02/09/2025
የዲያቆን ጌቱ ተሾመ አስደናቂው ምላሽ !!!😳🤔
አንድም ሰው ይህቺን ልጅ በበቂ አመክንዮ ሲሞግታት ዐላየሁም። አንድም ሰው አልሞገታትም። እኔ በግሌ በግልጽ ስላነሣችው እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። ጋብቻን እስካልነቀፉ፣ ብልግናን እስካላበረታቱ... ድረስ በድፍረት ወጥተው የኅብረተሰቡን ችግር ለማሳየት የሚጥሩትን አደንቃለሁ።
ስለ ልጅቷ ፐርሰናሊቲ አላወራም። አላውቃትም። ግን ማን ያዘዋልና እግረኛው ጋር ቀርባ ያወራቻቸው ትክክል ናቸው። ስንቱ ወጣት ይሄንን ተግባር አደባባይ ላይ ይፈፅማል። "ከትዳር ውጪ የሚደረግ ግንኙነት ዝሙት ነው" ብለን ብናምንም ስንቱ ይህንን እንደሚተገብር አናውቅም። ግለ ወሲብም ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ግንኙነትም ጸያፍ ነው። ይህንን በግልጽ አውጥተው "ከዚህ እንዴት እንውጣ?" የሚሉ ሰዎችን ማጥላላት አስቂኝ ነው። በድብቅ የሚተገብር ሰው በሞላበት ኹኔታ "ስለዚህ አይወራም፤ የሕዝቡን ዕሴት ይንዳል" አይባልም። ካስፈለገ ለምን እንክትክቱ አይወጣም። ስንት ወላጆች ልጆቻቸውን ከዚህ ሱስ ማውጣት ያልቻሉት በግልጽ ስለማያወሯቸው ብቻና ብቻ ነው።
ይህን ችግር ማስተካከል ያልቻልነው ፍትወት ተፈጥሮአዊ መኾኑን ማመን ስላልፈለግን ነው። ሰው የተባለ ኹሉ የወሲብ ፍላጎት አለው። አይደለም እኛ ቀርቶ ዕድሜ ልካቸውን ከተቃራኒ ጾታ ርቀው የሚኖሩ መነኰሳት የዚህ ፍላጎቱ አላቸው። የመቋቋምና ያለ መቋቋም እንጂ ፍላጎቱ በሰው ኹሉ ላይ ያለ ነው። አጉል ጨዋ ለመኾን ስንሞክር ይህንን ማመን አንፈልግም። ብዙዎች ወደ ግለ ወሲብ፣ ወደ ዝሙት የሚገቡት ይኼ የተፈጥሮ ፍላጎት በውስጣቸው ስላለ ነው። አስቀድመን ይህንን እውነታ እንረዳ።
ይህንን ፍላጎት ሥራ ላይ ማዋል እንደሚቻል አወራች። በቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ፍትወት ሲነሣ እንድንሠራ፣ እንድንሰግድ... የሚነገረን ለዚህኮ ነው። በፖርኖግራፊ፣ በማስተርቤት... ጉዳይ ወጣቱን የሚያሳትፉ ዝግጅቶች መደረግ አለባቸው። በሽታው የተደበቀ መድኃኒቱ አይገኝም።በርቺ ሲስቱካ !!!❤️🙏❤️
©ዲያቆን ጌቱ ተሾመ