ቅን ልቦች የሬዲዮ ፕሮግራም/Qin liboch

ቅን ልቦች የሬዲዮ ፕሮግራም/Qin liboch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቅን ልቦች የሬዲዮ ፕሮግራም/Qin liboch, Media/News Company, Addis Ababa.

26/03/2025

በተመጣጣኝ ክፍያ የምትፈልጉትን አይነት ዜና እና ማስታወቂያ ከ 48000 በላይ ተከታይ ባለው ፌስቡካችን ማስተላለፍ ምትፈልጉ በውሰሰጥ መስመር አናግሩን

26/03/2025

ይሄንን 48,000 በላይ ተከታይ ያለውን የፌስቡክ ፔጅ ለመልካም ስራ እጠቅመበታለው የሚል ሰው ካለ በቅናሽ ዋጋ እንሸጣለን ትክክለኛ ገዢ የሆናቹ ብቻ በውስጥ መስመር አውሩን

[ የተፈራው ደረሰ ። አሁን የዚህችን ወጣት ንጹህ ስሟን ስሟን የሚመልስላት ማን ነው ? ማንን ነው የምትከሰውስ ? ]**********************************************...
26/06/2024

[ የተፈራው ደረሰ ። አሁን የዚህችን ወጣት ንጹህ ስሟን ስሟን የሚመልስላት ማን ነው ? ማንን ነው የምትከሰውስ ? ]
************************************************
ለእውነት መቆም

ሰረቀች ከተባለው መኪና በላይ የመግዛት አቅም ያላቸው ሚሊየነር አባት አሏት።

#አሁን በስልክ ሳወራት፣ ስህተት ተፈጥሮ እንደሆነና ከወንጀሉ ነፃ ሆና መኖርያ ቤቷ እንዳለች ነግራኛለችና ልጅቱ " መና ከበደ" ሰረቀች የተባለው መኪና በስህተት እንደሆነ ይታወቅላት።

አይዞሽ እንበላት እናረጋጋት።

መና ከበደ ትባላለች። እኔ እማውቃት ከሦስት ዓመት በፊት እንግሊዝ ሀገር እማውቃት አክስቷ ጋር እኔ እምሰጠውን አገልግሎት ለአባቷ አቶ ከበደ ለማግኝት እኔ ጋር ሲመጡ ነበር።

አባቷ አቶ ከበደ ከወጣትነት እስከ አሁን እስካሉበት እድሜያቸው ድረስ ታታሪ ሰራተኛ እና በሚልየን የሚገመት ሀብት እንዳፈሩ አጫውተውኛል።

በተለይ ( መኪና ሰረቀች ) ስለተባለችው ልጃቸው " መና " ሲያወሩኝ፣ እጅግ የሚተማመኑባት፣በትምህርት ጥሩ ደረጃ ደርሳላቸው ከባህርዳር ዩኒበርስቲ እንደተመረቀችላቸውና በገዙላት መኖርያ ቤት ምንም ሳይጎድልባት የሚያኖሯት የሚወዷት ልጃቸው እንደሆነች አጫውተኛል።

እኔም እንዳየሁት ከሆነ " መና " በጥሩ ስነ-ምግባር ያደገች፣ ጉዳት የደረሰባቸውን አባቷን እምትንለባከብ ምንም ሳይጎድልባት በጥሩ ሁኔታ ያሳደጓት እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ።

ከዚህ ሁኔታ አኳያ እንኳን ሰረቀች የተባለውን መኪና ልትሰርቅ ይቅርና፣ ሰረቀች ከተባለው " ቪትስ " መኪና በላይ ሊኖራት ወይም ሊገዙላት ታታሪ ጎበዝ፣ እና ጉዳት ያላሸነፋቸው አባት እንዳሏት ልመሰክር እችላለሁ።

