24/10/2025
የተዘነጋው የአእምሮ ህመም።
እኛ እያለን «አንድም ሰው በአዕምሮ ህመም ምክንያት ጎዳና ላይ አያድርም።» ቦርን አጌን የአእምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማእከል።
"አእምሮ ያለው ሰው ሁሉ ሊታመም ይችላል" በአለም ላይ ከ300 በላይ የአእምሮ ሕመም ዓይነቶች አሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰራ ጥናት ከአራት ሰው አንዱ በአእምሮ ሕመም ጤናው ይታወካል በኢትዮጵያም ውስጥ ተመሳሳይ ነው።
እንደሚታወቀው በማህበረሰባችን የአእምሮ ሕመም ታክሞ እንደሚድን አለመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ የአእምሮ ሕመምን ከመንፈስ ጋር ማገናኘት፣ የሚጋባ ነው ብሎ ማሰብ፣የአእምሮ ሕሙማን ኃይለኛ እና ሰው ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ናቸው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ያርቋቸዋል፣ያሸሿቸዋል ይህም እነዚህን ወገኖች ለማግለልና ለማራቅ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
እውነታው ግን ይህ አይደለም የአእምሮ ሕሙማን ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ስድስት እጥፍ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ጥቃቶቹም አካላዊ፣ ጾታዊ እንዲሁም ሥነ_ልቦናዊ ወዘተ… ናቸው። በዛ ላይ ደግሞ በአእምሮ ህመም ምክንያት ቤተሰብም ሆነ ወገን በማጣት በየጎዳናው የሚገኙት ዜጎች ደግሞ ጥቃቱ ከዚህም እጅግ ይከፋል።
በሃገራችን ለነዚህ ህሙማን ማገገሚያ ተብለው ህክምና የሚሰጥባቸው ማእከላት በግሉም ሆነ በመንግስት እጅግ ጥቂት ናቸው። ችግሩ ግን ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰና እየከፋ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ በመንግስት ብቻ የሚፈታ አልሆነም።
ይህንን የሃገር ክፍተት ለመሙላት ታዲያ ቦርን አጌን የአእምሮ ህሙማን ማገገሚያ መርጃ ማዕከል በአዕምሮ ህመም ምክንያት በጎዳና ላይ ወድቀው የሚኖሩ እና ምንም አይነት እገዛ ያሌላቸው ወገኖች አገልግሎት የሚያቀርብ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ሆኖ ከተፍ አለ።
ይህ ግብረሰናይ ድርጅት በአንድ ቅን ኢትጵያዊትና ቤተሰቧ በድንገት ከዛሬ 9 አመታት በፊት ነበር የተጀመረው። በዚህ ማእከል ከጎዳና ላይ ማህበረሰቡ ያገለላቸው፣የገፋቸው፣ ያልተረዳቸው፣ ያላገዛቸው፣ የፈራቸው፣ያራቃቸውና የጣላቸውን የሁሉንም እምነት ተከታዮች፣ዘር፣ፆታና ቀለም ሳይለይ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ድረስ የነበሩ ወገኖች ከሃገራችን ሁሉም ክልል ከየጎዳናው በማንሳት ህክምና የሚሰጥበት ማእከል ሆነ።
ቦርን አጌን ከ9 አመታት በላይ ማህበረሰቡን በበጎ ፍቃድ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን በርካቶችን ወደ ቀደመ ማንነታቸው እንዲመለሱ በማድረግ በዘርፉ የበኩሉን ሚና እየተወጣም ይገኛል።
በቦርን አጌን በአሁን ሰአት ከ120 በላይ ህሙማን የሚገኙ ሲሆን በትምህርትና ባጠቃላይ እንክብካቤ ብቻ ሳይሆን በቅጥር ግቢ ውስጥ በሚፈጥሩት ህብረት፣መተዛዘን፣ መተባበር በማህበረሰቡ ተነጥለው ያጡትን ፍቅርና ደስታ እርስ በርስ በጋራ እንዲሰጣጡ በማድረግና ህክምናውን ከመድሃኒታቸው ጋር ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ በመስጠት በቶሎ እንዲያገግሙ አድርጓል።
በዚህም 374 ከጎዳና የተነሱ የአእምሮ ህሙማን በአጭር ግዜ አገግመው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በአሁን ሰአትም በዚሁ ማእከል አገግመው የማእከሉ ሰራተኛ የሆኑ በደሞዝ የሚሰሩ ከ27 በላይ ሲሆኑ 27 የሚሆኑ በማገገሚያው የተወለዱና ከጎዳና የተነሱ ህፃናት በመልካም ጤንነት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
በቦርን አጌን አገግመው ቤተሰብ የሌላቸው እና በማገገም ላይ የሚገኙ ዜጎች በአራቱ ማእከላት ማለትም በሴቶች፣በወንዶችና በህፃናት የማእከሉ ቤቶች ውስጥም ይገኛሉ።
ይህ አንጋፋ ሃገር በቀል ድርጅት ነው እንግዲህ በየካ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ አለም አቀፍ የአእምሮ ህሙማንን ቀን በማስመልከትበእኛ እያለን «አንድም ሰው በአዕምሮ ህመም ምክንያት ጎዳና ላይ አያድርም።» በሚል መሪቃል የፓናል ውይይትና ለተለያዮ አካላት እስካሁን ስለተደረገለትና ወደፊት ስለሚደረግለት ነገር ሁሉ ቀድሞ ያመሰገነው። በእለቱም በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች፣የማእከሉ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ስለ አእምሮ ህመምና ስለ ማእከሉ አሁናዊና ቀጣይ ጉዞ ገለፃ ተደርጓል።
በዚህም በቀጣይ ማእከሉን ለማገዝ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትና ተሰሚነት ያላቸውን አካላት የአምባሳደርነት ሹመት ሰጥቷል።
በአምባሳደርነት የተሾሙት
1—ሐዋርያ ዶር ማርቆስ
2— ጋዜጠኛ መሃመድ ስራጅ
3—አቶ እስራኤል ማናዬ
4—አቶ ፍቅረሚካኤል ዘገየ
5—ወ/ሮ ጫልቱ ናቸው።
ቦርን አጌንን ለመደገፍ!
ማንኛውም ግለሰብና ድርጅቶች በፀሎት፣ በገንዘብ፣ በአይነት፣ በቁሳቁስ፣ በአገልግሎት እና በመሳሰሉት ድርጅታችንን በመደገፍ ከበረከቱ ትቋደሱ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል።
የድርጅቱ የባንክ አካውንቶች የሚከትሉት ናቸው
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000191092997 swift-code (CBETETTS)
ብርሃን ባንክ 1601310013232 swift-code (BERBETAA)
አዋሽ ባንክ 01304463028100 swift-code (AWINETAA)
ዳሽን ባንክ 0120232415011 swif-code(DASHETAA)
አቢሲኒያ ባንክ 60083018
ኦሮሚያ ባንክ 4108564/3001/0
Tel. Office: Mobile: +251911247248/+251901333330;
Email: [email protected]
Youtube:- Born Again Mental Health rehabilitation
Website. WWW.bornagainrehablitation.com
Address: Yeka Sub-city, Woreda 12, H.No. New, Addis Abeba, Ethiopia.
“No one stay on the street because of mental illness” «አንድም ሰው በአዕምሮ ህመም ምክንያት ጎዳና ላይ አያድርም።»