A'ash stories - ዛንታታት ዓሽ

A'ash stories - ዛንታታት ዓሽ Welcome! Explore a world of captivating stories, from fiction to real-life adventures. Join us on a journey of imagination and inspiration!

Like our page for doses of storytelling magic. Share your story with us!

11/09/2024

Happy New Year, 2017 E.C!

22/08/2024

ርሑስ በዓል ኣሸንዳ, 2016 ዓ.ም.

10/07/2024

"The future belongs to the people who prepare for it." Jim Rohn

It is essential to constantly educate ourselves, acquire new skills, and stay open to change in order to succeed in the ever-evolving world. By staying proactive and forward-thinking, we can shape our own destiny and create a future that is fulfilling and successful. Those who stay ahead of the curve and invest in their own growth and development will be better equipped to seize opportunities and overcome challenges in the years to come. It is up to us to take control of our own future and be prepared for whatever may come our way.

07/04/2024

#1 ዛንታታት ዓሽ

ሮዝ: የ87 አመት የኮሌጅ ተማሪ
የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ፕሮፌሰሩ እራሳቸውን አስተዋወቁ እና ከማናውቀው ሰው ጋር እንድንተዋወቅ ሞክሩ አሉን።

ሮዝ፥ ትክሻየን ነካነካ አደረገችኝ።

እኔ፥ ትከሻዬን የነካ ለማየት ተነስቼ ዞር ስል፣ አንዲት የዋህ፣ የተሸበሸበ ፊት ያላት፣ ትንሽ አሮጊት ሴት መላ ሰውነቷን በሚያበራ ፈገግታ ደምቃለች።

ሮዝ፥ “ሰላም ቆንጅየ። ሮዝ እባላለሁ። ሰማንያ ሰባት አመቴ ነው። ላቅፍህ እችላለሁኝ?” አለችኝ። ሳቅኩኝ እና በጋለ ስሜት “በርግጥ ትችያለሽ!” ስል መለስኩ። እና ጥብቅ፣ ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝ።

እኔ፥ "ለምንድን ነው እንደዚህ ባለ ወጣት እና ንጹህ እድሜ ኮሌጅ የምትማሪው?" ስል ጠየኩ።

ሮዝ፥ “እዚህ የመጣሁት አንድ ሀብታም ባል ለማግኘት፣ ለማግባት እና ሁለት ልጆችን ለመውለድ ነው…” ብላ በቀልድ መልክ መለሰች።

እኔ፥ “አይ በቁም ነገር” ስል ጠየቅኳት። በእድሜዋ ኮሌጅ እንድትማር ያነሳሳት ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ጓጉቼ ነበር።

ሮዝ፥ "ሁልጊዜ የኮሌጅ ትምህርት የማግኘት ህልም ነበረኝ እና አሁን እየተማርኩ ነው!" አለችኝ።

ከክፍል በኋላ ወደ የተማሪዎች-ካፌ ህንፃ ሄድን እና አብረን ጁስ ጠጣን። ቶሎ ጓደኛሞች ሆንን። ለቀጣዮቹ ሶስት ወራት በየቀኑ ከክፍል ወጥተን ያለማቋረጥ እናወራ ነበር። ይህን "የጊዜ ማሽን" ውስጤ ጥበቧን እና ልምዷን ስታካፍለኝ ሁል ጊዜም ይማርከኝ ነበር።

በዓመቱ ውስጥ፣ ሮዝ የካምፓስ 'አይከን' ወይም ተምሳሌት ሆነች እና በሄደችበት ቦታ በቀላሉ ጓደኞች ታፈራለች። መልበስ ትወድ ነበር እና ከሌሎች ተማሪዎች በተሰጣት ትኩረት ተደሰታ እየኖረች ነበር።

ሴሚስተር ሲጠናቀቅ ሮዝን በእግር ኳስ ድግሳችን እንድትናገር ጋበዝናት። ያስተማረችንን መቼም ቢሆን አልረሳውም። ለታዳሚ አስተዋወቋት እና ወደ መድረክ ወጣች። መናገር ስትጀምር የተዘጋጀችውን ንግግር የተጻፈበት 3 በ4 ካርዶችን መሬት ላይ ጣለች። ተበሳጭታ እና ትንሽ እያፈረች ወደ ማይክራፎኑ ተጠጋች እና በቀላሉ፣