ውድ እህቴ ፣ አክባሪዬ " መና ከበደ" ተደረገ ተብሎ የተወራብሽ ወሬ ምን ያህል ልብሽን እንደሚጎዳው እረዳለሁ።

ይሁንና ጠንካራ እና ታታሪ አባትሽን፣ ወንድምሽን እና እንቺን በቅርበት እማውቃችሁ እኔ " ሰሎሞን አማረ" ስለ አንቺና ስለቤተሰቦቻችሁ ንፁህነት ስመሰክር ታላቅ ኩራት ይሰማኛል።

ስለሆነም አይዞሽ በርቺ ጠንክሪ ።

© Solomon Amare Kuch Kuch

የዛሬ አንድ አመት ከ6ወር አካባቢ በስራዬ ላይ ያጋጠመኝ አሳዛኝ ነገርበአንድ ታዋቂ የመንገስት ሆስፒታል  የማታ ተረኛ ሀኪም ነበርኩ። በእለቱ በዛ ያሉ እናቶችን በኦፕሬሽን (cesarean s...
30/05/2024

የዛሬ አንድ አመት ከ6ወር አካባቢ በስራዬ ላይ ያጋጠመኝ አሳዛኝ ነገር

በአንድ ታዋቂ የመንገስት ሆስፒታል የማታ ተረኛ ሀኪም ነበርኩ። በእለቱ በዛ ያሉ እናቶችን በኦፕሬሽን (cesarean section) አዋልደን ስለነበር ሁላችንም ድካም ውስጥ ነበርን።

ከሌሊቱ 9 ሰዓት ስልኬ ጠራ። በእለቱ አብራኝ ተረኛ የነበረችው የእኔ አንድ ጁኒየር ሬዚደንት (R2) ሀኪም ነበረች። "CORD አለ ዶክ" አለችኝ።

CORD PROLAPSE የፅንሱ እትብት ከፅንሱ ቀድሞ ሲወጣ ማለት ሲሆን በደቂቃዎች ውስጥ ኦፕሬሽን ካልተሰራ የፅንሱ ህይወት ያልፍል።

እኔም የኦፕሬሽን ክፍል ልብሴን ይዤ የሰመመን ሀኪሞችንና የኦፕሬሽን ክፍል ነርሶችን ቀስቅሼ በሩጫ ሄድኩ። እናቲቱን ተገቢውን ምርመራ ካደረኩ በኋላ በፍጥነት ኦፕሬሽን መደረግ እንዳለባት አሳወኩ።

'ሚስቴን መቀስ አይነካትም አለ' ባልየው። እኔም በንዴትና በብስጭት ለማስረዳት ሞከርኩ። ሞቼ እገኛለሁ አለ። የሚገርመው ነገር የእናትየው ከባልየው ጋር መስማማትና በአንድ ቋንቋ መናገር ነው። በጊዜው የነበሩ ባለሙያዎች
በሙሉ ለሰውየው ለማስረዳት ሞከሩ። ሩጫው ከጊዜ ጋር ነበር። በደቂቃዎች ከሚቆጠር ጊዜ።

በጊዜው የነበሩ ሲኒየር ሀኪሞች ሁሉ ቢመጡም ከሀሳቡ ንቅንቅ አላለም። ምክንያት ሲጠየቅ ሚስቴን መቀስ አይነካትም ነው። የእናቲቱም ሀሳብ ተመሳሳይ ነው። ፈቃደኛ አልሆነችም።

ባልየው የሆነ ሰው ጋር ስልክ ደወለ። እጁን ሆዷ ላይ አድርጎ አይኑን ጨፍኖ አሜን አሜን አሜን ይላል። ምንድነው ብዬ ጠየኩት "አዋቂ ፓስተር ነው አየፀለየላት ነው" አለኝ። እንደማይሳካለት አውቃለሁ።

ሁሉም ተስፍ ቆርጧል። በጊዜዉ የነበሩ አዋላጅ ነርሶች ፣ ሬዚደንት ሀኪሞች ፣ እጩ ዶክተሮች (interns) ፣ ሲኒየር ሀኪም እንዲሁም የሌሎች ህመምተኛች አስታማሚዎች። የፅንሱ የልብ ምት በአልትራሳውንድ ስናይ እየቀነሰ ነው።

