ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital ሓሪ ነገን ማያ!

18/09/2025

የዛሬ አመት ክስተት የነበረችው ሳሌሚያ ሰሞን አፊማ አዋርድ እጩ መሆኗ ታውቋል።

እሷን ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ እየመረጧችዋት

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ! እንድትቀላቀሉ ይሁን።

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” ብለን የሰየምነውን ዘመቻ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለን። በዚህ ዘመቻ እስከ 1500 የሚሆኑ መጽሐፍትን በሁሉም የጉራጌ አካባቢ ትምህርት ቤቶች እና ቤተ-መጽሐፍት ለማዳረስ ርብርብ እናደርጋለን።

አቅማችሁ የቻለውን ያህል መጸሐፍት በመግዛት፣ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን በማስተባበር ዘመቻው እንዲሳካ ቀና ትብብር እንደምታደርጉልን አንጠራጠርም።

ለማንኛውም መረጃ

Abeyu Wolde (0912241972).. ...... .................(0913011764)

መጽሐፍቱን ለመግዛት

1000368668153 (CBE)
23661128 Abyssinia Bank
0912241972 Tellbirr
7000015527884 Nib Bank

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ!አማረች ጠንክር ከእምብር ተቀላቅላናለች።እናንተስ?? “ጉራጊኛን ለልጆቻችን” ብለን የሰየምነውን ዘመቻ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለ...
18/09/2025

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ!
አማረች ጠንክር ከእምብር ተቀላቅላናለች።

እናንተስ??

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” ብለን የሰየምነውን ዘመቻ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለን። በዚህ ዘመቻ እስከ 1500 የሚሆኑ መጽሐፍትን በሁሉም የጉራጌ አካባቢ ትምህርት ቤቶች እና ቤተ-መጽሐፍት ለማዳረስ ርብርብ እናደርጋለን።

አቅማችሁ የቻለውን ያህል መጸሐፍት በመግዛት፣ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን በማስተባበር ዘመቻው እንዲሳካ ቀና ትብብር እንደምታደርጉልን አንጠራጠርም።

በተለይም ተደራሽነት እና ተደማጭነት ያላችሁ ወገኖቻችን ዘመቻው እንዲሳካ ድጋፍ እንድታደርጉልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን!

ለማንኛውም መረጃ

Abeyu Wolde (0912241972).. ...... .................(0913011764)

መጽሐፍቱን ለመግዛት

1000368668153 (CBE)
23661128 Abyssinia Bank
0912241972 Tellbirr
7000015527884 Nib Bank

አጠቃላይ ንቅናቄውን በተመለከተ መረጃዎች በተከታታይ የምናደርስ ይሆናል። ስርጭቱም በተመለከተ የገዛችሁትን መጽሐፍ ለእራሳችሁ አለያም ላሰባችሁት ቦታ በክብር እናደርሳለን!

እስካሁን "ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ! የተቀላቀሉ ቤተሰቦች።እናንተስ???09130117640912241972
18/09/2025

እስካሁን "ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ! የተቀላቀሉ ቤተሰቦች።

እናንተስ???

0913011764
0912241972

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ!በተለያየ መንገድ እንደሚገለፀው ጉራጊኛ ቋንቋ ስርዓታዊ ስብራት ገጥሞታል። የተናጋሪው ቁጥር እየቀነሰ ነው። በቋንቋው የተፃፉ መጽሐፍት ቁጥር ...
18/09/2025

“ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የመጽሐፍት ስርጭት ዘመቻ!

በተለያየ መንገድ እንደሚገለፀው ጉራጊኛ ቋንቋ ስርዓታዊ ስብራት ገጥሞታል። የተናጋሪው ቁጥር እየቀነሰ ነው። በቋንቋው የተፃፉ መጽሐፍት ቁጥር ጥቂት ነው። ቋንቋው የሚዲያ ቋንቋ መሆን አልቻለም።

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አካላት ይህንን ችግር ለመፍታት የተለያየ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል።

እኛም ይህንን ጥረት ለማገዝ “ጉራጊኛን ለልጆቻችን” የሚል ዘመቻ ጀምረናል። በዚህ ዘመቻ “የጫሙት ሽካ” እና “አገኪ” የተሰኙ ልቦለድ መጽሐፍት በጉራጌ አካባቢ በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ቤተ-መጻሕፍት ለማዳረስ ጥረት እናደርጋለን።

