Food & Drug Admin

Food & Drug Admin The official page of AAFDA, Addis Ketema Branch
የምግብና የመድኃኒት ምርቶች፣ የጤና አገልግሎት ተገቢነት፣ ደህንነት ፣ፈዋሽነት እና የጥራት ደረጃ ማረጋገጥና መቆጣጠር

11/09/2024

እንዲህም አለ
በስራ ቦታዬ በድንገት..,..
ያለኔ ፈቃድ የተቀረፀ ነው። ግን ይሁን ብለናል።

10/09/2024
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ65 ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች የበዓል መዋያ ስጦታ አበረከተ፡፡***********************ጳጉሜ 4-2016ዓምቅርንጫፍ ጽ/...
09/09/2024

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ65 ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች የበዓል መዋያ ስጦታ አበረከተ፡፡
***********************
ጳጉሜ 4-2016ዓም

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በወረዳ 12 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስረክቧል፡፡

በፕሮግራሙ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ ወ/ሮ አይዳ አወል የምናደርገው ስጦታ እህትማማችነትንና ወንድማማችነታችን ለማጠናከር በማሰብ መሆኑን ገለፀው አስተዳደሩ በማንኛውም ማህበራዊ ድጋፍ በማድረግ ከችግረኞች ጎን እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ እንጋ እርቀታ በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን ቀድሞ ከአባቶቻችን የወረስነውን የመረዳዳት፣ የመከባበርና የመቻቻልን እሴቶችን አስጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልፀው ባለ 5ሊትር ዘይትና 15 ኪሎ ዱቄት ለ65ቱም ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች መበርከቱን ገልፀዋል፡፡

የወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ተዘራሽ ገ/መድህን በበኩላቸው የመረዳደት ባህላችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን፤ ይህንን የተቀደሰ አላማ የተባበሩና ያገዙ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ https://www.facebook.com/share/p/Le9qJSoB8dUYQZDF/?mibextid=oFDknk

በአዲስ ዓመት ጳጉሜ ቀናቶች የተለያዩ የበዓል እና የገብያ ቦታዎችን በተለየ መልኩ ምልከታ አድርገን እየተቆጣጠርን እንገኛለን። ቅዳሜ እሁድን ጨምሮ ስራ ላይ ነን! የሚገጥማችሁ የምግብና መጠጥ...
07/09/2024

በአዲስ ዓመት ጳጉሜ ቀናቶች የተለያዩ የበዓል እና የገብያ ቦታዎችን በተለየ መልኩ ምልከታ አድርገን እየተቆጣጠርን እንገኛለን። ቅዳሜ እሁድን ጨምሮ ስራ ላይ ነን! የሚገጥማችሁ የምግብና መጠጥ ድህንነት ችግር ካለ ጥቆማና ድጋፋችሁ አይለየን። ቢሯችን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ እንገኛለን።

06/09/2024
Caution‼
22/06/2024

Caution‼

ህገወጥነት ውስብስብ እና በድብቅ የሚፈፀም መሆኑ ብቻ ሳይሆን በጥቅም ትስስር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ችግሩን መዋጋትና ማክሰም የሚቻለው በመንግስት ተቋማት ቅንጅት ብቻ መሆኑን ተገለፀ።  ዛሬ...
08/06/2024