ለሰዓታት አምጣ ህይወቷ ያለፈ ሴት ልጅ ወለደች። አሁንም ህይወቷ ያለፈ ጨቅላ ህፃን ላይ ካልፀለይኩ አለ። ፓስተር ተብየው ጋር ደውሎ እጁን የህፃኗ ሆድ ላይ አድርጎ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።

እንቅልፍ ማጣት ድካም ብስጭት ስለነበረብኝ እሱን ማየት አልፈለኩም። በጥበቃ ከሆስፒታል እንዲወጣ አስደረኩ።
አሁን አሁን ያለው የሀይማኖት ቢዝነስና ማጭበርበር የመጨረሻ የአደገኝነት ምእራፍ ላይ ደርሷል። ህመምተኞች የሀኪም ምክር እንዳይቀበሉ ፣ መድሀኒት እንዳይወስዱ ፣ ክትትል እንዳያደርጉ እንዲሁም ጥርጣሬ እንዲፈጠርባቸው እያደረጉ ይገኛሉ።

በመጨረሻ ግን ተጎጂ የሚሆነው ይህ ምስጊን ህዝብ መሆኑ ይህ አጋጣሚ ምስክር ነው።

ዶ/ር በላይ አለሙ: የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
ለማማከር ☎️ 0977297156 ይደውሉ

ለሪል ስቴት በሊዝ የገዛውን መሬት ፡  ለሌላ  ጥቅም ያዋለው ናይጄሪያዊ ኳስ ተጫዋች ።.........ጄጄ ኦካቻ ፡ ከቀድሞ የናይጄሪያ ቡድን ተጫዋችነቱ በተጨማሪ ፡ ብዛት ባላቸው የአውሮፓ ክ...
25/04/2024

ለሪል ስቴት በሊዝ የገዛውን መሬት ፡ ለሌላ ጥቅም ያዋለው ናይጄሪያዊ ኳስ ተጫዋች ።.........
ጄጄ ኦካቻ ፡ ከቀድሞ የናይጄሪያ ቡድን ተጫዋችነቱ በተጨማሪ ፡ ብዛት ባላቸው የአውሮፓ ክለቦች ያሳይ በነበረው ድንቅ ብቃት አለም ያወቀውና ተደናቂነትን ያተረፈ ዝነኛ ኳስ ተጫዋች ነበር ። ....
ጄጄ ፡ ከእግር ኳስ አለም በይፋ ከተሰናበተ በኋላም በሀገሩ ናይጄሪያ ውስጥ በተለያዩ ቢዝነሶች ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን ፡ በቅርቡ ባደረገው ነገር መነጋገሪያ ሆኗል ።...
ኦካቻ በሚኖርበት ከተማ. .. ለራሱና ለቤተሰቡ የሚሆን እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ሰርቶ ካጠናቀቀ በኋላ ፡ ለዴልታ ስቴት ማዘጋጃ ቤት ብዛት ያላቸው ቤቶችን ለመስራት ጠይቆ ሰፊ መሬት በሊዝ ይገዛል ።

በዚህ በወሰደው መሬት ላይም ባጠቃላይ ብዛታቸው መቶ የሚሆኑ የተለያዩ ባለአንድና ሁለት መኝታ ቤት መኖሪያ ቤቶችንና ኮንደሚኒየሞችን ካሰራ በኋላ ...........
በዴልታ ስቴት ለሚኖሩ በእድሜ ገፋ ላሉ .. ችግረኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ሁሉንም ቤቶች ፡ በነጻ ሰጥቶ ሰውን አስገርሟል ።....
ጄጄ ሙሃመድ ያቪዝ ኦኮቻ ቤቶቹን ለነዚህ ሰወች ካስረከበ በኋላ እንደተናገረው. ..

