Awramba Times

Awramba Times Awramba Times is an online media outlet providing latest news and analysis about Ethiopia & the horn

13/07/2025

የሙሉ ቃለምልልሱን Link ኮመንት ላይ ይገኛል

ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋልን?----------አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ሰኔ 15 ቀን 2...
30/06/2025

ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋልን?
----------
አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ ድንገተኛ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው በሚኒስትርነት የሚመሩት ተቋም ዛሬ ይፋ አደረገ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳብራራው፣ አደጋው የደረሰው ከመደበኛ ስራቸው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው የሚገኝበት ካርል አደባባይ ላይ መሆኑን እና በእለቱ ሚኒስትሩ ወደ ሆስፒታል አምርተው በቂ የህክምና አገልግሎት አግኝተው አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዋዜማ የተባለው የበይነ መረብ ሚዲያ ባለፈው ቅዳሜ ባወጣው ዘገባ፣ ዶ/ር ካሳሁን አደጋው የደረሰባቸው፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ለሰኞ አጥቢያ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ ወደ ቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ፣ በአልኮል ተጽእኖ ስር ሆነው ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና በካርል አደባባይ ከቆመ ኤክስካቫተር ጋራ በመላተሙ እንደኾነ ገልጾ በኢትዮ-ጠቢብ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል (ICU) የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ መዘገቡ ይታወሳል።

ለዚህ ዘገባ ምላሽ በሚመስል መልኩ፣ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ዛሬው መግለጫው "ሁነቱን ለርካሽ ፖለቲካዊ ግብ ለመጠቀም ከአውድ ውጪ ባልተረጋገጠ መረጃና በአሉባልታ የሚናፈሰው የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባ የተሳሳተ ነው" በማለት ከበቂ የእረፍት ቆይታ በኋላ ሚኒስትሩ ወደ መደበኛ ስራቸው እንደሚመለሱ ይፋ አድርጓል።

--------
ዜናዎቻችንን በነዚህ ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ

ዩቲዩብ
https://youtube.com/?si=c-1VsIDf_R40Bp2A

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/awrambatimes

ትዊተር/ኤክስ
https://x.com/AwrambaTimes?t=YLACUGpSq3nLWhgltZ0myQ&s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=ZN-8x75B6o1Ako&_r=1

27/06/2025
ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ልዕሊ 1300 ተምሃሮ ሎሚ ኣምሪቑ-------ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ዝተምሃረ ሓይሊ ኣብ ምፍራይ ብዕቱብ እናሰርሐ መፂኡን ኣሎን ክብሉ ፕረዚደንት እቲ ዩኒቨርስቲ ገሊፆም ። ...
21/06/2025

ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ልዕሊ 1300 ተምሃሮ ሎሚ ኣምሪቑ
-------

ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ዝተምሃረ ሓይሊ ኣብ ምፍራይ ብዕቱብ እናሰርሐ መፂኡን ኣሎን ክብሉ ፕረዚደንት እቲ ዩኒቨርስቲ ገሊፆም ። ፕረዚደንቲ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ዶክተር ዛይድ ነጋሽ ነዚ ዝገለፁ እቲ ዩኒቨርስቲ ልዕሊ 1300 ተምሃሮ እንተመርቕ እዩ ።

ዶክተር ዛይድ ነጋሽ ኣተሓሒዞም ኣብቲ ዝተሳለጠ ስነ ስርዓት ምረቓ ከምዝበልዎ በዚ ዕለት ብቀደማይን ካልኣይን ድግሪ የመርቆም ካብ ዘሎ 1307 ተመረቕቲ ተምሃሮ እተን 461 ደቂ ኣንስትዮ እየን ።

ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ስርሑ ካብ ዝጅምር 2004 ዓ/ም ጀሚሩ ምስዞም በዚ ዕለት መበል ዓሰርተ ሓደ ዙር ዝምረቑ ዘለው ተምሃሮ ሓዊስካ፣ ትሸዓተ ሽሕ ደቂ ኣንስትዮ ዝርከበኦም ልዕሊ 27,000 ተምሃሮ ብዝተፈላለዩ ዓውዲታት ትምህርቲ ኣምሂሩ ከም ዘመረቐ ድማ ተዛሪቦም ።

ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ዋላ እኳ ብዘጋጠመና ጀነሳይዳዊ ኵናት ከቢድ ዕንወት እንተጋጠሞ ፣ ዝፅገን ፀጊኑን ዘለውዎ ሃፍቲታት ፀንቂቁ ብምጥቃምን ፅሬት ዘለዎ ትምህርቲ ይህብ ከም ዘሎ ድማ ኣረዲኦም ።

