Kambo Media ካምቦ ሚዲያ

Kambo Media  ካምቦ ሚዲያ ሁለገብ መረጃዎች በማራኪ አቀራረብ፣ በፍጥነት እና በጥራት እናቀርባለን።

ብልፅግና 😂
09/03/2023

ብልፅግና 😂

21/02/2023

በስንዴ እጥረት ምክንያት የዱቄት ፋብሪካዎች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ

(Via Ethio FM)

የፓስታና መኮሮኒ አምራች ፋብሪካዎች የስንዴ ምርት እጥረት ገጥሞናል፤ በዚህም ስራ ለማቆም ተገደናል እያሉ እንደሚገኙ ኢትዮ ኤፍኤም ዛሬ ዘግቧል።

የዱቄትና የዱቄት ውጤቶች አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ስንዴ በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድ ሆኗል፤ ማንም እንደፈለገ መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም ብለዋል፡፡

መንግስት ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴን ለማግኘት ሲል ዩኒዮኖች ብቻ እንዲገዙ ፈቀደ፣ ለዱቄት አምራቾችም በዩኒዮኖች በኩል ታገኛላችሁ ተባሉ፣ በኋላም 12 ባለሃብቶች ተመርጠው ወደ ስራ ገቡ፣ ዱቄት አምራቾች ግን ስንዴ ሊያገኙ አልቻሉም ብለዋል፡፡

ይህ ችግር ከተፈጠረ 2 ወራትን አስቆጥሯል የሚሉት አቶ ሙሉነህ አምራቾች በእጃቸው ያለችውን ስንዴ እየቆጠቡ ሲጠቀሙ ቆይተው አሁን ላይ ስራ ማቆም ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በዳቦ ላይ የሚስተዋለው ጭማሬ እንዳለ ሆኖ የ1 ኪሎ መኮሮኒ ዋጋ ከ40 ብር ወደ 80 ብር ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

እንደ አቶ ሙሉነህ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ስንዴ እንደ ኮንትሮባንድ ተቆጥሮ በየኬላዎች በፍተሻ እየተያዘ ነው፡፡ በዚህም አምራቾች ገዝተው መተቀም አይችሉም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መጋዘን ላይ ስንዴ የተገኘባቸው ዱቄት ፋብሪካዎችም ሆነ ነጋዴዎች በህገ ወጥ መንገድ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ከሁሉም በፊት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ይቀድማልና ችግሩን ለመፍታት መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ አቶ ሙሉነህ ጠይቀዋል፡፡

ማታ ላይ ባልና ሚስት በከባዱ ተጣሉ። ባልየው በጣም በመናደዱ  ሚስቱን "በዚህ ሌሊት ወደ ውጭ አስወጥቼሽ የጅብ ራት አድርግሻለሁ" አላት። በዚህን ጊዜ በበሩ በኩል ሲያልፍ የነበረ ጅብ ይሄን...
16/02/2023

ማታ ላይ ባልና ሚስት በከባዱ ተጣሉ። ባልየው በጣም በመናደዱ ሚስቱን "በዚህ ሌሊት ወደ ውጭ አስወጥቼሽ የጅብ ራት አድርግሻለሁ" አላት። በዚህን ጊዜ በበሩ በኩል ሲያልፍ የነበረ ጅብ ይሄንን ሰማና ያላሰበውን ሲሳይ መጠባበቅ ጀመረ።

በመጨረሻም ባልና ሚስቱ ብዙ ተነጋገሩና ጭቅጭቃቸውን እየቀነሱ መጥተው እርቅ ፈጸሙ።

ጅቡ የባልና ሚስቱን እርቅ ሲሰማ ተናዶ በሩን አንኳኳና እንዲህ አላቸው "እናንተስ ታረቃችሁ ቅድም በበር በኩል የሰማሁት የእኔስ ነገር እንዴት ሆነ?"

