AFMA Media & communication

AFMA Media & communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AFMA Media & communication, Broadcasting & media production company, Addis Ababa.

24/08/2023

Check out Afma fire safety's video.

17/07/2020
28/06/2020
24/06/2020
17/06/2020

የቀዳማዊ ሚኒሊክ እና ታቦተ ፂዮን ወደ ኢትዮጲያ ጉዞ የሚዳስስ

10/06/2020

ጠቢቡ ሰለሞን እድሜው ሲገፋ ስለሞት አሰበ። በምድር ላይ ያለውን ዝና፣ ሃብት፣ክብርና ምቾት ሊያጣ መሆኑን ሲረዳ ሞትን እጅግ ፈራት። ሽንፈት አድርጎ አሰበው። "እንደኔ ያለ የአለም ጠቢብ መሞት የለበትም። ስለዚህ አንድ መላ መፈለግ ይጠበቅብኛል። ራሴን ከሞት መታደግ አለብኝ።" ብሎ አብዝቶ ተጨነቀ። የሞት መድሃኒት ለማግኘት መመራመር ጀመረ። ከብዙ ጥበባዊ ምርምር በኋላ ያለ እድሜ ገደብ በምድር ላይ መኖር የሚችልበትን የሞት መድሃኒት አገኘ። ጥበበኛው ሰለሞን ጮቤ ረገጠ።
ከመጠቀሙ አስቀድሞ ግን አዋቂዎችን ማማከር እንዳለበት ተረዳ። እድሜ ጠገብ አባቶችን፣ የየሃገራቱን ጠቢባንና አዋቂዎችን አማከረ። ሁሉም ከሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ ሰጡት።
ከዱር አራዊት እስከ ቤት እንስሳት፣ ከተሳቢ ፍጡር እስከ ሰማይ በራሪ አእዋፋት አማከረ። " መኖር ማን ይጠላል? ጥበብህን ለኛም ብትገልፅልን ስንገዛል እንኖር ነበር።" ብለው አሉት።" ከነዚህ ሁሉ ፍጡራን ግን አንድ አሞራ ለሰለሞን የጠቆመው ነገር ቀልቡን ሳበው።
ጥቆማውም ያልኖርኩበት እኔ አስተያየት ከምሰጥህ እዚያ ማዶ ዋሻ ውስጥ አንድ 400 አመት እድሜ የኖረ ንስር አለ። እሱን ብታማክረው ለውሳኔ የሚረዳ ምክር የሚሰጥህ ይመስለኛል።" የሚል ነበር። የእድሜ ባለፀጋው ንስር የሚሰጠውን ሃሳብ ለመስማት ሰለሞን እየተጣደፈ ወደ ተጠቆመበት ዋሻ አመራ።
ለነብሳቸው ያደሩ አንዳንድ አሞራዎች አልፎ አልፎ ቅንጣቢ ስጋ ሊወረውሩለት ከሚመጡት በስተቀር በአለም የተረሳው ይህ አሞራ ዛሬ እቤቱ በመጣው እንግዳ እጅግ ተደንቋል። መጀመሪያ አካባቢ እንዲያውም ህልም ሁሉ መስሎት ነበር። "የአለም ንጉስ፣ ጥበበኛው ሰለሞን... እንዴት እኔ ጋ ሊከሰት ቻለ?" እያለ ሲያሰላስል ሰለሞንም ስለገባው በቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ። ሁሉን ነገር ለንስሩ አጫወተው።
ንስሩ ሰለሞንን በፅሞና ካደመጠው በኋላ ልምዱን እንዲህ ሲል አካፈለው። "ከ350 ዓመት በፊት ከእድሜ እኩዮቼ ጋር ጥሩ ወዳጅነትና ተቀባይነት ነበረኝ። ለምሳሌ አንድ ወዳጄ እቤቱ በእንግድነት ስሄድ ሰንጋ በሬ ያርድልኝ ነበረ። ከጊዜ በኋላ እቤቱ በእግድነት ጎራ ስል 'ያባታችን ወዳጅ መጣ' ብሎ ወይፈን አረደልኝ። ለብዙ አመታት ቆይቼ ተመልሼ እዚያ ቤት ስሄድ የወዳጄ ልጅ ሞቶ የልጅ ልጁን አገኘሁት። 'ውይ ያያታችን ወዳጅ መጣ ብሎ ሙክት አረደልኝ። እሱን ተስተናግጄ ተመለስኩ። ከብዙ አመታት በኋላ ተመልሼ እዚያ ቤት ጎራ አልኩኝ። የወዳጄ የልጅ ልጅ አልፎ ልጁ ላይ ደረስኩ። በመሄደ ደስተኛ የሆነ አይመስልም ብቻ ግን ዶሮ አርዶ ጋብዞ ሸኘኝ። ከጥቂት አመት በፊት እንዲሁ እዚህ ወዳጄ ቤተሰቦች ቤት ጎራ አልኩኝ። ዶሮ አርዶ ያስተናገደኝ በሂወት አልነበረም። ልጁን አገኘሁት። ማንነቴንና ከቅምቅማያቱ ጋር የነበረኝን ወዳጅነት ነገርኩት። 'የኔ ቤተሰቦች ካንተ ጋር ወዳጅነት አለኝ-በብስጭት። 'አዎ' አልኩት ፈጠን ብዬ። ቆይ ጠብቀኝ ብሎ ፈጠን፣ ፈጠን ብሎ ወደ ቤቱ ገብቶ አፍታ ሳይቆይ መሳሪያ ይዞ ወጥቶ 'አንተንን ብሎ ወዳጅ!' ብሎ ሲተኩስ ክንፌን መትቶ አቁስሎ ይኸው እቤት እንድውል አደረገኝ። " ሁሉም የሚያምረው በጊዜው ነው።

26/05/2020

6ተኛ ሞት ተመዘገበ ። ጥንቃቄ አይለየን!
*************

የሸገር ታይምስ የመረጃ ምንጮች ከደቂቃዎች በፊት በስልክ አሳወቁን ብሎ እንደዘገበው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተጨማሪ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

የመረጃ ምንጮቻችን ህይወቷ ያለፈው ግለሰብ ፆታዋ ሴት መሆኑን ከመግለፅ ውጭ ስለ እድሜዋም ሆነ ተያያዥ መረጃዎች ከመናገር ተቆጥበዋል። ብሏል

ጥንቃቄ አይለየን!
ዘገባው የሸገር ታይምስ ነው

24/05/2020

የጃንሆይ የመጨረሻ የስር ጊዜና የቀለበታቸው ሚስጥር

16/05/2020

Address

Addis Ababa

Telephone

0925243301

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AFMA Media & communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share