እነዚህ መጽሐፍት ወደ ማህበረሰቡ በተለይም ወደ ታዳጊዎች በአግባቡ መዳረስ ቢችሉ ልጆች አዳዲስ ቃላትን እንዲለማመዱ፣ ሀሳባቸውን በፅሁፍ መግለፅ እንዲለማመዱ፣ በአጠቃላይ በጉራጊኛ አጠቃቀም ላይ ዓይነተኛ መሻሻል እንዲመጣ ያግዛሉ ብለን ከልብ እናምናለን።

መጻሕፍቱን ለራሳችሁም ሆነ ለልጆቻችሁ ብትሸምቱ ታተርፉበታላችሁ ብለን እናምናለን። በገጠር ለሚገኙ ቤተ-መጻሕፍት እና ትምህርት ቤቶች በስጦታ መልክ ብታበረክቱ ለቋንቋ ልማቱ ቀጥተኛ ድጋፍ ታደርጋላችሁ። ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን ትወጣላችሁ! ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች እንዲበረክቱ ታግዛላችሁ! ታዳጊዎች በጉራጊኛ ቋንቋ እና በጉራጌ ስነ-ነልቦና እንዲያድጉ ታደርጋላችሁ!

ሐሳባችን ከዚህ ዘመቻ የገንዘብ ትርፍ ማግኘት አይደለም። ህፃናትና ልጆችገና ከማለዳው ከቋንቋቸው ጋር እንዲለማመዱ የሚያግዙ መጽሐፍት በአጠገባቸው እንዲኖራቸው በማሰብ እንጂ። ዳጎስ ያለ ገጽ ያላቸው እነዚህ መጽሐፍት በ600 ብር የመሸጫ ዋጋ የቀረቡት ማትረፍን ታሳቢ አድርጎ እንዳልሆነ የወቅቱን የመጽሐፍት ህትመት ዋጋ የሚያውቁ ይረዱታል ብለን እናምናለን። መጽሐፍቱን ስናሳትምም ሆነ ይህንን ዘመቻ ስነጀምር ዓላማችን በቋንቋው እድገት ላይ የራሳችን ጠጠር መውርወር ብቻ ነው።

በመሆኑም “ጉራጊኛን ለልጆቻችን” ብለን የሰየምነውን ዘመቻ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለን። በዚህ ዘመቻ እስከ 1500 የሚሆኑ መጽሐፍትን በሁሉም የጉራጌ አካባቢ ትምህርት ቤቶች እና ቤተ-መጽሐፍት ለማዳረስ ርብርብ እናደርጋለን። አቅማችሁ የቻለውን ያህል መጸሐፍት በመግዛት፣ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን በማስተባበር ዘመቻው እንዲሳካ ቀና ትብብር እንደምታደርጉልን አንጠራጠርም። በተለይም ተደራሽነት እና ተደማጭነት ያላችሁ ወገኖቻችን ዘመቻው እንዲሳካ ድጋፍ እንድታደርጉልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን!

ለማንኛውም መረጃ

Abeyu Wolde (0912241972)
መጽሐፍቱን ለመግዛት

1000368668153 (CBE)
23661128 Abyssinia Bank
0912241972 Tellbirr
7000015527884 Nib Bank

አጠቃላይ ንቅናቄውን በተመለከተ መረጃዎች በተከታታይ የምናደርስ ይሆናል። ስርጭቱም በተመለከተ የገዛችሁትን መጽሐፍ ለእራሳችሁ አለያም ላሰባችሁት ቦታ በክብር እናደርሳለን!

ኢትዮጵያ ድምዳ ድራርየርቅ ገን ቡላቃ ምስርኣጋት ያነን ሙራ ፈረስሕዳሴየንዳው ገን ያረግስጃድ  በበሮት በደም በደም የትከበረየዲና ኣሙር ተርቅ ተርቅ የሰፐረዝቧረንዳ የሕር ይፍቴ የትኃጨረይሕር...
18/09/2025

ኢትዮጵያ ድምዳ ድራር
የርቅ ገን ቡላቃ ምስር
ኣጋት ያነን ሙራ ፈረስ
ሕዳሴየንዳው ገን ያረግስ

ጃድ በበሮት በደም በደም የትከበረ
የዲና ኣሙር ተርቅ ተርቅ የሰፐረ
ዝቧረንዳ የሕር ይፍቴ የትኃጨረ
ይሕርሸ ኤያት ሕዳሴው ጨት የሐረ ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

#ሕህዳስየንዳድምጻዊ ፦ጌቱ ደግአርጋቸው ጉራጊኛ ግጥም፦ ወንድሙ ብሩዜማ፦ ስዩም አባተ ሀያቱ አብራር---------------------------------የሓሪ ዲጂታል የሚድያ አማራጮችን ይተዋወቁ ሓሪ ዲጂታል፡- በተ.....

