Holistic knowledge for transformer generation

Holistic knowledge for transformer generation The page is not created for profit. It is a page created to provide accurate, unbiased information and news to the public.

09/07/2026

“እኛ የምንፈልገው በሌሎች ከተሞች ያለውን የኮሪደር ልማት መቐለ ማየት” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አስመራዎች ሰሞኑን... 💆‍♂️☕️**«ፈርኦን ከጉድ አውጣኝ!» ብሎ ወደ ግብጽ አማላክት መጸለይ ካልጀመሩ በስተቀር የሰሞኑ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ነገር ለአስመራ ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም**...
09/07/2026

አስመራዎች ሰሞኑን... 💆‍♂️☕️
**«ፈርኦን ከጉድ አውጣኝ!» ብሎ ወደ ግብጽ አማላክት መጸለይ ካልጀመሩ በስተቀር የሰሞኑ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ነገር ለአስመራ ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም**☠️
ታሪክ የሚያውቀው ነገር ቢኖር ጎረቤቶች ሲቃረኑ መሃል ላይ ገብቶ "ደህንነት" መሸጥ እና የአየር ክልል ማከራየት የለመደው ሀይል ፣ አዲስ አበባና ሞቃዲሾ እጅና ጓንት መሆን ሲጀምሩ ማርሽ ቀያሪ ያጣ ይመስላል።
የባህር በር ፍለጋውና የአንካራው ድርድር ካሰቡት በላይ ሰላማዊ እየሆነ ሲመጣ... የቀጠናው "ብቸኛ ወታደራዊ ኮከብ" የመሆን ድራማ ተመልካች እያጣ መድረኩ እየደበዘዘ ነው!!
ለመሆኑ ፎርሙላው ምን ነበር? 🤫😂
#የአፍሪካቀንድ

የባህር በር ለኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ ነው!
09/07/2026

የባህር በር ለኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ ነው!

🛑 ቀይ ባህር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ።

#የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:30 ሲሆን ብርጋዴር ጄነራል ተሾመ ተሰማ ምጽዋ ከተማ ላይ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችንና ማዕረግተኞችን ሰብስበው ንግግር አደረጉ።በንግግራቸውም እንዲህ አሉ፡-

‹‹......ሻዕብያ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ምጽዋን ለመያዝ ቆርጦ መነሳቱ ጥርጥር የለውም። እኔ የሚጠበቅብኝን አደራ ተወጥቻለሁ፡፡ ከጥር 30 ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን1982 ዓ.ም የሞት ሽረት ትግል አድርጌያለሁ። ከዚህ በኋላ የራሴን ህይወት በክብር ማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖች ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም።

ጀግንነት ማለት በሁሉም መልክ ለጠላት ምቹ ሁኖ አለመገኘት ነው። እኔ ዛሬ ብሞት ብሸነፍም በታሪክና በመጭው የኢትዮጵያ ትውልድ ፊት አልሸነፍም። የአጼ ቴዎድሮስን እድል በማግኘቴ በጣም እኮራለሁ።
#ጎበዝ ስሙኝ! ይህ የአደራ መልክቴ ነው። ነገ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይደርስ ይሆናል። ምን አልባት አምላክ ካለ ከእናንተ አንዱ መልዕክቴን ያደርስልኛል።ዛሬ ሻዕብያ ምጽዋን ይቆጣጠራል፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሀገሬ እና ህዝቧ ትልቅ አደጋ ነው፡፡ ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነውንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ጸንቶ የቆየውን የባህር በራችንን በመዝጋት በምድር ተወስነን እንድንቆይ ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነው።...... የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ የባህር በር አልባ ሁኖ በኢምፔሪያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነ የአጼ ዮሐንስ፣ የራስ አሉላ አባነጋና የእኔን ጨምሮ የአብዮታዊ ሰራዊት አባላት አጥንትና ደም በኢትዮጵያውያን ትውልድ ሁሉ እስከ ዘላለሙ ይፈርዳል።ጊዜውን ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ምጽዋን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የጸና ነው።
#እናንተ መኮንኖች ስሙኝ!

#አንድ ሰው ቤት ሲሰራ የሚሰራው ቤት በርና መስኮት አሉት። አንድ ሰው ደግሞ ሞተ እንበል መቃብሩ በርና መስኮት የለውም። ይህ ምሳሌ ከገባችሁ ባህር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ሰው የምትለየው በትንሹ ነው።ቀይ ባህር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ። ደስተኛ እና እድለኛ ጄነራል ነኝ።እኔ ብሞት ታሪኬ አይሞትም። ቻው! ቻው! ማንም ሰው ወደ እኔ እንዳይጠጋ›› አሉና ጄነራል ተሾመ መኮንኖቹ ከተሰበሰቡበት ቦታ ተፈናጥረው ወደ ቀይ ባህር ጠረፍ አመሩ፡፡

#የሰራዊት አባላቱ ተደናግጠው ከተቀመጡበት ተነስተው የጄነራሉን የመጨረሻ ፍፃሜ ለማየት እየዘገነናቸው እንባ በእንባ ሆኑ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ህይወታቸውን ለማጥፋት የመሳሪያቸውን መጠበቂያ ከፍተው የጀነራል ተሾመን ምሳሌነት ለመከተል ተዘጋጁ።
ተሾመ ከወደቡ በስተቀኝ ለቀይ ባህር ውሃ መገደቢያ በተሰራ ግንብ ጠርዝ ላይ ጀርባቸውን ቀይ ባህር ፊታቸውን ወደ ምጽዋ ከተማ አድርገው ቆሙ። ቀጥለው በእጃቸው የነበረውን ክላሽኒኮቭ ጠመንጃ ወደ ቀይ ባህር ወረወሩና በወገባቸው ታጥቀውት የነበረውን ኮልት ሽጉጥ አውጥተው አፈሙዙን በአፋቸው ጎርሰው የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:10 ቃታውን ሳቡት። ድምጹ እንደተሰማም በጀርባቸው በቀይ ባህር ውሃ ላይ ወድቀው ሰጠሙ። ወዲያውም የጄነራሉን ሞት በምስክርነት ቆመው ካዩት መካከል ከ150 የማያንሱ መኮንኖችና ማዕረግተኞች በተለያየ መሳሪያ ህይወታቸውን አጠፉ።ሌሎችም እንደዚሁ አደረጉ፡፡በአጭር ደቂቃ ውስጥ አካባቢው ሬሳ በሬሳ ሆነ!

ኤርትራን ከኢትዮጵያ የነጠለ ጦርነት አይምጽዋ፤አስር አለቃ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Holistic knowledge for transformer generation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Holistic knowledge for transformer generation:

Shortcuts

Share