Fish- Green technology and Innovation

Fish- Green technology and Innovation This page was created aiming at promoting green innovations and mitigating environmental degradation

29/08/2025
18/11/2024

Hello members of this group. I am back to active.

የኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ልማት ባንክ እና ከተባባሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ጋር በጋራ በመሆን ኢኖቬቲቭ የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸውን ጀማሪ እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን...
13/08/2023

የኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ልማት ባንክ እና ከተባባሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ጋር በጋራ በመሆን ኢኖቬቲቭ የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸውን ጀማሪ እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን በማወዳደር ምርትና አገልግሎታቸውን ወደ ገበያ በማስገባት ውጤታማ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር ይቻል ዘንድ የብድር ዋስትና የፋይናንስ አቅርቦት አመቻችቷል፡፡
በመሆኑም የመወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ኢንተርፕራይዞች ከጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከታች በተቀመጠው መስፈንጠሪያ በመጠቀም በቀረበው የፕሮፖዛል ቅጽ መሰረት የቢዝስ ሀሳባችሁን በመላክ እንድታመለክቱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

http://registration.mint.gov.et/
ለበለጠ መረጃ በ + 251 967 944 500 ወይም +251 993 530 103 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን

የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ግብአትነት በመቀየር እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪ ማዳን ለሚያስችል ፕሮጀክት ትግበራ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፦ ====(በኢትዮጵያ...
10/08/2023

የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ግብአትነት በመቀየር እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪ ማዳን ለሚያስችል ፕሮጀክት ትግበራ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፦
====
(በኢትዮጵያ ከ380,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ክምችት ያለ ሲሆን መልሶ መጠቀም የተቻለው 10 ከመቶ ብቻ ነው።)

የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ግንባታ ግብአቶች በመቀየር፣ የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ፣ ለስራ እድልና ሃብት ፈጠራ ለማዋል ያለመ ፕሮጀክት ትግበራ አጋርነትና ድጋፍ ማመቻቸት ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ፎዚያ አሚን (ዶክተር) ና በአዲል ቴክኖሎጂስ እና የኢኖቬሽን ማእከል መስራችና ባለቤት ዶክተር አዲል አብደላ ፈርመውታል።

እንደ ዶክተር አዲል አብደላ፥ በኢትዮጵያ እና በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች የፕላስቲክ ቆሻሻ በስፋት ተከማችቶ ይገኛል። ይህን አካባቢ የሚበክል ክምችት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ላይ ያለመ ቴክኖሎጂ በበርካታ ዓለም አገራት እየተሰራበት ይገኛል።

በእኛም አገር ከ380,000 ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ተከማችቶ እንደሚገኝ የቆዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ጠቁመው፥ ይህን ክምችት ለአካባቢ ተስማሚ ወደ ሆኑ ተኪ የግንባታ ቁሳቁሶች በመቀየር መጠቀም፥ ሃብት ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪን መቀነስ የሚያስችል የቴክኖሎጂ አማራጭ ይዘው መቅረባቸውን አስረድተዋል።

ዶክተር አዲል አክለውም አስፈላጊው ድጋፍ ከተገኘ ከስድስት ወራት ባነሰ ተረፈ ምርቶቹን በማሰባሰብ ለግንባታ አስፈላጊ ወደ ሆኑ ግብአቶች ለመቀየርና ለበርካቶች የስራና የሃብት ምንጭ ለመሆን እንደተዘጋጁ አስረድተዋል።

ሚንስቴር መስሪያቤቱ የቴክኖሎጂውን ጠቀሜታና ችግር ፈችነት በማመን የመንግስት እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ምቹ ሁኔቻ እንዲፈጥርላቸው ጠይቀዋል።

ድርጅታቸው የሚፈልጋቸው ድጋፎች የቴክኖሎጂ መትከያ የኢንቨስትመንት ቦታ፣ የፕላስቲክ ማከማቻ በቂ ቦታ፣ ወጣቶችንና ስራ ፈላጊዎችን በአመቺነት ማደራጀት፣ ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማገዝ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ያካተቱ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክብርት አማካሪ ሚንስትር ዲኤታ ፎዚያ አሚን (ዶክተር) የተጠየቀው ትብብር ቴክኖሎጂን እና ፈጠራን የሚያበረታታ፣ የተከማቹ በካይ ፕላስቲኮች የሚፈጥሩትን ችግር ለመፍታት መነሳሳቱ በራሱ የሚበረታታ ነው ብለውታል።

አክለውም ለአገሪቱ ወጣቶች የስራና የሃብት እድል በመፍጠር፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርን የማመቻቸት እና ከውጭ የሚገቡ የግንባታ እቃዎችን በመተካት የግንባታ ዘርፉን የሚያበረታታ በመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግለት ከሚመለከታቸው ጋር ለመነጋገር እንሰራለን ብለዋል።

መንግስት ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍና የዳበረ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በማሰብ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ እየሰራ ይገኛል።

አክለውም ለፈጠራ ኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥርዓቱ አጋዥ ለሆኑ የምርምርና ችግር ፈች ፕሮጀክቶች ወሳኝ ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የጠቀሱት ዶክተር ፎዚያ ለስምምነቱ ትግበራ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር ይሰራል ብለዋል።

ይህ ስምምነት ለችግር ፈች ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር፥ ለስራ እድልና ሃብት ፈጠራ ምቹ ሁኔታን በማስገኘት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በውይይቱ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተመራማሪዎ

25/07/2023

የምርምር ድጋፍ ውድድር ጥሪ!!!
====
የኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፥ ከአፍሪካ የቴክኖሎጂ ጥናት ማዕከል (African Center for Technology Studies) ጋር በመተባበር ምርምሮችን በአገር አቀፍ ደረጃ አወዳድሮ መደገፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም በአገራዊ የልማት አቅጣጫዎች የትኩረት ዘርፎች ላይ ችግር ፈች የምርምር እና የኢኖቬሽን ሥራዎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አከባቢያዊ ፋይዳ ማስገኘት ወደሚችሉበት ደረጃ ለማሸጋገር ሀገር አቅፍ ውድድር አመቻችቷል፡፡

በዚህ ማስታወቂያ ፎርም ላይ የተቀመጠውን የመወዳደሪያ መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ከሀምሌ 13/ 2015 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 23/ 2015 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ ይጋብዛል።

ለማመልከት ቀጥሎ በተቀመጠው የGoogle ማስፈንጠሪያ የተቀመጠውን ቅጽ በመጠቀም በቀረበው የኮንሰፕት ኖት /የውጥን ሃሳብ ቅጽ መሰረት ሞልተው ይላኩ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

ለበለጠ መረጃ +251 912010792 (ዶ/ር ሰለሞን በላይ) በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911856521

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fish- Green technology and Innovation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fish- Green technology and Innovation:

Share

Category