 #ኢትዮጵያ በ  #ሱዳን እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ76,000 በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀኢትዮጵያ በሱዳን እየተካሄደ የሚገኘው...
18/09/2025

#ኢትዮጵያ በ #ሱዳን እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ76,000 በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በሱዳን እየተካሄደ የሚገኘውን ግጭት በመሸሽ ከቀያቸው የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን መቀበሏን ቀጥላለች ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ስደተኞች መካከልም የሱዳን ዜጎች፣ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ከለላን የሚሹ ሌሎች ሰዎች ይገኙበታል ብሏል።

ኮሚሽኑ "ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው የስደተኞች እንቅስቃሴ" በሚል ትናንት ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርቱ በሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰበት ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም አንስቶ እስከ ነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 76,052 ዓለም አቀፍ ከለላ የሚያስፈልጋቸው ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ገልጿል።

ሪፖርቱ አክሎም፣ በ2017 ዓ.ም ብቻ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች ቁጥር 8,268 መድረሱን ጠቁሟል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ገብተዋል ከተባሉ 76,052 ስደተኞች መሀከልም 45,118 ሱዳናውያን ሲሆኑ፣ 20,226 ኢትዮጵያውያን፣ 8,284 ኤርትራውያን እና 2,424 የሚሆኑት ደግሞ የሌሎች ሀገራት ዜጎች ናቸው ተብሏል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት (RRS) ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ባሉ የመግቢያ ቦታዎች ላይ አዲስ የሚገቡ ስደተኞችን የማጣራትና የመመዝገብ ሥራ መቀጠሉም ተመላክቷል።

አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

18/09/2025

I got over 10,500 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

ዛሬም  63 በመቶው ነጋዴ በየዓመቱ ግብሩን በአግባቡ አይከፍልም -ገንዘብ ሚኒስቴርገንዘብ ሚኒስቴር አስጠናሁት ባለው ጥናት 63 በመቶው ነጋዴ ዛሬም በየዓመቱ ግብሩን በአግባቡ አይከፍልም ተብ...
17/09/2025

ዛሬም 63 በመቶው ነጋዴ በየዓመቱ ግብሩን በአግባቡ አይከፍልም -ገንዘብ ሚኒስቴር

ገንዘብ ሚኒስቴር አስጠናሁት ባለው ጥናት 63 በመቶው ነጋዴ ዛሬም በየዓመቱ ግብሩን በአግባቡ አይከፍልም ተብሏል፡፡

ኮንትሮባንድ ሌላውም ችግር በገበያ በስፋት ይታያል፡፡
የተመሳቀለውን የገበያ ስርዓት ለማስተካከል በየጊዜው ወሳኝ የታክስ ፖሊሲ ማሻሻያን ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል።

በተያያዘም ግብሩን በትክክል የሚቆርጠው የተከበረው ግብር ከፋይ ከፍተኛ ጫና እንዳይደረግበት እና ከግዙፍ ስራ ቢዝነስ ኢኮኖሚ እንዳይወጣ ሊጠበቅ ይገባዋል ይባላል።

ሸገር ሬድዮ

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

ከአባይ እና ኢትዮጵያ ቀድሞ የተፈጠረው ማን ነው?ሓሪ ዲጂታል Hari Digital
17/09/2025

ከአባይ እና ኢትዮጵያ ቀድሞ የተፈጠረው ማን ነው?

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

የሓሪ ዲጂታል የሚድያ አማራጮችን ይተዋወቁ ሓሪ ዲጂታል፡- በተለያዩ የሚድያና ሚዲያ ነክ ዘርፎች ማለትም ሓሪ ዜና ትንታኔ፣ ሓሪ ፖድካትን ጨምሮ በዲጂታል ሚዲያ የሚሠራጩ የተለያዩ ይዘቶ...