ህገወጥነት ውስብስብ እና በድብቅ የሚፈፀም መሆኑ ብቻ ሳይሆን በጥቅም ትስስር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ችግሩን መዋጋትና ማክሰም የሚቻለው በመንግስት ተቋማት ቅንጅት ብቻ መሆኑን ተገለፀ።
ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 01/2016ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
#በህገወጥ የመድኃኒት ፣የምግብና መጠጥ ምርቶች እንዲሁም በትምባሆ ምርቶች ዙሪያ በክፍለ ከተማችን ከሚገኙ ከጸጥታ ዘርፍ አመራሮች እና ከፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ መክፈቻ ላይም ፦
#አቶ እንጋ እርቀታ፦የቅ/ጽ/ቤታችን ስራ አስኪያጅ፤ ለታዳሚዎች የውይይቱን ዓላማ፣ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያካሄደውን ሪፎርም፣አዲሱን ሎጎ፣ቅ/ጽ/ቤቱ በህገወጥ የመድኃኒት ፣የምግብ፣መጠጥና ትምባሆ ምርቶች ላይ የተሰራ ስራዎችን ፣እነዚህን ህገወጥ ምርቶች በመቆጣጠሩ ሂደት የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና የፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ሚና እና በቅንጅት መስራት ያለውን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ዙሪያ ገለፃና ማብራሪያ በመስጠት የውይይት መድረኩን አስጀምረዋል።
በዉይይት መድረኩ ፦
#አቶ ልዑልሰገድ ወርቁ (የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)፦የውይይት ሰነዱን አቅርበዋል። የውይይት ሰነዱ ያካተታቸው አንኳር አንኳር ነጥቦችን ስንመለከት ፦
#ስለ ህገወጥ የምግብ ፣መጠጥ ፣መድኃኒት እና የትምባሆ ምርቶች ፀባይና ባህሪያት፣
#ህገወጥ የምግብ ፣መጠጥ ፣መድኃኒት እና የትምባሆ ምርቶች የሚመረቱበትና የዝውውር ሂደቱም ህጋዊ ያልሆነና የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ምንም ዓይነት ፈቃድ የሌላቸው ስለመሆኑ ፣
#ምንጫቸው አለመታወቁ ፣
#በአለም አቀፍ እንዲሁም በሀገራችንና በክፍለ ከተማችን ደረጃ እያስከተሉ ስላሉ ጉዳቶች/ቀውስ
#ተጠቃሚ ህብረተሰብ ላይ እያደረሱት ያለውን የጤና ችግሮች፣
#ህገወጥ ምርቶችን በምን ዓይነት መንገድ መቆጣጠር እንደሚቻል፣
#ህገወጥ ምርቶችን በመቆጣጠሩ ሂደት በክፍለ ከተማችን ያሉ ከጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ከፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ምን ይጠበቃል፤ በሚሉትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ የሰነዱ አቅራቢ ግልጽና በተብራራ መልኩ አቅርቧል።
#በውይይቱ የተሳተፉ የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና የፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች በቀረበው ሰነድ፣ በህገወጥ ምርቶች እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
#ከጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ከፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ማብራሪያ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ እንጋ እርቀታ በነዚህ ህገወጥ በተባሉ ምርቶች ዝውውር ፣የስርጭት ሂደቱን ፣በህብረተሰቡ ላይ እያደረሱ ያሉትን የጤና ችግሮችና የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት እነዚህን ህገወጥ ምርቶችን በመቆጣጠሩ ረገድ የሰራቸውን ስራዎች፣ እያጋጠሙት ስላሉት ተግዳሮቶች/ፈተናዎችና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ስጥተዋል። ህገወጥነት ውስብስብ እና በድብቅ የሚፈፀም መሆኑ ብቻ ሳይሆን በጥቅም ትስስር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ችግሩን መዋጋትና ማክሰም የሚቻለው በመንግስት ተቋማት ቅንጅት ብቻ ነውና በዚህ ረገድ መበርታት ይጠበቅብናል ብለዋል።
#በመጨረሻም ያስተላለፉት መልዕክት በክፍለ ከተማችን ደረጃ የህገወጥ ምርቶችን ዝውውርና ግብይት ሂደቱን ማስቆም እና መቀነስ የሚቻለው ቅ/ጽ/ቤቱ ከጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ከፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ጋር በተሰናሰለና በተቀናጀ መልኩ ከሰራ እንደሆነ በመግለጽ ውይይቱ በዚህ መልኩ ተጠናቋል።
ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም

ዛሬ በቀን 30/09/16 ዓ.ም አጠቃላይ የ2016 ዓ.ም የጤና ተቋማት እና የመድኃኒት ተቋማት ውይይት ተካሄደ።በአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድኃኒት የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዓመቱ የጤ...
07/06/2024