ባሻዬ! የአንተን ጉዳይ እንዴት ብናደርግልህ ይላል?
Vi Tesfaye Hailemariam

መግለጫ ከቤተ ክህነት
15/02/2023

መግለጫ ከቤተ ክህነት

የሚያወዛግብ እና ግራ አጋቢ ብዙ ነገሮች አሉ...ነገር ግን እግዚአብሔር ከማመስገን ውጪ አማራጭ የለንም። ***ከ24 ሰዓት በፊት...የቀደመው ውግዝ ቡድን አዲስ ጳጳሳትን ስለመሾም እና ወደ ...
15/02/2023

የሚያወዛግብ እና ግራ አጋቢ ብዙ ነገሮች አሉ...ነገር ግን እግዚአብሔር ከማመስገን ውጪ አማራጭ የለንም።
***

ከ24 ሰዓት በፊት...የቀደመው ውግዝ ቡድን አዲስ ጳጳሳትን ስለመሾም እና ወደ ሌሎች ሀገረ ስብከቶች መስፋፋቱን እንደሚቀጥል ደረቱን ነፍቶ መግለጫ እየሰጠ ነበር ።
***
ከ24 ሰዓት በፊት....ይቅርታ የጠየቀን አንድ መኖክሴ ዳግም የሹፈት መግለጫ እንዲሰጥ አድርገው ቅድስት ቤተክርስትያን ላይ ሲዘባበቱ ነበር።
***
ከ24 ሰዓት በፊት ከቀን 08 በኃላ የፍርድ ቤት እግድ ሲነሳ ወደሌላው ሀገረስብከት ይህ ቡድን እንደሚንቀሳቀሱ ሲያወሩ ነበር።
***
ከ24 ሰዓት በፊት ሴት ጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶችን ነጠላ አልብሰው መግለጫ ሲያሰጡ ነበር ።
***

አሁን ግን ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ ከጴጥሮስ የመጸጸት ዕድሜ ባነሰ ርዝመት የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ ተባለ።

እኛም አሜን አልን ። እግዚአብሔርን አመሰግን።

ብዙ የሚያወዛግብ፣ግራ የሚያጋባ ነገር አለ። ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ብጽአን አባቶችን ከማመን ውጪ የልጅነት አማራጭ የለንም። ተፈጥሯዊ አቅም መንፈሳዊ መብቃቱም የለንም ።

ዕቅድ ሁለት የሚነድፍ አካልን እየተጠነቀቅን አሜን ከማለት ውጪ አማራጭ የለንም።

አባቶች ሲናገሩ .... ቢገባንም ባይገባንም ፍቃድ እግዚአብሔርን እያስቀደመን በጸሎት ትጋት አይናችንን ከጉልላቷ ላይ ከመትከል ውጪ ዕድል የለንም።

እግዚአብሔር የወደደውን ያድርግ!!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

ቱርካዊው ወጣት ህይወትን እና ጊዜያዊ ደስታን እውነታ ጠቅለል አድርጎ እንዲህ ገልጿል..!ከቀናት በፊት ቤት ያከራየኝ አንድ ሰው ኪራይ ከሚገባው በላይ ጨምሮብኝ መክፈል ስላልቻልኩ ጊዜም ሳይሰ...
12/02/2023

ቱርካዊው ወጣት ህይወትን እና ጊዜያዊ ደስታን እውነታ ጠቅለል አድርጎ እንዲህ ገልጿል..!

ከቀናት በፊት ቤት ያከራየኝ አንድ ሰው ኪራይ ከሚገባው በላይ ጨምሮብኝ መክፈል ስላልቻልኩ ጊዜም ሳይሰጠኝ ከቤቱ አባረረኝ ። ካባረረኝ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጡ ተከሰተ ።

ታዲያ ዛሬ በመጠለያ ድንኳን ውስጥ አብረን እሳት እየሞቅን ነው። ብዙ በባንክ ብድር የገዛቸው ንብረቶቹ ወድመውበታል ። በአደጋ ምክንያት የተበደረውን ማጣቱን ግንዛቤ ውስጥ ካልከተቱለትም ባለ ዕዳም ነው ። አሁን የፊቱን ገጽታ ሳየው ሳልሻለው አልቀርም በጣም ተኮራምቷል።