እኔ ሚሊየን ዶላር የፈጀ ቪላ ውስጥ እየኖርኩ ፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ችግረኞች ምንም ማድረግ አለመፈለግ ሀጢያት ነው ብሏል ። .......
( ናይጄሪያ በአለም የታወቁ ሀብታሞች ያሉባት ሀገር ብትሆንም ፡ ለመስጠት በራሱ የሚሰጥ ልብ ይፈልጋልና. .. እነሱ ያላሰቡትን ኦካቻ አድርጎ አሳይቷቸዋል ።

❤️❤️❤️🙏🙏🙏እነ ሶልያናንን ለማሳከም 400ሺህ የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል እንዲሁም እንስካሁን ድረስ ወደ 63ሺህ የካናዳ ዶላር ወይንም 46ሺህ የአሜሪካን ዶላር በgo Fund me...
23/04/2024

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

እነ ሶልያናንን ለማሳከም 400ሺህ የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል እንዲሁም እንስካሁን ድረስ

ወደ 63ሺህ የካናዳ ዶላር ወይንም 46ሺህ የአሜሪካን ዶላር በgo Fund me ተዋጥቷል::

ነገር ግን ወንድማችን ክብሩ ኮሜዲያን እሸቱ እንደ ወትሮው ሁሉ ለእነዚህ ልጆች ለህክምና የሚሆን

በዶንኪ ቲዮብ :-

* 3 ቀን
* 4 ቀን ወይንም
* ሳምንት ይፍጅ

LIVE ላይ ቁጭ ብሎ 400ሺህ ዶላሩ እስኪሞላ ቢያሰባብስ እርግጠኛ ነን

በመላው ዓለም ብዙ ደጋጋ ኢትዮጵያውያን ስላሉ እንደሚሳካ ባለሙሉ ተሰፋ ነው::

እኛም ከጎን ነን.........

አሻራችንን እንጣልን
ይሄን መልካም ሀሳብ ሼር በማድረግ ተባበሩ::

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

የኛ አባት 😭እኚህ አባት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት በየትም ቦታ ሄደው ሰርተው የመኖር ህገመንግስታዊ መብት አላቸው::ነገር ግን አንዳንድ ቤተሰቦቻቸው ና ማህበረሰቡ በጥ ላ ቻ ና በመጥ...
18/04/2024

የኛ አባት 😭

እኚህ አባት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት በየትም ቦታ ሄደው ሰርተው የመኖር ህገመንግስታዊ መብት አላቸው::

ነገር ግን አንዳንድ ቤተሰቦቻቸው ና ማህበረሰቡ በጥ ላ ቻ ና በመጥፎ ስነምግባር ያሳደጏቸው ሰዎች

እኚህን አባት :-

* ከየት መጣህ ?
* ለምን መጣህ ?
* ማን ነህ ?
* ምንድን ነህ ?

እያሉ እየደበደቧቸው ና እያሰቃዯቸው
መረጃው ወጥቷል::

መንግስት ለእኚህ አባት ሙሉ አላፊነት እንዲወስድ ና እኚህን አባት አፈላልጎ

በህይወት:-

* ይኑሩ
* አይኑሩ

እንዲያረጋግጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን በትህትና መንግስትን ጠይቀዋል::

እንዲሁም ብዙ ኢትዮጵያውያን በህይወት ካሉ እባካችሁ እንርዳቸው ፈልጉልን ብለዋል::

ለኚህ አባት ድምፅ መሆን ትልቅ መልካም ነገር መስራት ነውና ሼር በማድረግ አፋልጉ
ድምፅም ሁኑ ተብሏል::

አባታችን

🙏🙏🙏

ካፌ ወይም ሬስቶራንት ስገባ ደስ እያለኝ ቲፕ የምሰጣቸው! የመፀዳጃ ክፍል እና ኮሪደር የሚያፀዱ እናቶች ። አስባችሁታል ሰው ገብቶ በወጣ ቁጥር ገብተው ያፀዳሉ አንድ አንድ ሰው እኮ ተጠቅሞ ...
11/04/2024