ዛሬ በቀን 30/09/16 ዓ.ም አጠቃላይ የ2016 ዓ.ም የጤና ተቋማት እና የመድኃኒት ተቋማት ውይይት ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድኃኒት የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዓመቱ የጤና ተቋማት የቁጥጥር ስራዎች መጠናቃቸውን ተከትሎ ከተቋማቱ ጋር የውይይት መድረክ አድርጓል በዚህም በዋናነት አጠቃላይ በተሰሩ የቁጥጥር ስረዎች፣በተገኙ ግኝቶች ላይ እና በተወሰዱ እርምጃዎች ላይ እንደዚሁም በቀጣይ በሚኖሩ አሰራሮች ላይ እና የ2016 ዓ.ም ሪፓርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል በመድረኩ የተገኙ የተቋማት ባለቤቶች እና የጤና ባለሞያዎች ሀሣብ እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ስለ ተቋማት እስታንዳርድ ፣የተለያዩ ስልጠናዎች ሰለሚያገኙበት ሁኔታ፣ስለ መድኃኒት ማዘዣ ወረቀት እንዲሁም በቁጥጥሩ ስለመጣ ለውጥና ሌሎች ሰፊ ሀሳቦችን አንስተዋል በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ከመድረክ በሁለቱም ዳይሬክተሮች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንጋ እርቀታ አማካኝነት ደግሞ ተጨማሪ ምላሽ እና ማብራሪያ እንዲሁም የቀጣይ የአሰራር አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ዉይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል።

04/06/2024

በደረቅ ቆሻሻ ክሬሸር ሲወገድ

ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ የጥራት እና የንፅህና ጉድለት ያለበት "በርበሬ" እንዲወገድ ተደርጓል።"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""...
04/06/2024

ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ የጥራት እና የንፅህና ጉድለት ያለበት "በርበሬ" እንዲወገድ ተደርጓል።
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት
ከከተማ አስተዳደሩ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት #በቀን 24/08/2016ዓ.ም በክፍለ ከተማችን በሚገኙ በሶስት(3) የተለያዪ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ላይ ድንገተኛ የቁጥጥር ስራ(Operation) መካሄዱ ይታወቃል።
#በዚህ ድንገተኛ ቁጥጥር ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል አንዱ የበርበሬ ወፍጮ ቤት ነው። በቁጥጥሩ ወቅት በተቋሙ ከሚገኙ የበርበሬ ምርቶች አራት (4) የበርበሬ ናሙና ምርት መወሰዱንና ተቋሙም መታሸጉ ይታወቃል።
#የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተወሰዱትን የበርበሬ ናሙና ምርት የምርምራ ውጤት(Test Result) በደብዳቤ አሳውቆናል። የተወሰዱት የበርበሬ ናሙና ምርቶች በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለምርቱ በተቀመጠለት አስገዳጅ በሚባሉት 2 የምርመራ መለኪያ (Test Parameter) እንዲመረመሩ ተደርገው በአንዱ መለኪያ የተወሰዱት ሁሉም ናሙናዎች ውድቅ ሆነዋል። በመሆኑም ለምግብነት መዋል የሌለበት ምርት አለመሆኑ በምረጋገጡ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ተደርጓል።
#በዚህም መሰረት ዛሬ በቀን 27/09/2016ዓ.ም የታሸገውን ተቋም በመክፈት በተቋሙ የሚገኙትን ምርቶች የቅ/ጽ/ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የተቋሙ ባለቤት በተገኙበት እንዲወገዱ ተደርገዋል።
የተወገዱ የበርበሬ ምርቶችም ፦
1. 6 ማዳበሪያ በኪሎ ግራም (223ኪ.ግ) የተፈጨ የበርበሬ ምርት እና
2. 5 ማዳበሪያ በኪሎ ግራም (122 ኪ.ግ) በተቋሙ የሚገኝ የተበላሸ የዛላ በርበሬ ምርቶች አጠቃላይ በድምሩ 345 ኪሎ ግራም የበርበሬ ምርቶችን በደረቅ ቆሻሻ ማጓጓዣ መኪና(ክሬሸር) አማካኝነት ተወግዷል።
#የተወገዱትን የተፈጩና የዛላ በርበሬ ምርቶች ዋጋ በገንዘብ ሲተመን 125,800.00ብር ነው። ምርቱን ከማስወገድም በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ አስፈላጊ ሂደቶችን በማስከተል ተጠያቂነቱ የሚቀጥል ይሆናል።