ኣብቲ ስነ ስርዓት ምረቓ ዝተረኸቡ ሓላፊ ቢሮ ትምህርቲ ትግራይ ዶክተር ኪሮስ ጉዑሽ ኣብ ዘመሓላለፍዎ መልእኽቲ ድማ ተመረቕቲ ኣብ ድሮ መዓልቲ ሰማእታት ይምረቑ ስለ ዘለው ሰማእታት ዝወደቕሉ ዕላማ ኣብ ዳርችኡ ክበፅሕ ብዝተምሃርሉ ዓውዲ ንህዝቦምን ዓዶምን ብቕንዕናን ተኣማንነትን ከገልግሉ ይግባእ ኢሎም ።

ኣብቲ ስነ ስርዓት ምረቓ ዝረኸብናዮም ተመረቕቲ ኣብ ዝሃቡና ርኢቶ ድማ ፣ ተማሂሮም ንኽምረቑ ዝተፈጠረሎም ዕድልን ኩነታት ሰላምን ዋጋ ተኸፊልዎ ስለ ዝተረኸበ ሰማእታት ዝወደቕሉ ዕላማ ንምግሃድ ክንሰርሕ ኢና ኢሎም ኣለው ።

©Dimtsi Weyane

21/06/2025

ሳምንቱ በታሪክ ውስጥ! የዛሬ 24 አመት በዛሬዋ ቀን!

"የተፈናቃዮቹ ጉዳይ በሰላም እልባት ካላገኘ የሚደረገውን ሁሉ እናደርጋለን እንጂ እጃችንን አጣጥፈን አናይም"አቶ አማኑኤል አሰፋየትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት
20/06/2025

"የተፈናቃዮቹ ጉዳይ በሰላም እልባት ካላገኘ የሚደረገውን ሁሉ እናደርጋለን እንጂ እጃችንን አጣጥፈን አናይም"

አቶ አማኑኤል አሰፋ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት

​​​​​​​​​​​​​​​​ ​​​​​​​​​​​ ​​​​​​​​​​​Ethiopia news | Ethiopian News | Tigray News | Eritrean News | Daily News | Getachew Reda | Tades...

ሁሉም የትግራይ መንግስታዊ ተቋማት ነገ ዝግ እንዲሆኑ ተወሰነ------አውራምባ ታይምስ (መቐለ) - በትግራይ ክልል ያሉ ሁሉም ቢሮዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለነገ አርብ 13/10/2017 ...
19/06/2025

ሁሉም የትግራይ መንግስታዊ ተቋማት ነገ ዝግ እንዲሆኑ ተወሰነ
------
አውራምባ ታይምስ (መቐለ) - በትግራይ ክልል ያሉ ሁሉም ቢሮዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለነገ አርብ 13/10/2017 ዓ.ም ዝግ እንዲሆኑና የተቋማቱ ሰራተኞች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ለተፈናቃይ ወገኖቻቸው ድምጽ እንዲሆኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ወሰነ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው "ፅላል ስቪል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ" በመባል የሚታወቀውና የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አላማ አድርጎ የሚሰራ ስቪክ ድርጅት ባቀረበው ጥያቄ ነው።

የድርጅቱን ጥያቄ የተቀበለው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ሁሉም የትግራይ ቢሮዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለነገ አርብ ዝግ እንዲሆኑና ሁሉም የክልሉ ነዋሪ "ይኣክል" (ወይም ደግሞ "በቃ") በሚል መሪ ቃል የተጠራውን ክልል አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተቀላቅሎ በተለያዩ መጠሊያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቹ ድምጽ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል።

ፅላል ስቪል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ በተባለ ስቪክ ተቋም ለነገ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለአለም አቀፍ መንግስታትና ተቋማት ብሄራዊ የሰላም ጥሪ የሚደረግበት እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
----------
ዜናዎቻችንን በነዚህ ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ

ዩቲዩብ
https://youtube.com/?si=c-1VsIDf_R40Bp2A

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/awrambatimes

ትዊተር/ኤክስ
https://x.com/AwrambaTimes?t=YLACUGpSq3nLWhgltZ0myQ&s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=ZN-8x75B6o1Ako&_r=1

18/06/2025

ሙሉእ ትሕዝቶ ናይቲ ቃለመሕትት ኣብ ንምክትታል ሊንክ ኣብ comment ይርከብ!

