹ በሙሉ «ተደመሰሱ» ከማለት በስተቀር የሟቾቹን ብዛትና የደረሰዉን ጉዳት መጠን በዝርዝር አልዘገበም።አካራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡንድን አ-ሸባብ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ በሶማሊያ መንግስት ጦር፣ በተለያዩ ተቋማት፣ በባለሥልጣናት፣ በደጋፊዎቻቸዉና ሶማሊያ በሰፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ሠራዊት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳል።ሶማሊያ የሠፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ይዞታዉን ለሶማሊያ መንግስት ጦር እያስረከበ፣ ሐገሪቱን ለቅቆ እየወጣ ነዉ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወሰነዉ መሠረት የአፍሪቃ ሕብረት ጦር እስከመጪዉ ታሕሳስ ማብቂያ ድረስ ሙሉ በሙሉ ከሶማሊያ ለቅቆ ይወጣል።

🚨🏆 ዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ድልድል.ኤሲሚላን 🆚 ሮማሊቨርፑል 🆚 አትላንታኦሎምፒክ ማርሴ 🆚 ቤነፊካባየር ሊቨርኩሰን 🆚 ዌስትሀም
15/03/2024

🚨🏆 ዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ድልድል.
ኤሲሚላን 🆚 ሮማ
ሊቨርፑል 🆚 አትላንታ
ኦሎምፒክ ማርሴ 🆚 ቤነፊካ
ባየር ሊቨርኩሰን 🆚 ዌስትሀም

የስፓርት ዜና:-በአውሮፓ ቻንፒዮንስ ሊግ 8 የገቡ ቡድኖች ቀጣይ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል ::
15/03/2024

የስፓርት ዜና:-
በአውሮፓ ቻንፒዮንስ ሊግ 8 የገቡ ቡድኖች ቀጣይ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል ::

ጄፍ ቤዞስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሃብት ሆነ ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለፀጋነትን ተቀምቷል።በዚህ ሣምንት የወጣው የምድራችን ባለ ፀጋዎች ዝርዝር ኤሎን መስክን ወደ ሁለተኛ ባ...
05/03/2024

ጄፍ ቤዞስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሃብት ሆነ

ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለፀጋነትን ተቀምቷል።
በዚህ ሣምንት የወጣው የምድራችን ባለ ፀጋዎች ዝርዝር ኤሎን መስክን ወደ ሁለተኛ ባለፀግነት አውርዶታል።

የአማዞኑ ባለቤትና መስራች ጄፍ ቤዞስ አሁን ላይ የምድራችን ባለፀጋ የሚለውን ማዕረግ መቀዳጀቱ ተሰምቷል።

ብሉምበርግ በሚያወጣው የምድራችን ቢሊየነሮች ዝርዝር ማሳያ መሰረት ቤዞስ በ200 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ቀዳሚ ባለሃብት ሆኗል።

ኤሎን መስክ ደግሞ 198 ቢሊየን ዶላር ተከታዩን ደረጃ ይዟል።

መስክ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 31 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ማጣቱን ያነሳው ሪፖርቱ ለዚህ ደግሞ በኩባንያዎቹ የሚታየው የአክሲዮን ድርሻና የገበያ መዋዠቅ ዋናው ምክንያት ነው ብሏል።

በአንጻሩ ጄፍ ቤዞስ በተጠቀሰው ጊዜ 23 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ማግኘት መቻሉንም ዘገባው አስታውሷል።

ማንችስተር ሲቲ 3 : 1 ማንችስተር ዩናይትድ* የማንችስተር ደርቢ በሲቲ የበላይነት ተጠናቀቀ    ዛሬ በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሁለቱን የማንችስተር ደርቢዎችን ያገናኘ ሲሆ...
03/03/2024

ማንችስተር ሲቲ 3 : 1 ማንችስተር ዩናይትድ

* የማንችስተር ደርቢ በሲቲ የበላይነት ተጠናቀቀ

ዛሬ በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሁለቱን የማንችስተር ደርቢዎችን ያገናኘ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ 3:ለ1 አሸንፏል።

ማንችስተር ዩናይትድ መምራት የቻለበትን ጎል ራሽፎርድ ያስቆጠረ ቢሆንም ማንችስተር ሲቲ በፎደን ሁለት እንዲሁም በአርሊንግ ሀላንድ አንድ ጎል ሶስት ነጥባቸውን አሳክተዋል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 62 በማድረስ ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር እኩል ነጥብ ላይ ይገኛል።

በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች  ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ። የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ...
24/02/2024

በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ።

የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ ዐራት አባቶችን መግደሉን ይታወቃል፡፡

መረጃውን በስልክ ያደረሱን አንድ የገዳሙ የሥራ ኃላፊ በግፍ የተገደሉት አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት በረሀማው ጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተፈጽሟል ብለዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊ ለጊዜው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገዳሙ ጥበቃ እያደረገ ሲሆን ነገሮች እስኪረጋጉ ጥበቃው እንዲቀጥል ጠይቀዋል ሲል EOTC TV ዘግቧል።

24/02/2024

🇵🇱 ከፖላንድ 30 የህክምና ባለሙያዎች ነጻ ህክምና ገብተዋል

| የነጻ ህክምና ለመስጠት ከፖላንድ ለመጡ በጎ ፈቃደኛ 30 የህክምና ባለሙያዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደረገ።

ባለሙያዎቹ ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናት በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳና በጦር ኃይሎች ሆስፒታሎች እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ላይ የነጻ ህክምና የሚሰጡ ሲሆን፤ የአሁኑ ለሶስተኛ ጌዜ መሆኑን በተደረገው አቀባበል ላይ ተገልጿል።

ባለሙያዎቹ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና፣ የሰመመን ህክምና፣ የማህጸንና ጽንስ ህክምና እንዲሁም በሌሎች ህክምናዎች ላይ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቅድስት ልዑልሰገድና ሌሎች የማህበሩ የስራ ኃላፊዎች ከአውሮፓ ያህክምና ባለሙያዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማርፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Press
በልጅዓለም ፍቅሬ

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BBC Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share