
03/05/2025
ወንዶች ለምን ከቤታቸው ውጭ ሄደው DSTV ቤት ወይም በካፌዎች ውስጥ እግር ኳስ ማየትን ይመርጣሉ?
እንጃ እስካሁን በታላላቅ ምሁራን በሰፊው የተጠና ምክነያት ባይኖርም አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ገጠመኛቸውን ለሰፊው ህዝብ እንደሚከተለው አጋርተዋል 😂😂
ሚስት፡ «ወዴት እየሄድክ ነው?»
ባል፡ «ወዴ DSTV ቤት ኳስ ለማየት እየሄድኩ ነው»
ሚስት፡ «DSTV እዚህ አለ አይደል እንዴ ? ለምን ከእኔ ጋር አብረን አናይም?»
ባል፡ «እሱማ ልክነሽ አለ ግን ከጓደኞቼ ጋር ማየት እፈልጋለሁ»
ሚስት፡ «አሃሃ ስለዚህ እኔ ለአንተ ምንም ማለት አይደለሁም ማለት ነው? ከእኔ ጓደኞችህን ታስበልጣለህ ማለት ነው?»
ባል፡ «እሺ እሺ ውዴ በቃ ይቅርታ !! ነይ አብረን እናያለን»
ሚስት፡ «እኔምልህ ውዴ ግብ ጠባቂው ለምን ጥቁር መለያ ለበሰ?
ባል፡ «አንድ የቅርብ ዘመዱ ሞታ ኃዘን ላይ ስለሆነ ነው»
ሚስት፡ «ስማኝማ ተንታኙ (Commentator) የሁሉንም ተጫዋቾች ስም እንዴት ሊያውቀው ቻለ?»
ባል፡ «ያው ስራው ስለሆነ ማወቅ አለበት»
ሚስት፡ «ኦውው ቀይ የለበሱት ደስ ይላሉ ... ጎል አገቡ አይደል?»
ባል፡ «አይ አላገቡም offside ነው»
ሚስት፡ «Offside ደግሞ ምንድን ነው?»
ባል፡ «ኧረ እየቀለድኩ ነው ጎል ነው»
ሚስት፡ «እሺ ግን offside ምንድ ነው?»
ባል፡ «Offside የአሰልጣኙ ስም ነው»
ሚስት፡ «አሃ ነው እንዴ? እና አሰልጣኝ የት ነው ያሉት?»
ባል፡ «ከሜዳ ውጪ ነው»
ሚስት፡ «ለምን ገብቶ አይጫወትም?
ባል፡ «አይ እሱ ተጫዋቾቹንና የጨዋታ ስልቶችን ይለውጣል እንጅ አይጫወትም»
ሚስት: «እስካሁን አላየኋቸውም። መሲና ሮናልዶ የታሉ ታዲያ?»
ባል: «ኧረ ውደ ተይ እንጅ እነሱኮ የሚጫወቱት ለሌላ ቡድን ነው»
ሚስት፡ «እሺ ፔሌና ማራዶናስ እዚህ አሉ?»
ባል፡ «እነሱ የሉም ሞተዋል»
ሚስት፡ «OMG! የፈጣሪ ያለህ... ምን ሆነው ሞቱ ?»
ባል፡ «አይገርምሽም ከባለቤታቸው ጋር እግር ኳስ ሲያዩ ነው አሉ የሞቱት»