አገር ተረካቢው ትውልድ ከትምባሆ መዘዝ ለመታደግ በተማሪዎች ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ተገለፀ። """""""""""""""" ”"""""""''' """"""""""""""""""""በአዲስ አበባ ከ...
31/05/2024

አገር ተረካቢው ትውልድ ከትምባሆ መዘዝ ለመታደግ በተማሪዎች ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ተገለፀ።
"""""""""""""""" ”"""""""''' """"""""""""""""""""
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት

#በዓለም ለ37ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ የጸረ ትምባሆ ቀን
"Protecting Children from To***co Industry Interference"
"ህፃናትን ከትምባሆ ኢንዱስትሪ ጣልቃ ገብነት እንከላከል" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በቀን 23/09/2016ዓ.ም በአዲስ ከተማ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት አጋፋሪነት/አማካኝነት በክ/ከተማው ስር በሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በደመቀና ባማረ መልኩ ስለ ትምባሆ ገዳይነትና የነገ ሀገር ተረካቢ አፍላ ወጣት ትውልድን እያሳጣን እንደሆነ በሰፊው ለተማሪዎችና ለመምህራን ግንዛቤ ሲሰጥና ሲከበር ውሏል።
#ዛሬ በክ/ከተማችን የፀረ ትምባሆ ቀን በተከበረባቸው በሁሉም የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችየተሰሩ የንቅናቄ ስራዎችን ስንመለከት፦
#ለትምህርት ቤቶች በትምባሆ ዙሪያ የተዘጋጀውን አጭር ፅሁፍ አቅርበንላችኋል።
#የዘንድሮውን መሪ ቃልና የትምባሆ ንቅናቄውን ዓላማ፣
#የትምባሆን አስከፊነትና ገዳይነት፣እንዲሁም ሰፊውን የወጣቱ/አዲሱ ትውልድ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት/ሞት፣
#የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ጥቁር 1112/2011፣
#ኢትዮጵያ የትምባሆን ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በ2006ዓ.ም ተቀብላ ስላፀደቀችው የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽን 822/2006(Framework Convention on To***co Control)፣
#የትምባሆ ምርት ማጨስና መጠቀም ስለሚከለከልባቸው ቦታዎች፣
#በትምባሆ ዙሪያ በተዘጋጁ ጥያቄዎች በተማሪዎቹ መካከል የጥያቄና መልስ ውድድሮች ተካሂደዋል።
#በጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ ለተሳተፉ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ዛሬ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በተከበረው የፀረ ትምባሆ ቀን ላይ የተገኙት የቅ/ጽ/ቤታችን ስራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ፦ ትምባሆ፡ በሰዎች ጤና፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ስነ -አእምሮ እንዲሁም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ እያስከተለ ያለውን ችግር ፤በተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለተማሪዎችና ለት/ቤቶቹ ማህበረሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
# # # #በመጨረሻም
*ዘንድሮ ከሚያዝያ 1/2016ዓ.ም እስከ ግንቦት 23/2016ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ከተማ አቀፍ ንቅናቄውን የአዲስ ከተማ ምግብና መድኃኒት ቅ/ጽ/ቤታችን የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ስንመለከት ፦
1.የቅ/ጽ/ቤቱ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ባለሙያዎች፣ቡድን መሪና ዳይሬክተሩ፣
2.የክላስተር ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፦
3.የአዲስ ከተማ ክ/ከ ትምህርት ጽ/ቤት፣የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት፣ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ፖሊስ፣ እና ሌሎችም ጽ/ቤቶች፣
4.የአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ናቸው። ለነዚህ አካላት ቅ/ጽ/ቤቱ የከበረና የላቀ ምስጋና ያቀርብላቸዋል።

# # #"ህፃናትን ከትምባሆ ኢንዱስትሪ ጣልቃ ገብነት እንከላከል"

30/05/2024

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Food & Drug Admin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share