20/10/2025
እንዲያውቁት!
የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት አጭር የጥሪ ማዕከል 6622
ውድ የተቋማችን ተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት!
የመንግስት ግዥ አገልግሎት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት (e-GP) ሲስተምን በመጠቀም ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት የሚውሉ ሀገራዊ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ዕቃዎች እና የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በየዓመቱ በቢሊየን ብር በማዕከል ግዥ ይፈጽማል፡፡
በሌላ በኩል ተቋማት ውሳኔ ሰጥተው የሚልኳቸውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘት በተጨማሪ ያለጥቅም ተከማችተው የነበሩ ንብረቶች የያዙትን ቦታ በማስለቀቅ የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ እና ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
በመሆኑም አገልግሎቱ በሚያከናውናቸው ስራዎች እና በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ቅሬታ ለመቀበል የአገልግሎቱ አጭር የጥሪ ማዕከል የሆነው 6622 ከዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