Selaam Tv

Selaam Tv ሰላም ቲቪ በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሚድያ ነው ፡፡

የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰማ።ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አበነዳጅ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ መደረጉን የትራንስፖርትና ...
07/07/2022

የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰማ።

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አ

በነዳጅ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ቀን 2014 ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ፡-

* በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን፤ አዲሱ ታሪፍ 0.5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0.0240 ሳንቲም ነው፡፡

- ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡

* ደረጃ ኹለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5120 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0.0300 ሳንቲም፡፡

- ደረጃ ኹለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም፡፡

* ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.4750 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0331 ሳንቲም ነው፡፡

- ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5735 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.375 ሳንቲም ነው፡፡

የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ
* በደረጃ አንድ ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53.60 ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 56.00 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ሊሎሜትር ብር 2:40 ነው፡፡

* በደረጃ ኹለት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51.20 የሚያስከፍል ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 54.20 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3.00 ነው፡፡

* በደረጃ ሦስት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47.50 የሚያስከፍል ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 50.81 ያስከፍላል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3.31 ነው፡፡

በመሆኑም ታሪፉ ከላይ በተገለጸው መሰረት ከዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣናቸውን ለቀቀ።ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አየብርታኒያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን 40 በሚሆኑ ሚኒስቴሮቻቸው ምክንያት ስልጣናቸውን...
07/07/2022

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣናቸውን ለቀቀ።

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አ

የብርታኒያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን 40 በሚሆኑ ሚኒስቴሮቻቸው ምክንያት ስልጣናቸውን ለቀዋል። 40ዎቹ ሚኒስቴሮች ለእንግሊዝ የማይመጥን መሪ ነው ከሱ ጋር አንሰራም ብለው የስልጣን መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ ነው ቦሪስ ጀንሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት።

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

ሲፒጄ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ አበረበ።ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አመንግሥት ጋዜጠኛ አበበ ባዩን ጨምሮ ሌሎችንም የሚዲያ ባለሞያዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጄ ጠየቀ የጋዜጠ...
07/07/2022

ሲፒጄ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ አበረበ።

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 30/2014 አ አ

መንግሥት ጋዜጠኛ አበበ ባዩን ጨምሮ ሌሎችንም የሚዲያ ባለሞያዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጄ ጠየቀ

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ መንግሥት ከቀናት በፊት በፀጥታ አካላት ከቤቱ የተወሰደውን ኢትዮ ፎረም የተሰኘው የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ባዩን ጨምሮ ሌሎችንም የሚዲያ ባለሞያዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ይህን የጠየቀው ትላንት ረቡዕ ሰኔ 29 ባወጣው መግለጫው ላይ ነው፡፡ ሲፒጄ የጋዜጠኛውን የቅርብ ሰዎች ጠቅሶ እንዳሠፈረው፤ አበበ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 22 ነው፡፡

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

የጀፎረ ቂጫሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 29/2014 አ አበእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የዒድ አል አድሃ ( አረፋ ) አንዱ ነው። በዓሉ በተለይ በጉራጌ ብሔረሰብ...
06/07/2022

የጀፎረ ቂጫ

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 29/2014 አ አ

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የዒድ አል አድሃ ( አረፋ ) አንዱ ነው። በዓሉ በተለይ በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ ከሃይማኖታዊ ትሩፋቱ በተጨማሪ በባህል ጭምር የሚጌጥ በመሆኑ ተናፋቂ ያደርገዋል። በተለያየ ቦታ የሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ለዚህ በዓል ተሰባስበው ወደ ትውልድ መንደራቸው ይተማሉ።

በዓሉ በተለያዩ ጉዳዮች ተናፋቂ ሲሆን ከነዚህ መካከልም የአካባቢው መልከዓ ምድርና ስርዓቶቹ የሚጠቀሱ ናቸው። ጀፎረ ደግሞ ብዙ ትዝታዎች የሚመለሱበት፣ ህግጋት የሚከበሩበትና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን የሚያካትት ስፍራ ነው።

ጀፎረ ማለት በሁለት ትይዩ (ግራና ቀኝ በሠፈሩ) መንደርተኛ መሀከል የሚገኝ ጎዳና ማለት ነው፡፡
ይህ ጎዳና ባለቤትነቱ የሕዝብ ሆኖ ማንኛውም ሰው እንዲተላለፍበት በህብረተሰቡ ስምምነት እንዳይታረስና አጥር እንዳይታጠር ይወስናል፡፡ የጎዳናው ስፋትም 12 ዘንግ እንዲሆን ተወስኖ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ ከብቶችን ውሃ የሚያጠጣቸውና ወደ ግጦሽ ሲያሰማራቸው መተላለፊያ እንዲሆንኑ የሚተዋቸው ሌሎችም ክፍት መሬቶች ወይም ጎዳናዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ጎዳናዎች በሰባት ቤት ጉራጌ "ወአድ" ወይም "እወ" ተብለው ይታወቃሉ፡፡

