26/07/2025
የዝግጅት ጥቆማ - አሻም ወቅታዊ በዚህ ሳምንት
የአሻም ወቅታዊ ዝግጅት ክፍል በዚህ ሳምንት ከአዲስ አበባ ከተማ 748 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ አቅንታለች፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲው እየተከበረ የሚገኘውን የ70 አመት የምስረታ እና የዩኒቨርስቲው የማስተማሪያ ሆስፒታል 100ኛ አመት (አንድ ምዕተ-ዓመት) ክብረ- በዓላት እንዲሁም ዩኒቨርስቲው የሚታወቅበትን ‹‹የጎንደር የቃል ኪዳን ቤተሰብ›› ሀገር ዓቀፍ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩን መነሻ በማድረግ የዩኒቨርስቲውን የ70 ዓመታት ጉዞ ወደ ኋላ እንዲያስቃኙዋት ከዩኒቨርስቲው የምርምርና የትብብር ም/ፕሬዝዳንት አይንእሸት አዳነ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ም/ፕሬዝዳንቱ አሁናዊ የዩኒቨርስቲው ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም አንስተው ነግረዋታል፡፡ይህንኑ ዛሬ ምሽት ከ2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚተላለፈው አሻም ወቅታዊ ሳምንታዊ ዝግጅት ትከታተሉት ያመቻችሁ ዘንድ በአሻም የቴሌቭዥን ቀጥታ እና በተመሳሳይ ሰዓት በዩቱብ ቻናላችን ማግኘት እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
አሻም ለሁላችን!