መፅሔተ ጥበብ - Metshete Tibeb FM 97.1

መፅሔተ ጥበብ - Metshete Tibeb FM 97.1 ዘወትር ቅዳሜ ከ11 እስከ 2 FM 97.1

ሽምግልና ፣ የፍቅር ቃል ፣ አውደ ምስጋና ከአንጋፋው አርቲስት አለልኝ መኳንንት ፅጌ፣ደሳለኝ መኩሪያ ፣ አሚ ደጀኔ፣ በሃይሉ ድንበሩ ጋር በአለም ዙሪያ በናይል ሳት በሚደመጠው 24 ሰአት በሚያዝናናው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

02/04/2025

የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም ። መቼ ይሆን የምንነቃው?

ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው? ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው?

ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ። ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አይደለም። ኃጢአት ሕመም ነው። ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

02/04/2025

*☞ #ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?*
የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ
ያሳልመናል ይላሉ።ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮእሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛውካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡርደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም
የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን
የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን
አሜን አሜን እንላለን።ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው..አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን
በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤
ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ
ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን
እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤
ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን
ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው።
ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤
ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ
እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ
ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ
የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ
መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን
ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን
እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ
በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ
ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል
ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12
ይሆናልና ነው
ወንጌል፦ የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ
ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን
አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን
ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን
ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል
በአራቱም አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን
የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ]
እና ፊሶን ናቸው።
ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ
ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው ወንጌሉም
እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ
ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች
ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!

❀ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❀
❀ወለወላዲቱ ድንግል❀
❀ወለመስቀሉ ክቡር❀

01/04/2025

+ አልቆም ያለ ደም+

"በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" ሉቃ. 8:44

ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።

ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም::

ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው:: በልብሱ ጫፍ ብቻ::

ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው:: የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው::

በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው? ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው:: የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን?

ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዐሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት::

መድኃኔዓለም እንዲህ ነው:: ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል ፤ በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል:: ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል:: እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ::

ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው?

ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ? እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው:: ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ::

ላቆመው ብል አልቆም አለኝ:: ያላሰርኩበት ጨርቅ ፣ ያልሞከርኩት ቅባት ፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም:: ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም:: እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው:: ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል::

ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው:: ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን:: ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ:: የእኔን ደሜን መግታት ላንተ ምንህ ነው? ደምህንስ አፍስሰህልኝ የለ?

እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር::
እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ::
በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ:: እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል:: እነጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 2015 ዓ.ም.

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

01/04/2025

“ጥበብ ይናፍቀኛል፥ ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ ያስቀናኛል፥ ድንቍርና ያስፈራኛል፥ ጦርነት ያስጠላኛል።”

ባንድ ወቅት ታላቁ ባለ ቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን እንዲህ ብሎ ነበር ።

01/04/2025

ድንቅ ታሪክ አሳዛኝና አስተማሪ አንብቡት

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።

01/04/2025

ተስፋ መቁረጥ ሲሰማህ ልብህን ወደ ፈጣሪህ አዙርና እንዲህ በል 👇
" አምላኬ ሆይ ችግር በረታብኝ። ፅናቱን ስጠኝ።

መከራን የምቋቋምበትን ብርታት ስጠኝ። እኔ አልችልም አንተ ግን ትችላለህ። እኔ ደካማ ነኝ አንተ ብርቱ ነህ።

በእኔ ሳይሆን ባንተ መንገድ ውሰደኝ!
ያንተ ፍጹምነት ከሰውነቴ ይበልጣል! የሁኔታዎች ሁሉ ባለቤት አንተ ነህ። በተዓምራቶችህ አልጠራጠርም! የጠፋውን ተካልኝ።

የተሰበረውን ጠግንልኝ። ተስፋዬን መልስልኝ። ተስፋዬን አለምልምልኝ።

አምላኬ ሆይ መከራን የምችልበት አቅም ስጠኝ። ነገዬ አብራልኝ። ነገ ብርሃን ከፊቴ እንዳለ በተስፋህ አግዘኝ።

አምላኬ ሆይ ከአጠገቤ አትራቅ።
ደካማህን ጠብቀኝ !

🙏 አሜን 🙏"
©️በጺቫ ነኝ የሊዮ ናፋቂ

01/04/2025

ህይወትን የምትሰጥ እናት ለሆስፒታል ለምን ትከፍላለች? ትራኦሬ‼️

በቡርኪኒፋሶ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታል ሴቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ ልጅ እንዲወልዱ ተወስኗል።

"እኔ የተወለድኩት ከሴት ልጅ ነው ሴት ልጅ ህይወትን ወደ እዚች ምድር ለማምጣት ብዙ ክፍያ ስትጠየቅ ማየት አልፈልግም ።
ድሃ እናቴ እኔን ለመውለድ በሚከፈል ክፍያ ምክንያት እኔን ልታጣ ነበር። ፈጣሪ ባይፈቅድ ኖሮ እኔም በህይወት የለሁም ነበር:: ዛሬ የዚህች አገር ፕሬዚዳንትም አልሆንም ነበር። ስለዚህ ህይወትን የምትሰጥ እናት ለሆስፒታል መክፈል የለባትም።"
የብርኪናፋሶ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ትራኦሬ
Via- አዩዘሀበሻ

መፅሔተ ጥበብ
28/03/2025

መፅሔተ ጥበብ

15/03/2025

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911719678

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መፅሔተ ጥበብ - Metshete Tibeb FM 97.1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category