BACO TUBE

BACO TUBE የሐዋርያት ሚዲያ - HAWARYAT MEDIA YouTube ገፅን🔴SUBSCRIBE🔴 ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/?si=W7ffhtFUAaqQDkCZ

11/09/2026

ምን ውስጥ እገባለሁ አትበሉ ❤ #ኦርቶዶክሳዊ #ስብከት #ኢትዮጵያ

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ፤ አሸጋገረን🙏በአዲሱ ዓመት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጎደለንን ትሙላልን፣ከክፉ ነገር ከልላ የልባችንን መልካም መሻት ትፈጽምልን🙏...
11/09/2026

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ፤ አሸጋገረን🙏

በአዲሱ ዓመት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጎደለንን ትሙላልን፣ከክፉ ነገር ከልላ የልባችንን መልካም መሻት ትፈጽምልን🙏

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢቱ ኢሳ 7፡14 "ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ብሎ የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝ 44÷9 "የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ የተናገረላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘችባት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕይ 12÷1 "ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት" ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ያስረዳናል፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ጠቢቡ ንጉስ ሰሎሞን በመኃልይ 4÷8 "ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡" ብሎ እንደተናገረ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት "ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያም ግን ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡ በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል።

ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ሰሎሞን እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን ስለእመቤታችን የተናገረውን ቃል መፈጸሙን ሲያመሰጠር "የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡" ይላል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ስለታላቅ መንፈሳዊ ተልዕኮ ሲባል ከሚያውቁት ቦታ መራቅን፣ ከለመዱት ቀዬ መሰደድን ከእመቤታችን የተረዱት ገዳማውያንም ዓለምን ንቀው ስሟን ስንቅ አድርገው ይመንናሉ።

05/09/2026

❤መረጋጋት❤ #ኦርቶዶክሳዊ #መዝሙር #ኢትዮጵያ #ስብከት

25/08/2026

ቀጥታ🔴 የቅዱስ ገብርኤል በዓል #ኦርቶዶክስ

24/08/2026

ካንቺ ጋር ነኝ ይለኛል❤ #ኦርቶዶክሳዊ #መዝሙር #እየሱስ #ማርያም ゚viralシ

14/08/2026

ስድቤን አርቀሽ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #መዝሙር

09/08/2026

አጥቷል ጎሎበታል❤

03/08/2026

ለዚ ያደረስከኝ እኔ ማነኝ❤ #ኦርቶዶክሳዊ #መዝሙር #ተዋሕዶ #አዲስ #እየሱስ

31/07/2026

❤
#ኦርቶዶክሳዊ #መዝሙር #ተዋህዶ

ድንግል ማርያም አማላጅ ናት። #ማርያም አማላጄ ናት። #እየሱስ #ኦርቶዶክሳዊ  ゚viralシ  ゚
30/07/2026

ድንግል ማርያም አማላጅ ናት።
#ማርያም አማላጄ ናት።
#እየሱስ
#ኦርቶዶክሳዊ

゚viralシ

゚

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BACO TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed media company?

Share