Astereyo Media Service - አስተርእዮ ሚዲያ አገልግሎት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Astereyo Media Service - አስተርእዮ ሚዲያ አገልግሎት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Astereyo Media Service - አስተርእዮ ሚዲያ አገልግሎት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወቅታዊ ሁነቶች፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ቅርሶች፤ እንዲሁም በምዕመናን ህይወት ላይ ያተኮሩ ዜናዎች፣ ዘገባዎችና ትንታኔዎች የሚቀርቡበት

19/01/2025

#ፋና #ኢትዮጵያ

18/01/2025
30/09/2024

✝️የመስቀሉ ማረፊያ መስቀለኛዋ ግሸን ደብረ ከርቤ✝️
ከ ክብረ በዓላት - ሃይማኖትና ባህል መጽሐፍ

⛪መስከረም 21 በግሸን ደብረ ከርቤ በከፍተኛ ሥነ ሥርዐት የሚከበር የገዳሙ ትልቁ በዓል ሲሆን በሁለት ምክንያት ይከበራል። አንደኛው የብዙኃን ማርያም እየተባለ ይጠራል፤ 318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በ325 ዓ.ም በሃይማኖት ምክንያት ከቅርብም ከሩቅም በኒቂያ ተሰባስበው አርዮስን አውግዘው ሃይማኖት ያጸኑበት ነው። ሁለተኛው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በአምባሰል ተራራ ግሸን ደብረ ከርቤ ቤተ መቅደስ ተሰርቶለት የተቀመጠበት ነው።

✝️የጌታን ግማደ መስቀል ስናር ላይ ከግብጾች የተቀበሉት ዐፄ ዳዊት እረፍተ ሞት ሲገታቸው በአባታቸው እግር የተተኩት ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብም እንደአባታቸው “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል” የሚል ራዕይ ታይቷቸው ግማደ መስቀሉን በ1443 ዓ.ም ከስናር ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት በደብረ ብርሃን፣ በሸዋ ደርሄ ማርያም፣ በጨጨሆ፣ በአንኮበር፣ በመናገሻ አምባና በእንጦጦ ለማስቀመጥ ቢሞክሩም ፈቃዱ ስላልሆነ አልተሳካላቸውም ነበር። በመጨረሻም በየአድባራቱ አዙረው ምድረ ኢትዮጵያን ካስባረኩ በኋላ መልክዓ ምድሩ የቀራንዮ አምሳል የሆነ የመስቀል ቅርጽ ያለው ቦታ በፍለጋ አስጠንተው የጌታ ቅዱስ ፈቃዱ ሲሆን መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም ግሼ አምባ ደብረ ከርቤ በሚባለው መስቀለኛ ሥፍራ አሁን የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ከታነጸበት ላይ አኑረውታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም መስከረም 21 ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በታላቅ በዓለ ንግሥ ይከብራል።

⛪የመስቀሉ ማረፊያ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም በደቡብ ወሎ አምባሰል ግሸን ተራራ አናት ላይ የምትገኝ አንድ መግቢያ ብቻ ያላት ናት። ግሸን በተለያዩ ዘመናት የተለያዩ መጠሪያ ስሞች እንደነበራት የታሪክ ድርሳናት ይነግሩናል።
✓ ከዐፄ ድልነዓድ ዘመን(866 ዓ.ም) እስከ 11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአሁኑ ስያሜ በደብረ ከርቤ ትታወቅ ነበር።
✓ በ11ኛው ክፍለ ዘመን ዐፄ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍለው እግዚአብሔር አብ የተሰኘ ቤተ ክርስቲያን በዚሁ ቦታ ሲያሰሩ ደብረ እግዚአብሔር በሚል ስም ታወቀች፤ ብዙ ሳይቆይ ግን ደብረ ነገሥት ተባለች።
✓ በ1446 ዓ.ም ግማደ መስቀሉ በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በዚህ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ ነገሥት መባሏ ቀርቶ ደብረ ከርቤ በሚለው ስም በድጋሚ ተጠራች። ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው እየገሰገስገሱ ስለመጡ በግዕዙ “ገሰ” ወይም በአማርኛው “ገሰገሰ” የሚለው ቃል ለቦታው ስያሜ ሆነ። በዘመናት ሂደት 'ገሰ' ወደ ግሼ ተለውጦ ግሸን ተብሎ ተጠራ።

እንኳን አደረሳችሁ!

