
15/11/2024
ከኤሌክትሪክ መስመር ላይ አልወርድም ያለው ወጣት
የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ የተሰቀለ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተመትረፏ ተሰምቷል።
ክስተቱ ያጋጠመው በደቡብ ኢትዮጵያ ሲሆን፣ አንድ ወጣት በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ቁንጭ ላይ ወጥቶ ይሰቀላል። በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት፣ በአካባቢው ሽማግሌዎችና የአስተዳደር አካላት ቢለመንም አሻፈረኝ ይላል።
ጉዳዩን የሰሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች አልወርድም ያለውን ወጣት ህይወት ለማትረፍ ኃይል ለማቋረጥ ተገደዋል ተብሏል። ባለሙያዎቹ ኃይል ካቋረጡ በኋላ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡
ወጣቱ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ፣ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
#ኢትዮጵያ