ለምስክርነት የቆየች ህይወትበዮድ አቢሲኒያ ባለቤት የተዘጋጀው "ለምስክርነት የቆየች ህይወት" መጽሐፍ ለአንባቢያን ልትበቃ ነው።የአቶ ትዕዛዙ ከልጅነት እስከዛሬ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ...
17/09/2025

ለምስክርነት የቆየች ህይወት

በዮድ አቢሲኒያ ባለቤት የተዘጋጀው "ለምስክርነት የቆየች ህይወት" መጽሐፍ ለአንባቢያን ልትበቃ ነው።

የአቶ ትዕዛዙ ከልጅነት እስከዛሬ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ እና ታሪካቸው የያዘ መፅሐፍ ነው።

“ለምስክርነት የቆየች ህይወት" በሚል ርዕስ የተሰናዳው ይህ መፅሐፍ የህትመትና ሌሎችም ወጪዎች ጨምሮ ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

"ለምስክርነት የቆየች ህይወት" መጽሐፍ ለመጀመርያ ጊዜ 5ሺ ቅጅ መታተሙ የተገለጸ ሲሆን የዚህ መጽሐፍ ሽያጭ ሙሉ ገቢው ለተመረጡ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይውላል ተብሏል።

ድርጅቶቹም መቄዶንያ ፣ ሜሪጆይ ፣ ቶራ የህፃናት ማሳደጊያ ፣ ሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ የወደቁትን እናንሳ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ናቸው።

መጽሐፉ የፊታችን መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ/ም ይመረቃል ተብሏል።

በቀኝ አዝማች ትዕዛዙ ህይወት ዙርያ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት የተጻፈው ወጣቶች፣ እየታተሩ ያሉ ሰዎች የትኛውም ችግር በሚያጋጥማቸው እንዴት መቋቋም ይችላሉ ችግር እንዴት ማለፍ ይችላሉ የሚለውን የማስተማር ነው ብለዋል።

ዮድ አቢሲኒያ በየአመቱ የሚያከብረው የዘንድሮው"መስቀረንዳ በቃያንዳ" ፕሮግራም እንዲህ አይነት የበጎ አድራጎት ስራ የሚከናወንበት ይሆናል ብሏል።

ቀደም ሲል እንደምናደርገው የዓመቱን 360 ቀናት ለኢትዮጵያ ሀገሬ 4 ቀናት ለበጎ አድራጎት ተግባራት ሲውል ፤ 365 ኛውን ቀን ደግሞ ዕድገት ያስተዋውቃል።

በመሆኑም ከቋሚ ደንበኞቻችን ፣ ከአጋሮቻችንና ከባለድርሻዎቻችን ጋር ከዚህ የተዘጋጀው 15ኛው የጉራጌ መስቀል በዓል እና የደንበኞች ቀን የፊታችን እሁድ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል ነው የተባለው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ ...
17/09/2025

ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ የሞተ ነው አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት “የመደመር መንግሥት” መጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ ሰላም አስቀድማ ድህነትን ትፋለማለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ መውጫ መግቢያ በሯን ታበጃለች ይህ ጉዳይ የማይቀር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ይህ ሲሳካ ምናልባትም እኛ ላንኖር እንችላለን ነገር ግን ልጆቻችን በተዘጋ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ድሃ ሳይሆኑ የታሪክ ሰሪ ልጆች ሆነው ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ሀገራትን የሚያግዙ ይሆናሉ ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጦርነት ያስፈልጋል ብላ እንደማታምን እንዲሁም ጥያቄዋን በሰላማዊ መንገድ ስታቀርብ እየደቆየች ገልጸው÷ ቀይ ባህርን መልሶ ለመጠየቅ የሚሰጋ እና የሚጠራጠር ትውልድ ሊኖር አይገባም ብለዋል።

ኢትዮጵያን ቆልፎ ድሃ ካደረጋት የባህር በር ችግር መገላገል አለባት ብለን እናምናለን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር በሰላማዊ መንገድ ለመምከር ፈቃደኞች ሲሉም አስገንዝበዋል።

ነገ ላይ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ወንድም ሀገራትን የምታግዝ መሆን አለባት፤ ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ መንግስት ያስፈልጋል ያሉት ዐቢይ (ዶ/ር)÷ መንግስት ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ማወቅ አለበት ብለዋል።

FBC

ሓሪ ዲጂታል Hari Digital

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በ2007 ዓ.ም የዓለም ቲያትር ቀን በተከበረበት ወቅት የቀረበ።
16/09/2025

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በ2007 ዓ.ም የዓለም ቲያትር ቀን በተከበረበት ወቅት የቀረበ።

የሓሪ ዲጂታል የሚድያ አማራጮችን ይተዋወቁ ሓሪ ዲጂታል፡- በተለያዩ የሚድያና ሚዲያ ነክ ዘርፎች ማለትም ሓሪ ዜና ትንታኔ፣ ሓሪ ፖድካትን ጨምሮ በዲጂታል ሚዲያ የሚሠራጩ የተለያዩ ይዘቶ...

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሓሪ ዲጂታል Hari Digital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share