መጽሐፉን ለመግዛት በ+251 930 10 92 82 ይደውሉ

11/07/2024

✝️ብርሃናት ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ✝️ ሐምሌ አቦ
ከ ክብረ በዓላት - ሃይማኖትና ባህል መጽሐፍ

🌿ሐምሌ ፭ ብርሃናተ አለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ዕለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን በማስፋፋቱ ምክንያት ታሰሮ ሞት ተፈርዶበት እንገቱን በስለት ተስይፎ ስማዕትነትን ተቀብሏል። ቅዱስ ጴጥሮስም ክርስትናን በመስበኩ ተይዞ ሊሰቅሉት ሲሉ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ስቀሉኝ ብሎ ተዘቅዝቆ በመሰቀል በሮም አደባባይ ሰማዕትነትን ተቀብሏል።

💒የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያቱን የቅዱስ ጴጥሮስን እና የቅዱስ ጳውሎስን ሰማዕትነት በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን በታላቅ ሥነ ሥርዐት ትዘክረዋለች። በዚህች ዕለት ተጋድሏቸውን የፈጸሙት እነዚህ ሁለት ቅዱሳን አባቶች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዕማድ ናቸው፤ በመሠረትነት ባጸኗት ቤተ ክርስቲያን ያላቸው ክብርም ላቅ ያለ ነው። ይህም የሆነው ለቤተ ክርስቲያን በፈጸሙት አገልግሎትና በዚህም በተቀበሉት ሰማዕትነት ነው።

✝️ሐምሌ አቦ
ሐምሌ ፭ የሐዋርያቱ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የዕረፍት በዓል ቢሆንም ቀኑ የጻድቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል በመሆኑ በአብዛኛው በልማድ ሐምሌ አቦ ተብሎ ታወቃል፤ ጉቡኣን አቦ እየተባለም የጠራል። ዕለቱ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ከመሠማራታቸው በፊት መንፈሳዊ ተልዕኳቸው እንዲቀናላቸው የጾሙትን ጾም በመፈጸም ዕጣ ተጣጥለው ሀገረ ስብከታቸውን የተከፋፈሉበትም ነው። ወሩ የሐዋርያት በዓል የሚበዛበት በመሆኑም በየአካባቢው በተለያዩ ቀናት ሐዋርያ እየተባለ ይከበራል።

🌿ሐዋርያት በዚህ ዓለም ሁሉን ትተው ድሆች ስለነበሩ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ይህንን ጾም ጾመው ሲፈጽሙ የፈሰኩት በተልባና በኑግ ስለነበር በዚህ ምሳሌ ሐዋርያትን አብነት አድርጎ የሚጾመው ጾመ ሐዋርያት በሚፈታበት ቀን፥ በጎንደርና አካባቢው እሪጦ የሚባል እንደ አነባበሮ የሚዘጋጅ እንጀራው ከተጋገረ በኋላ ተልባ ወይም ኑግ ተቀብቶ እንደገና ተደርቦበት ይበስልና ይበላል። ይህን የበላ ልጅ መብረቅ አይመታውም፥ የክረምቱ ብርድም አይጎዳውም ተብሎ ይታመናል። በደቡብ ጎንደር አካባቢ በዓሉ የጾም መፍቻ በመሆኑ አቅሙ የቻለ በእርድ ያከብረዋል። በኑግ የተዘጋጀ ትኩስ የጤፍ ቂጣም የዕለቱ ዋነኛ ምግብ ነው።

💒ከፍቾዎች ወርኃ ሐምሌን ሁነቱን በማሰብ አውራቲ ይሉታል፤ የሐዋርያት ወር ለማለት ነው።
ሐምሌ 5 በተጨማሪም የ72ቱ አርድእት የመታሰቢያ በዓላቸው ነው።

የሐዋርያቱ በረከት ይደርብን!
መጽሐፉን ለማግኘት በ+251 935 35 09 00 ይደውሉ

07/01/2024

መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

ሰላምን ባጣችው ቤተልሔም የሰላሙ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አልተከበረም🎄✝️🌟         🎄✝️🌟         🎄✝️🌟የጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ቦታ በሆ...
25/12/2023