በትግራይ ጦርነት፣ የሻዕብያ ሰራዊት ትግራይ መውረሩን ለመጀመርያ ጊዜ ያጋለጠ ጋዜጠኛ ታሰረ--------አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የኢትዮጵያን ኢንሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወ...
10/06/2025

በትግራይ ጦርነት፣ የሻዕብያ ሰራዊት ትግራይ መውረሩን ለመጀመርያ ጊዜ ያጋለጠ ጋዜጠኛ ታሰረ
--------

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የኢትዮጵያን ኢንሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መታሰሩ ታወቀ።

ጋዜጠኛው በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሚሰራበት ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። ተቋሙ ይፋ ባደረገው የፕሬስ መግለጫ፣ ጋዜጠኛው በቀጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ሌሊቱን ሙሉ እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉንም ገልጿል።

ጋዜጠኛ ተስፋለም በትግራይ ልሂቃን ዘንድ የሚታወስበት አንድ ወሳኝ ሙያዊ ተግባርም አለ። እሱም በ2013ቱ የትግራይ ጦርነት ወቅት "የኤርትራ ሰራዊት በጦርነቱ አልተሳተፈም" ተብሎ በመሀል አገር ሚዲያዎች በሚካድበት ወቅት ያለምንም የጥበቃ ከለላ፣ አስተማማኝ ጸጥታ ወዳልነበረበት ክልል በጥር 2013 ዓ/ም በአካል ተጉዞ በሰራው ዘገባ የሻዕብያ ሰራዊት ትግራይ መግባቱንና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ እየፈጸመ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም ያሳወቀ ጋዜጠኛ ነው።

የሻዕቢያ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ገብቶ መጠነ ሰፊ ግፍ መፈጸሙን በርካታ የትግራይ ሚዲያዎች በወቅቱ ቢገልጹም ነባራዊ ሀቁን በአካል ተገኝቶ ያረጋገጠ ብቸኛው የመሀል አገር ጋዜጠኛ የኢትዮጵያን ኢንሳይደሩ ተስፋለም ወልደየስ እንደነበረ ብዙዎች በአድናቆት ያስታውሱታል። በብዙዎች ዘንድ ለሙያው ታማኝ እንደሆነ የሚነገርለት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ተወስኖለት የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እስካሁን ከእስር እንዳልተፈታ የሚሰራበት የሚዲያ ተቋም በሰጠው የፕሬስ መግለጫ አሳውቋል።

-------------
ዜናዎቻችንን በነዚህ ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ

ዩቲዩብ
https://youtube.com/?si=c-1VsIDf_R40Bp2A

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/awrambatimes

ትዊተር/ኤክስ
https://x.com/AwrambaTimes?t=YLACUGpSq3nLWhgltZ0myQ&s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=ZN-8x75B6o1Ako&_r=1

የምክክር ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ለመንቀሳቀስ ከፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ ጋር መነጋገሩን ገለጸ ---------አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - በትግራይ ክልል አጀንዳን ለማሰባሰብ የሚያስችል...
10/06/2025

የምክክር ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ለመንቀሳቀስ ከፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ ጋር መነጋገሩን ገለጸ
---------

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - በትግራይ ክልል አጀንዳን ለማሰባሰብ የሚያስችል የምክክር ምዕራፍ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ማቀዱን፣ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ ኮሚሽናቸው እስከ ሐምሌ 30፣ 2017 ዓ.ም ድረስ በትግራይ ክልል የወረዳና የክልል ተሳታፊዎች ምርጫና የአጀንዳ ማሰባሰብ ለማካሄድ እንዲችል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደና ከሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ንግግር ማድረጉን ገልጸዋል።

ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተካሂዶ በተጠናቀቀው የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት የአጀንዳ ማሰባብሰብ የምክክር ምዕራፍ ወቅት፣ የኮሚሽኑ አመራሮች ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ገንቢና አሳታፊ ውይይት አድርገዋል ብለዋል። "የትግራይ ክልልን ሳይዙ አሳታፊና አካታች አገራዊ ውይይት ማድረግ አይቻልም" ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ፣ በውይይቱ ወቅት የኮሚሽኑን ተልእኮ በተመለከተ መተማመን ለመፍጠር ከአመራሩ ጋር አስቀድሞ መገናኘት እንደሚያስፈልግ፣ ህዝቡም ለምክክሩ ዝግጁ እንዲሆን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ዝርዝር ውይይቶች መደረጋቸውን አብራርተዋል።