ዛሬ የኛ የሆነው ንብረት/ገንዘብ/ውበት/መልክ/ዝና/ስልጣን/....ነገ ልናጣው እንችላለን ። የሚመጣና የሚከሰት ነገር አይታወቅምና ራስ ወዳድ አንሁን ። ለምንናገረውና ለምንተገብረው ለምናደርገውም ጭምር ማስተዋልን እናክልበት።

"እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
12/02/2023

"እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ሰበር ዜና!!በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ  ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ  ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓት...
12/02/2023

ሰበር ዜና!!
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።

በይቅርታ ደብዳቤያቸውምሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ።

በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።
EOTC TV

ሰበር መረጃ ከቤተ ክህነት
10/02/2023

ሰበር መረጃ ከቤተ ክህነት

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::" የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያ...
10/02/2023

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::"
የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን
የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::

ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (President Pontifical Council for Prompting Christian Unity) እንደገለጹት "በተፈጠረው ችግር እና ሁኔታ ጥልቅ ሐዘን የተሰማን ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለንን አጋርነት በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረትን በሙሉ እንደግፋለን" ብለዋል::

በመልእክታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በላከው የመጀመሪያ መልእክት “አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥26 ያለውን ጠቅሰው ሕመሟ ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው ሲሉ በአጽንዖት ገልጸዋል።

በመጨረሻም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እናት በምልጃዋ እጅግ የተከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ታድርግልን ብለዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

Bishop Dawit Molalignእኔ ዳዊት ሞላልኝ እባላለሁ ስራዬ ወንጌል ሰባኪነት ነው:: እኔ የተገኝሁበት ቤተሰብ አባቴ የኦርቶዶክስ መነኩሴ ናቸው እናቴ ወደ እረፍቷ እስከሄደችበት ጊዜ ...
10/02/2023

Bishop Dawit Molalign
እኔ ዳዊት ሞላልኝ እባላለሁ ስራዬ ወንጌል ሰባኪነት ነው:: እኔ የተገኝሁበት ቤተሰብ አባቴ የኦርቶዶክስ መነኩሴ ናቸው እናቴ ወደ እረፍቷ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ ቤተክርስትያን ስትሄድም ሆነ ስርአቶችን ስትፈፅም አይቼ አላውቅም ነበር ታማ በነበረችበት ሰዓት ጌታን ተቀብላ አባቷ ከአይሁድ ወገን እንደሆነ ነግራን ነው ያረፈችው። አራቱ ወንድሞቼም ሶስት ታናናሽ እህቶቼ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ናቸው እኔን ጨምሮ አምስት ወንድሞቼ የወንጌል አማኞች (ጴንጤ) ነን ::

በልጅነት እኛ ቤት አባታችን ከወደ ራያ ወሎ ስለነበሩ ደስ የሚል ነፃነት ነበረ በቤታችን :: በክብር ዳንቴል ለብሳ በምትውለው ናሽናል ቴፕ የኦቶዶክስ መዝሙር ይከፈት ነበር የሚገራርሙ ቅኔና ምክር የሞላባቸው አማርኛ መንዙማዎች ይከፈቱ ነበር የጴንጤ መዝሙርም የተስፋዬ ጋቢሶና የታምራት ሃይሌ ካሴት ይከፈት ነበር ታዲያ ተመልከቱ አሁን በሃገራችን በሚፈጠሩ ማናቸውም አይነት ችግሮች አያገባኝም አይነካኝም ማለት አይቻልም::

ስለዚህ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በተፈጠረው ነገር እንደ አንድ የወንጌል አማኞች አገልጋይ ሰላማቸው እንዲመለስ የሰው ህይወት እንዳያልፍ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እፇማለው እፀልያለው::

Address

Addis Ababa

Telephone

+251900312123

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kambo Media ካምቦ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share