ካፌ ወይም ሬስቶራንት ስገባ ደስ እያለኝ ቲፕ የምሰጣቸው! የመፀዳጃ ክፍል እና ኮሪደር የሚያፀዱ እናቶች ።

አስባችሁታል ሰው ገብቶ በወጣ ቁጥር ገብተው ያፀዳሉ አንድ አንድ ሰው እኮ ተጠቅሞ ውሀ ሳያፈስም ነው የሚወጣው ።

ከዛ ኮሪደሩን ይወለውላሉ ትንሽ ፋታ ሲያገኙ እዛው ኮሪደሯ ጋር ቁጭ ይሉና ስለሚያሳድጓቸው ልጆች እና የልጅ ልጆች ያስባሉ ። ደሞዛቸው አንድ ሺ ብር የሚሞላ አይመስለኝም በሷ ልጆቻቸውን ያስተምራሉ ።

ማንም ልብ አይላቸውም!! ኪሳቸው ውስጥ የሆነች ብር ውሽቅ ሲደረግላቸው ፊታቸው ይበራል ቲፕ ስላለመዱ ድንግጥ ይሉና ከዛ ምርቃታቸው ከሰጠሀቸው ገንዘብ በላይ ነው!!!

እስኪ ሞክሩት የሆነች ነገር ጥቅልል አርጋችሁ ኪሳቸው ውስጥ ወሸቅ አድርጉ እና ምርቃታቹን ተቀበሉ !!!!

የማይጠገብ ቀልድየሀይማኖት አባቶች እኮ ልዩ ናቸው። ይቺ አለም ከንቱ ናት ለሰማይ ቤታችሁ በምድር ዘርን ዝሩ ለዚህ ምድር አትጨነቁ ስለ ምድር ማሰብ ከንቱ ነው። ብለው ይሰብኩናል፤ እኛም የእ...
11/04/2024

የማይጠገብ ቀልድ
የሀይማኖት አባቶች እኮ ልዩ ናቸው። ይቺ አለም ከንቱ ናት ለሰማይ ቤታችሁ በምድር ዘርን ዝሩ ለዚህ ምድር አትጨነቁ ስለ ምድር ማሰብ ከንቱ ነው። ብለው ይሰብኩናል፤ እኛም የእነሱን ቃል አምነን ከጉድለታችን ሰጥተን ስንመለስ እነሱ በ v8 በሹፊር ሆነው በመኪናው መስኮት በኩል መስቀል አውጥተው እየባረኩን ላሽ ይላሉ።*****
እኛ ከ/ቤክ መልስ በእግራችን ብቻ ሳይሆን በባዶ ሆዳችን ወደቤታችን ተመልሰን እቤት ስንገባ የቤቱ ጣሪያ የሚያፈስ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ስንገባ የኛ አባቶች ደግሞ በሁለት ዘበኛ የሚጠበቅ ባለ 3 እና ባለ 2 ፎቅ ቤት ውስጥ ይገባሉ። እኛ ይቺ አለም ከንቱ ነች የሚለውን የአባቶቻችንን ቃል እያሰብን የሰማዩን ስንናፍቅ አባቶቻችን ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ የሚያከራዩትን ቤት ሂሳብ ሲሰሩ ሲደምሩ ሲቀንሱ ያድራሉ።*****
አባቶቻችን ሲያስተምሩ እንዲህ ይሉናል
በሰማይ ቤት ትልቅ ክብር እና ቦታ ያለው ሰው ማለት ይቺን አለም ንቆ ፤ ድንጋይ ተንተርሶ አፈር ልሶ ፤ ጥሬ ቆርጥሞ ፤ ሰውነቱን ለጌታ ክብር አዋርዶ በዱር ፤ በጫካ ፤ በገዳም የሚኖር በባዶ እግሩ የሚሄድ ፤ ለገላው የማይጨነቅ ፤ 24 ሰአት ቆሞ የሚፀልይ እሱ በሰማይ ቤት ልዩ አክሊል አለው ብለው ያስተምሩናል። (ታዲያ ለምን እዛ ገዳም አትሄዱም? ብሎ የሚላቸው ሰው ግን የለም።) *****
ግን ቆይ አባቶቻችን የተደላደለውን ኑሮ ትተው ገዳም ይሄዱ ይሆን?)
አባቶቻችን ግን በመሀል ከተማ ዘንጠው እየኖሩ ፤ ብስል ከ ጥሬ ፤ አማርጠው እየበሉ ሲፈልጉ ከሀገር ሀገር ተንደላቀው እየዞሩ ያም ሳያንሳቸው 15 ቤተሰብ የሚያስተዳድር ደሞዝ ተከፋይ ሆነው ፤ ቀለብ አንዴ በአርባ ፤ አንዴ በሙት አመት እያሉ በልተው ጠጥተው ፤ በሚያምር ሶፋ ወንበር ላይ ተቀምጠው ፤ በግራ እና በቀኝ ሁለት ዣንጥላ ተይዞላቸው ዝናብ እና ፀሐይ ንፋስ እንዳይነካቸው እንደ እንቁላል ሲንከባከቧቸው ውለው በክብር ወደ ቪላ ቤታቸው ይሄዳሉ።*****
የዚህ አይነት ብዙ እውነቶችን መዘርዘር ይቻላል። ህዝቤ ግን ይሄን እውነት ደፍረህ ስትነግረው በሀይማኖቴ አትምጣብኝ ይልሀል። አባቶቻችንም ብልጦች ናቸው ፤ ጥያቄ ህዝቡ እንዳያስነሳ የእግዚያብሔር ቃል ነው ብለው በሀሰት ትብታብ አእምሮውን ተብትበውታል። እንዲነቃ ብለህ ብታስተምረውም እንኳን ከገባበት ድንዛዜ የተነሳ ይሰድብሀል እንጂ እንዴት እና ለምን በማለት አይጠይቅም።
በቃ ሀይማኖት ማለት እንዲህ ነው!!