ጎዳናዎች እንዳይታረሱ፣ ግለሰቦች በባለቤትነት እንዳይዙዋቸው ....ወዘተ የሚቆጣጠሩባቸው ደንቦች "የጀፎሮ ቂጫ" ይባላሉ፡፡ ይህ ደንብ በአንድ መንደር የሚገኙ ሰዎችንም ያስተዳድራል፡፡ እድርና ሳቡኚት የመሳሰሉትን ሕጎች ይቀረጻል፡፡ በአንድ መንደር የሚሰባሰቡትን ሰዎች በማስተባበር የአካባቢያያቸውን ጎዳናዎች እንዲጠበቁና ለሕዝብ መተላለፊያ የሆኑት መንገዶች በእርሻ እንዳይደፈር ቁጥጥር እንዲኖር ያስገድዳል፡፡

በአሁን ወቅት የሚታየው የጉራጌ ብሔረሰብ መንደር ምስረታ ከሌሎቸ ብሔረሰቦች ለየት የሚያደርገው የዚህ ደንብ (የጀፎረ ቂጫ) መሆኑ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡
ምንጭ፡-ጎጎት የጉራጌ ብሔረሰብ ታሪክ ገፅ ከ122-123

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

የነዳጅ ድጎማ የቀን ኮታሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 29/2014 አ አ*ባለ3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር* መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር*ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊት...
06/07/2022

የነዳጅ ድጎማ የቀን ኮታ

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 29/2014 አ አ

*ባለ3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
* መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
*ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
*መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
*የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
* የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
*ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ሆኗል።

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

06/07/2022

ነገ ብሞት ፀፀት እንዳይሆንብኝ ዛሬ እናገራለሁ።

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 29/2014 አ አ

« የፓርላማ አባሉ ዶክተር ሀንጋሳ ኢብራሂም »

ወለጋ ያለውን ጭፍጨፋ የሚፈፅሙት የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና አመራሩ ናቸው። ሸኔዎች አይደሉም። ሁለት አይነት ሸኔ ነው ያለው። አንዱ ሸኔ የሚመራው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ነው። ሌላኛው ሸኔ ንፁህ ታጋይ ነው።

ሰዎች በብሔር ማንነታቸው ተለይተው እንዳይገደሉ ከተፈለገ የክልሉ መንግስትና መዋቅሩ መፍረስ አለበት። ዶክተር አብይ አትታለል። በውሸት አይሸውዱህ። የውሸት ሪፖርት ነው የሚሰጡህ። እሱን እየሰጡህ በህዝብ ፊት እያሷሹህ ነው። ገዳይ ያለው እዚህ መንግሥት ቢሮ ውስጥ ነው።
የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀላፊና የክልሉ መንግስት ናቸው እያስገደሉ ያሉት።

ይችን ሀቅ ተናግሬ ብሞትም አይቆጨኝም።
ሳልሞት በፊት ያስቀየምኳችሁ ሰዎች ካላችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ። ከሦስት ቀን በፊት ነበር የሀንጋሳ ኢብራሂም የግል ጠባቂ አዲስ አበባ ላይ የተገደለበት።

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

05/07/2022

ከኦሮሚያ መጅሊስ የተሰጠ መግለጫ

በድጋሚ ሙስሊም ወሎዬዎች ተጨ_ፈጨፉ

በቄለም ወለጋ ዞን በመቻራ ወረዳ መንደር 20 ቀበሌ ውስጥ በወሎ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ጭፍ_ጨፋ ተፈፅሟል።

ኢናሊላሂ ወእና ኢሌይሂ ራጂኡን። ቁስለኞች ሆስፒታል አጨናንቀዋል። የሟቾች ቁጥር ብዙ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመልክታል። ከማህበረሰቡ የደረሰን መረጃ በኦነግ የታጣቂዎች እንደተፈፀመ አሳውቀውናል። ታጣቂዎቹ በቅርብ ግዜ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተጨፍጭፈዋል። ተፈናቅለው ያሉትም አስፈላጊ እርዳታ አልደረሳቸውም።

የወሎዬዎች ሞት መች ያበቃ ይሆን? ሃላፊነቱስ ማን ይወስዳል? ለፖለቲካ ፍጆታ ለምን የሙስሊሞች ደም ይፈሳል? እስከመቼ?