ሮዝ፥ “ይቅርታ በጣም ስለተናደድኩኝ ነው። ለዓብይ ፆም ቢራ ትቼ፤ ይሄ ውስኪ እየገደለኝ ነው! ንግግሬን በሥርዓት ላልለው እችላለው። ስለዚህ እኔ የማውቀውን ዝምብየ ልንገራችሁ" አለች።

እየሳቅን ጉሮሮዋን ጠራረገችና፣

ሮዝ፥ “እኛ ስላረጅን መጫወት አናቆምም፤ መጫወት ስላቆምን እናረጃለን። ወጣት ለመሆን፣ አራት ምስጢሮች ብቻ አሉ። ደስተኛ መሆን፣ ስኬትን ማግኘት፣ በየቀኑ መሳቅ እና ቀልድ ማግኘት አለባቹ። ህልም ሊኖራቹ ይገባል። ህልምህን ስታጣ ትሞታለህ። ብዙ ሰዎች አሉን፤ የሚንቀሳቀሱ ግን በሞት የተለዩን እናም መሞታቸውን የማያውቁ! በታላቅነትና እና በትልቅነት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። የአሥራ ዘጠኝ ዓመት ልጅ ከሆናችሁ እና አንድ አመት ሙሉ በአልጋ ላይ ከተኛችሁ እና አንድ ፍሬያማ ነገር ካላደረጋችሁ። ሃያ አመት ይሞላቿል። የሰማንያ ሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ ለአንድ ዓመት ያህል በአልጋ ላይ ብቆይ ምንም ሳላደርግ ሰማንያ ስምንት ይሆነኛል። ማንም ሰው በእድሜ ሊተልቅ ይችላል። ያ ምንም ችሎታ ወይም የተለየ ክህሎት አይፈልግም። ዋናው ነገር፣ ሁል ጊዜ የለውጥ እድልን በማግኘት ማደግ፣ መለወጥ እና ትልቅ መሆን ነው። አትጸጸትም። አረጋውያን ባደረግነው ነገር አይቆጨንም፤ ይልቁንም እኛ ባላደረግናቸው ነገሮች እንጸጸታለን። ሞትን የሚፈሩት ሰዎች ጸጸት ያለባቸው ብቻ ናቸው።“

ንግግሯን የደመደመችው በድፍረት “The Rose – Lifeline” የሚለውን ዘፈን በመዝፈን ነው።

እሷ እያንዳንዳችን ግጥሞቹን እንድናጠና እና በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንድንኖር መከረችን። በዓመቱ መጨረሻ ሮዝ ከእነዚያ ዓመታት በፊት የጀመረችውን የኮሌጅ ዲግሪ አጠናቀቀች። ከተመረቀች ከአንድ ሳምንት በኋላ ሮዝ በእንቅልፏ ላይ ሳለች በሰላም አረፈች።

በምሳሌ ያስተማረችውን ድንቅ ሴት በማመስገን ከ2000 በላይ የኮሌጅ ተማሪዎች በቀብሯ ላይ ተገኝቷል። ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ ለመሆን መቼም አልረፈደም። ይህንን አንብበው ሲጨርሱ ፣ እባክዎን ይህንን ሰላማዊ የምክር 'ዛንታ' ለጓደኞችዎ እና ለቤተሰብዎ ያጋሩት፣ እነሱ በእውነት ይደሰታሉ!

እነዚህ ቃላት ለሮዝ በፍቅር ትውስታ ውስጥ ተላልፏል።

ያስታውሱ፣ ታላቅነት ግዴታ ነው። ትልቅነት ግን አማራጭ ነው።

ባገኘነው ነገር ኑሮን፣ በሰጠነው ሕይወትን እንፈጥራለን።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251974020482

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A'ash stories - ዛንታታት ዓሽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share