06/10/2026
በድጋሚ የተፖሰተ 😭
“የቤተሰቡን እንባ እናብስ፤ የአልአዛር አስክሬን በሀገሩ አፈር እንዲያርፍ እንተባበር!”
እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼርር አድርጉ እባካችሁ 😭🙏🙏🙏
ልብን የሚሰብር፣ እጅግ የሚያሳምም መርዶ ነው። ከተወለደበት፣ አድጎ ካደገበት የጨርቆስ ሰፈር የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ተስፋ ሰንቆ የተሰደደው ወንድማችን አልአዛር ታሪኩ ፤ በሰው ሀገር በፈረንሳይ በወጣትነቱ ህይወቱ አልፏል።ዛሬ አልአዛር የለም። ነገር ግን አሁንም በህይወት ያሉ፣ በሀዘን የተሰበሩ፣ የልጃቸውን አስክሬን እንኳን አይተው ለመሰናበት አቅም የሌላቸው ምስኪን ወላጆችና ቤተሰቦች አሉት።
========
የወንድማችን አስክሬን ወደ ሀገሩ ገብቶ በክብር እንዲያርፍ በአውሮፓ ያሉ ወገኖች ጥረት እየደረጉ ቢሆንም፤ አስክሬን ወደ ሀገር ለመመለስ የሚጠይቀው ወጪ ከአቅም በላይ ሆኗል።ይህ የጨርቆስ ልጆች ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊ ፈተና ነው!
ወንድማችን አልአዛር በሰው ሀገር ባይተዋር ሆኖ ቀርቶ እዚያው ሜዳ ላይ ሊቀበር አይገባም። ወላጅ እናቱ የልጃቸውን አስክሬን እንኳን ሳይስሙ "ልጄን አፈር ሳልምረው" ብለው የሚያለቅሱትን እናት እንባ የምናብስበት ሰዓት አሁን ነው።
========
በተለይ በውጭ ሀገር የምትኖሩ፣ በልጅነትና በሰፈር ፍቅር የምታምኑ የጨርቆስ ልጆች እንዲሁም ሩህሩህ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ይሄንን ሀዘን የራሳችሁ አድርጋችሁ እንድትነሱ በፈጣሪ ስም እንማጸናለን። ዛሬ የምናወጣው ጥቂት ዶላር ወይም ዩሮ ለአንድ እናት ትልቅ መጽናኛ፣ ለአንድ ወጣት ወንድማችን ደግሞ የመጨረሻ ክብር ነው። ቸል አንበል! ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ የምንችለውን በማበርከት የወንድማችን አስክሬን ወደ ሀገሩ እንዲገባ እናድርግ። የአልአዛርን ነፍስ በገነት ያኑርልን! ለወላጆቹና ለቤተሰቡ ጽናቱን ይስጥልን!
የውጪ ሃገር የባንክ አካውንት
[LULE KIROS]
34803303
Sort code
04-00-03
@ቢኒ ዘቂርቆስ