የኦሮሚያ መጅሊስ ድርጊቱን አጥብቆ ያወግዛል። ሀገርን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ነው። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በአስቸኳይ አጣርቶ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ አጥብቀን እንጠይቃለን። የቶሌ ጉዳይ ፈር ሳያገኝ በድጋሚ መከሰቱ አሳፋሪ ነው።

የአላህ ወንድሞቻችን የሸሂድነት ደራጃ የቆሰለቱን ፈውስን ለቤተሰባቸው ሰብርን ወፍቃቸው። አሚን

04/07/2022

ሰበር መረጃ‼️

በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ ታጣቂዎች ዘግናኝ ጥቃት ዳግም ፈጸሙ!!
---RN05----

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከትናንት ዕሁድ ማታ ጀምሮ ለሰኞ አጥቢያ እስከ ዛሬ ሰኞ 4፡00 ድረስ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት እንዳለፈ የአካባቢዉ ነዋሪዎች መረጃ አድርሰውናል፡፡
………
ምንም እንኳ ነዋሪዎቹ ለክልሉ ልዩ ሃይል ቀድመው የድረሱልኝ ጥሪ ያሰሙ ቢሆንም መረጃው የደረሰው ልዩ ሃይል "እናስራችኋለን አርፋችሁ ተቀመጡ" የሚል ምላሽ መስጠቱን ስማቸን እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተውናል።
…………
በቅርብ ርቀት የሚገኘው የመከላከያ ሃይልም ከነዋሪዎቹ የድረሱልኝ ጥሪ የደረሰው ሲሆን "የስምሪት ትዕዛዝ አልተሰጠኝም" በሚል በጥቃቱ በርካቶች እስከተጨፈጨፉበት እስከ ዛሬ 4፡00 ድረስ ለተጠቂዎቹ ሊደርስላቸው እንዳልቻለ ለአር ኤን 05 አስረድተዋል፡፡
………
ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለደህንነታቸው የሰጉ ምንጮቻችን እንደተናገሩት ከሆነ በዛሬዉ እለት ታጣቂ ቡድኑ በከፈተዉ ጥቃት ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ንጹሀን እንደተገደሉና ከጥቃት ሰላባ መሀል በርካቶቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዉልናል።

የነበረዉ የሽብር ቡድኑ ሀይል ብዛት የነበረዉ በመሆኑ በአካባቢዉ የሚገኙ የሚሊሻ የጸጥታ ሀይሎች ተጨማሪ ሀይል እስኪመጣ ድረስ ወደ አካባቢዉ መግባት እንዳልቻሉም ነዋሪዎቹ አስረድተውናል።

ቲቲባይታወቅም ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ንጹሀን ተገድለዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ።

ከዚህ በተጨማሪም የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ በርካታ ዜጎች እንደሚገኙ እና ቁስለኞቹንም ከአካባቢዉ ለማስወጣት እንደተቸገሩም ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

ይህን መረጃ በተመለከተ እስካሁን የጥቃት ቡድንም ይሁን መንግስት በጉዳዩ ዙርያ ያሉት ነገር የለም።

በወለጋ ሰኔ 11/2014 በተጸመ ተመሳሳይ ጥቃት ቁጥራቸዉ በሺዎች የሚገመት ንጹሀን እንደተገደሉ መዘገቡና መከላከያን ጨምሮ የተለያዩ ሀይሎች ወደ ቦታው ሄደዋል መባሉ ይታወቃል።
----------
የዚህ ዘገባ አላማ መረጃን ቶሎ በማድረስ የዜጎችን ደህንነት ከባሰ አደጋ በቶሎ ለመታደግ ነው

ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በድጋሚ መሪ አድርጎ መረጠ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ለመጪዎቹ ሶስት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሚ ተመረጡ። በእርሳቸ...
03/07/2022

ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በድጋሚ መሪ አድርጎ መረጠ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ለመጪዎቹ ሶስት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሚ ተመረጡ። በእርሳቸው የአመራር ስብስብ ስር ሆነው ለውድድር የቀረቡት አቶ ዮሐንስ መኮንን የፓርቲው ምክትል መሪ ሲሆኑ፤ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ደግሞ የፓርቲውን የሊቀመንበርነት ቦታ ተረክበዋል።

የፓርቲው አመራሮች የተመረጡት ዛሬ እሁድ ሰኔ 26፤ 2014 በተካሄደው የኢዜማ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ነው። ከትላንት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚሁ የኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 900 ገደማ ጉባኤተኞች መሳተፋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትዕግስት ወርቅነህ ገልጸዋል።

