26/01/2020
ዓለም ቲቪ በአዲስ መልክ እንቅስቃሴ ጀመረ!!
ዓለም ቲቪ ላለፉት ጥቂት ዓመታት አንድ ጠንካራ እና ተጽኖ ፈጣሪ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሆኖ ለመውጣት ሲያደርገው የነበረው ጥረት በፋይናንስ እና ሌሎች ተግዳሮቶች ምክንያት የተስተጓጎለ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ያጋጠሙትን መሰናክሎች አልፎ ራእዩን እውን ለማድረግ ስራውን ለአፍታም ሳያቋረጥ ቀጥሏል፡፡
ዓለም ቲቪ ዛሬም ጥረቱን አጠናክሮ በመቀጠል እና ወሳኝ የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ ለሀገራችን አንድ ተጨማሪ የቴሌቪዥን አገልግሎት ለመፍጠር በአዲስ ኃይል እና አደረጃጀት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
ዓለም ቲቪ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት በሀገራችን የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ የፕሮግራም እና የኮንሴፕት ሽግሽግ ያደረገ ሲሆን፣ በሀገራችን የብሮድካስቲንግ ህግ መሰረት የአሰራር ለውጥ ለማካሄድ የሚያሰፈልጉ የህግ ማሻሻያዎችንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በተለያዩ የፖሊሲ፣ አስተዳደራዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃይል እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች የታጠረውን የሀገራችን የፕሮድካስቲግ ሴክተር፣ በአንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ አስተዋጾ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው የዓለም ቲቪ እውን ሆኖ ለማየት የቴሌቪዥኑ አደራጆች በአዲስ አስተሳሰብ እና አመራር እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡
የዓለም ቲቪ ፕሮግራሞችን በቴሌቪዥን መስኮት የምናይበትን ግዜ ሩቅ አይሆንም፡፡
ከዓለም ቲቪ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነውን “ለውጥ” የተሰኘ ፕሮግራም ለቅምሻ ጀባ ብለናል፡፡
ዓለም ቲቪ፡ የመረጃ አለም፡፡