አስተናጋጆች ላይ ዝም ብለህ አትጩህ ። የምትፈልገውን አጥርተህ ጠይቅ ። እነሱ ቆመው ከሌላ ጋ የጀመርከውን ወግ አትቀጥል ። ዝም ብለህ አታቁማቸው። ይደክማቸዋል ፦ብዙ ሰው ሲያስተናግዱ ውለው...
11/04/2024

አስተናጋጆች ላይ ዝም ብለህ አትጩህ ። የምትፈልገውን አጥርተህ ጠይቅ ። እነሱ ቆመው ከሌላ ጋ የጀመርከውን ወግ አትቀጥል ። ዝም ብለህ አታቁማቸው።

ይደክማቸዋል ፦

ብዙ ሰው ሲያስተናግዱ ውለው ሊሆን ይችላል ። አሟቸው ሊሆን ይችላል ። ውጣውረድ አለባቸው አዙሯቸው ሊሆን ይችላል ።

እንዴት ያልኩት አልመጣም ቆየህ/ሽ ብለህ አታካብድ ትንሽ እንዲሳሳቱ ፍቀድ ።

አልፈገጉም ብለህ አትታዘባቸው ሲስቁላቸው ዚፔን ካልከፈትኩ የሚል አዝጓቸው ሊሆን ይችላል።

ሰላምታ አስቀድም ። አይንህ ላይ ትንሽ ትህትና አሳያቸው ። ደምበኛ ከሆንክ በስማቸው ጥራቸው ። እንደ-ማሽን ስሜት የሌላቸው አይምሰልህ ።

የሚሰራን እናበረታታ ።

የሚሰሩትን በተረዳን ቁጥር ሌባ ፣ሴተኛአዳሪ፣ አጭበርባሪ እና ጉበኛ እንዲቀንስ አስተዋፆ ልናበረክት እንችላለን ።

«ማታ ወደ አልጋሽ ሄደሽ ጓደኞችሽ የተሻለ ቦታ ደርሰው አንቺ አሁንም እየታገልሽ እንደሆነ ስታውቂ ይፈትንሻል። ፈተና የሌለው ምንም ነገር የለም ስኬት እንደተለያየ ሰው ይለያያል፣ ለአንዳንድ ...
09/03/2024