ከ15 ቀናት በፊት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ ሲደረግ ህወሓትም አብሮ እንደተጋበዘ በዚሁ ቃለምልልሳቸው ያወሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ሆኖም ግን ከህወሓት የተሰጣቸው ምላሽ "ከምክክሩ በፊት ስለፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም መነጋገር አስፈላጊ ነው"
የሚል እንደሆነ አስታውሰዋል።

----
ዜናዎቻችንን በነዚህ ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ

ዩቲዩብ
https://youtube.com/?si=c-1VsIDf_R40Bp2A

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/awrambatimes

ትዊተር/ኤክስ
https://x.com/AwrambaTimes?t=YLACUGpSq3nLWhgltZ0myQ&s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=ZN-8x75B6o1Ako&_r=1

"ግማሹን ከወሰድክ በቂ ነው፤ ቀሪውን ግማሽ ግን መልስላት"አቶ መለስ ዜናዊ--------ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከቀድሞ ባሏ የፍቺ ውዝግብ ጋር ተያይዞ የቀድሞ ባሏ ንብረቷን በሙሉ ወስዶ ...
09/06/2025

"ግማሹን ከወሰድክ በቂ ነው፤ ቀሪውን ግማሽ ግን መልስላት"

አቶ መለስ ዜናዊ
--------
ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከቀድሞ ባሏ የፍቺ ውዝግብ ጋር ተያይዞ የቀድሞ ባሏ ንብረቷን በሙሉ ወስዶ ባዶ አስቀራት። ደራርቱም ችግር ላይ ወደቀች። ደራርቱ ግን "መለስ ዜናዊ ድረስልኝ" አላለችም። መለስ ግን ስለጉዳዩ ቀድሞ ሰምቶ ነበርና ደወለላት። "መለስ ነኝ ቢሮ እፈልግሻለሁ አሁኑኑ ነይ" አላት። የገጠማትን ችግር በዝርዝር እንድትነግረውም ጠየቃት። በጨዋነት የምትታወቀው ደራርቱ ግን "ባሌ በደለኝ" ብላ መናገር አሳፍሯተ ከመናገር ተቆጠበች። ሆኖም መለስ ስለጉዳዩ ከሳምንት በፊት እንደሰማና ዝርዝሩን እንድታስረዳው ጠየቃት። የሰማውን እውነት በዝርዝር ደገመችለት።

ከዛም ለደራርቱ ባል ተደወለ። "መለስ ነኝ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ነኝ። ባሏ በድንጋጤ ስልኩን ጣለ። ስልኩ በድጋሜ ተደወለ። መለስ ነኝ ተረጋጋ። ከደራርቱ ጋራ ስለገባችሁበት ውዝግብ እንድንነጋገር ፈልጌ ነው፤ በሰላም ተወያይታችሁ ብትፈቱት ይሻላል። ዞሮ ዞሮ በፍርድ ቤትም 50/50 ስለሚደርሳችሁ ግማሹን ብትመልስላት ጥሩ ነው። ቢሮ ና እፈልገሃለሁ። እንዴት መምጣት እንዳለብህ ሰው እልክለሃለሁ።"

የደራርቱ ባል "አረ ሁሉንም ትውሰድ: አሁኑኑ እመለስላታለሁ። እኔኮ ተናድጄ ስለተጣላን ብዬ እንጂ..."

መለስ ዜናዊ "አይ ሙሉ አይሆንም። ግማሹ ላንተም ይገባሃል። ግማሹን ግን መልስላት። ያላንተ ድጋፍም ይሀ አይመጣም ነበር። ለማንኛውም ቢሮ ና: እንወያይበታለን" ተባለ። ያለ አንዲት መኪና ሁሉንም ንብረት መለሰልኝ። መለስ ዜናዊ ሁሌም ለወገኑ ለህዝቡ የኖረ ነው"

ደራርቱ ቱሉ የመለስ ዜናዊ ቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለETV የተናገረችው

-----
ዜናዎቻችንን በነዚህ ተጨማሪ አማራጮች ይከታተሉ

ዩቲዩብ
https://youtube.com/?si=c-1VsIDf_R40Bp2A

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/awrambatimes

ትዊተር/ኤክስ
https://x.com/AwrambaTimes?t=YLACUGpSq3nLWhgltZ0myQ&s=09

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awramba Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Awramba Times:

Share