ሰላምን ባጣችው ቤተልሔም የሰላሙ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አልተከበረም
🎄✝️🌟 🎄✝️🌟 🎄✝️🌟

የጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ቦታ በሆነችው ቤቴልሔም የዘንድሮው ፈረንጆቹ የገና በዓል በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ምክንያት ሳይከበር መቅረቱን ምዕራባውያን የሚዲያ ተቋማት ከቦታው ካጋሩት ምስሎች ለመረዳት ተችሏል።

የጌታ የትውልድ ከተማዋ ቤቴልሄም የለመደችው የአከባበር ሥነ ሥርዐት ቀርቶባት፤ የቱሪስቶች ወከባና ድምቀት ርቋት በምዕራባውያኑ የጌታ ልደት ቀን ጭርታ ወርሷት ለመዋል ተገዳለች።

የዘንድሮ የገና አከባበር በጦርነቱ ምክንያት የተሰረዘ ሲሆን በተለምዶ መንገር ተብሎ የሚጠራውን አደባባይ የሚሞሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችና ምዕመናን አልተገኙም። ከተማዋ ልጆችና የገና አባት ዝር ሳይሉባት የለመደችውን የበዓል ሁካታና ደስታ ተነፍጋ ባዶ ሆናለች።
በፍልስጤሟ ዌስት ባንክ የቤተልሔም ከተማ ነዋሪ የሆነችው ማዴሊን በዚህ ዓመት ምንም ዓይነት በዓል እንደሌለ ተናግራለች። በመኃል አደባባይ ይቆም የነበረው የገና ዛፍ እንዳልተረሠራና ዝማሬዎች እንደማይደመጡ እንዲሁም የተለመደው ደማቁ የገና ገበያ አለመኖሩንም ገልጻለች።

ባልተለመደ ሁኔታ ባዶ በሆነችው የክርስቶስ ልደት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ የሆኑት አባ ኢሳ ታልጂያ እንደተናገሩት "በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለ12 ዓመታት ካህን ሆኜ አገልግያለሁ፤ የተወለድኩት በቤተልሔም ነው ከተማ ነው፤ እንደዚህ ዓይነት መቀዛቀዝ አይቼ አላውቅም" ብለዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ እንኳን እንዲህ ዓይነት ነገር እንዳልገጠማቸው ይገለጹት አባ ኢሳ በጋዛ ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች ያሉበት ሁኔታ በዓሉን ለማክበር አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።

በቤተልሔም በፍርስራሽ በተሞሉ ሥፍራዎች ያሉ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የሚያስመለክቱ ዝማሬዎችን በመዘመር ሰላም ለህፃናት እያሉ ጥሪ ሲያደርጉና የቤተክርስቲያን ደወል ሲደወል መስማታቸውን በቦታው የሚገኙ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በቤተልሔም በሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ባህላዊውን ጥቁር እና ነጭ የፍልስጤም ማህበረሰብ ልብስ ለብሰው የተገኙ ሲሆን "ይህ በጣም የሚያሳዝን የገና በዓል ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ!

© Mirror

የ # ክብረ በዓላት - ሃይማኖትና ባህል  መጽሐፍ አዘጋጅ መላኩ ጌታቸው በዐለ መስቀልን አስመልክቶ ከNBC Ethiopia ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፤ ተጋበዙ!💚💛❤️
28/09/2023

የ # ክብረ በዓላት - ሃይማኖትና ባህል መጽሐፍ አዘጋጅ መላኩ ጌታቸው በዐለ መስቀልን አስመልክቶ ከNBC Ethiopia ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፤ ተጋበዙ!💚💛❤️

National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be f...

27/09/2023

የመስቀሉ ፍቅር ይደርብንና ለሀገራችንና ለምድራችንም ሰላምና ዕረፍት ይሁን!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

12/09/2023

🌼እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2016 ዓ.ም አደረሳችሁ ወዳጆች!🌼
🥀አዲሱን ዓመት🌾 ክፋትና ችግር፣ ሀገራዊው ፈተና መከራ የማይሻገሩበት ያድርግልን እስኪ!🌿

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Astereyo Media Service - አስተርእዮ ሚዲያ አገልግሎት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Astereyo Media Service - አስተርእዮ ሚዲያ አገልግሎት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ:

Share

Category