23/09/2026
የቦክስ ወግ
የእጅ እና የእግር ቦክስን ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ጨዋ ያልሆነ (ከሞያ የማይቆጠር)ጨዋታ ያደርጉታል። "ዝክረ ነገር" ላይ። ከሞያ የሚቆጠሩትን ጨዋታዎች የሚፈልግ ገጽ ከ866 _871 ይመልከት
አንድ ትውስታው የማያወላዳ የረጅም ዘመን ጨዋታ ትዝ ብሎኝ ነው። ያጫወተኝ ተሜ(ተመስገን ደሳለኝ) ይመስለኛል
የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጅ ናቸው አሉ(የትኛው ይሆኑ?)፣ ጎንደር ውስጥ ይንሸራሸራሉ። እንዲያ ወዲያ ሲማትሩ አንድ ወጠምሻ ወጣት ያያሉ
" አንተ ጎበዝ፣እንዲህ ተሽቀርቅረህ ወዴት እየሄድክ ነው?" ይጠይቃሉ
"ወዳዲሳባ" ይመልሳል
"ምነ?፣ ምን ተገኘ?"
"ከሙላው ጎንደር ትግል አሸንፌ አዲሳባ ልገጥም"
የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጅ አፈፍ አድርገውት
"እኔን ሳትገጥም ነው እንዴ ከሙላው ጎንደር የምትል?"
አፍታም አላቆዩት አንስተው አፈረጡት፣ ደገሙት፣ ሠለሱት..... አዲሳባው ቀርቶወደ ሆስፒታል
አለማየሁ ገላጋይ (ደራሲና ኃያሲ)