«ማታ ወደ አልጋሽ ሄደሽ ጓደኞችሽ የተሻለ ቦታ ደርሰው አንቺ አሁንም እየታገልሽ እንደሆነ ስታውቂ ይፈትንሻል።
ፈተና የሌለው ምንም ነገር የለም ስኬት እንደተለያየ ሰው ይለያያል፣
ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣

ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።

ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ

ለጥንቃቄ‼️በቀን 27/06/2016 የገጠመኝ ነው። ሌላውም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቢጠነቀቅ። እኔ የምሰራው ሽያጭ ነው በመኪና እየዞርኩኝ 7ሰአት አካባቢ ስልክ ተደወለልኝ ድርጅቱ በሰጠኝ ሲ...
08/03/2024

ለጥንቃቄ‼️
በቀን 27/06/2016 የገጠመኝ ነው። ሌላውም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቢጠነቀቅ። እኔ የምሰራው ሽያጭ ነው በመኪና እየዞርኩኝ 7ሰአት አካባቢ ስልክ ተደወለልኝ ድርጅቱ በሰጠኝ ሲም ካርድ ለይ ።የኛን ምርት እንደሚፈልግና ዋጋ ጠየቀኝ ።እኔም አንዱ ካርቶን 3160 ብር መሆኑን ስነግረው 60 ካርቶን እንደሚፈልግ አስቸኳይ አለኝ አሁን እንደማልችል ለማክሰኞ ጠዋት አልኩት የለውን ምርት አይቼ የምርት እጥረት ስላለብን አልኩት እሺ አለኝ። ትንሽ ቆይቶ አስቸኳይ እንደሆነና እንድተባበረው አለኝ።ያለኝን እንደጨረስኩና ለነገ ያለውን አይቼ 9ሰአት ስገባ ልደውል ብዬው ተለያየን።

9ሰአት ቢሮ ገብቼ እስቶክ ስጠይቅ ምርተ ትንሽ እንዳለ ሲነገኝ ደወልኩለትና ለነገ 20 ካርቶን ላቀብልህ አልኩት ዛሬ ካልሆነ በፒካፕ መኪና እንድልክለትና የፒካፑን እና ለኔም የሻይ እንደሚሰጠኝ ነገረኝ ።እንደማልችል እና ለጠዋት ስለው የድርጅቱን አካውን ስጠኝ ብር አስገብቼ የገባበትን ደረሰኝ ልላክልህ አለኝ። በጣም ስለፈጠነብኝ ብዛት ካለው ዋጋ እንኳን እንደሚቀንስ ሳይጠይቀኝ ይሄን ያህል ማዘዙ አጠራጠረኝ እና ወደራሴ አካውንት እንዲያስገባልኝ ነገርኩት እሺ አለ 10 ሰአት ላይ ደወለልኝ እና አስገብቻለሁ አለኝ በቴሌግራም እንዲልክልኝ የራሴን ስልክ ቁጥር ላኩለት ወዲያው ላከልኝ።

ስጠብቅ ከባንክ ቴክስት አይገባም በሞባይል አፕ ያስገባበትን ቁጥር አስገብቼ ስሞክረው አልገባም ።በማግስቱ ጠዋት ቼክ ሳረግ አልገባም የላከውን ደረሰኝ በደንብ ሳየው ኤዲት ተደርጎ የተሰራ ሀሰተኛ ደረሰኝ ነው እናንተም ደረሰኙን በደንብ እዩት 20*3160=63200 ብር ተርፌያለሁ እባካቹ ተጠንቀቁ መሳለሚያ አካባቢ ነበር ያዘዘኝ።

የደወለበተ ስልክ ቁጥር 0993512141 ቴሌግራም የላከበት ቁጥር 0940287854

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቅን ልቦች የሬዲዮ ፕሮግራም/Qin liboch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share