የፓርቲው ጉባኤተኞች በሁለተኛ ቀን ውሏቸው፤ ኢዜማ ለመምራት በዕጩነት ለቀረቡት ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዷለም አራጌ እንዲሁም የፓርቲውን ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች ለመያዝ ለተወዳደሩ ግለሰቦች ድምጽ ሰጥተዋል። በውጤቱም መሰረት ፕሮፌሰር ብርሃኑ 549 ድምጽ በማግኘት የኢዜማ መሪነት ስልጣናቸውን አስጠብቀዋል።

ከኢዜማ ምስረታ አንስቶ የፓርቲውን የምክትል መሪነት ቦታ ይዘው የቆዩት አቶ አንዷለም አራጌ 326 ድምጽ አግኘተዋል። ኢዜማን ለመምራት በዕጩነት የቀረቡት ሶስት ተወዳዳሪዎች የነበሩ ሲሆን ሶስተኛው ተወዳዳሪ አቶ ጸጋው ታደለ ራሳቸውን ከውድድሩ አግልለዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመሪነት በመቅረብ ብቸኛው የነበሩት አቶ ጸጋው ራሳቸውን ከውድድር ያገለሉት ምክትላቸው የነበሩት አቶ አየለ ዳመነ “የፓርቲውን ውስጥ መስፈርት ባለማሟላታቸው” ምክንያት ከውድድር ውጭ በመሆናቸው ነው። አቶ ጸጋው ከእሳቸው ጋር ምክትል መሪ በመሆን የሚወዳደር ግለሰብ እንዲመርጡ በፓርቲው የአንድ ሳምንት ጊዜ ቢሰጣቸውም ማቅረብ አልቻሉም።

ለፓርቲው መሪነት ተወዳድረው በተሸነፉት አቶ አንዷለም አራጌ ምትክ፤ አቶ ዮሐንስ መኮንን የኢዜማ ምክትል መሪ እንዲሆኑ ዛሬ በጉባኤተኛው ተመርጠዋል። አቶ ዮሐንስ ለተረከቡት ቦታ በሌላኛው ጎራ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ሐብታሙ ኪታባ ነበሩ።

ፓርቲው ከመሪ እና ምክትል መሪ ባለፈ፤ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ ጸሐፊ እና የፋይናንስ ኃላፊ ምርጫዎችንም አድርጓል። ኢዜማን በሊቀመንበርነት ለመምራት አምስት ጣምራ ዕጩዎች ለውድድር ቀርበው ነበር።

ከዕጩዎቹ መካከል የአሁኑ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ምክትላቸው ዶ/ር ጫኔ ከበደ ይገኙበታል። ዶ/ር ጫኔ 435 ድምጽ በማግኘት የፓርቲውን ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፤ አቶ የሺዋስ 238 ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ሰበር መረጃ======👉 እየተንገላቱ ያሉ ሃጃጆች ገንዘብ አስመላሽ ኮሚቴ አቋቋሙ ተባለ  👉 መጅሊሱ ሃጃጆቹን በሃሰት ዉንጀላ ከግቢው በፖሊስ ሊያባርራቸው ሞክሮ ሳይሳካ ቀረ!----RN05---...
03/07/2022

ሰበር መረጃ
======

👉 እየተንገላቱ ያሉ ሃጃጆች ገንዘብ አስመላሽ ኮሚቴ አቋቋሙ ተባለ
👉 መጅሊሱ ሃጃጆቹን በሃሰት ዉንጀላ ከግቢው በፖሊስ ሊያባርራቸው ሞክሮ ሳይሳካ ቀረ!

----RN05----

በሀጅ ጉዳይ " ሃጁንም ሳናደርግ ገንዘባችንም ተመዘበርን" ያሉ ከተለያዩ ክልሎች መጥተው በመጅሊሱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ አዉላላ ሜዳ ላይ በመፍሰስ ደጅ እየጠኑ እና እየተጉላሉ ያሉ ሙስሊሞች ገንዘባቸዉን ለማስመለስ ኮሚቴ ማቋቋማቸው ታወቀ !

ይህ አስመላሽ ኮሚቴ መቋቋሙን ያወቁት የመጅሊስ ሰዎች ዛሬ እሁድ ቀን ላይ ፖሊስ ጠርተው ሊያባርሯቸው መመኮራቸው መረጃ ደርሶናል፡፡

ፖሊሶቹ በመጡበት ወቅቱ በመጅሊሱ ግቢ ዉስጥ የተኮለሉ አዛዉንቶች እና በድንኳን ዉስጥ የተጠለሉ ሙስሊሞችን ያነጋገሩ ሲሆን

ሀጃጆቹም የደረሰባቸዉን እንግልት በማብራራት ይህንኑ ችግራቸዉን ለመቅረፍ ተደራጅተው ሃላፊ መመረጣቸዉን እንጂ ከዛ ዉጪ የፈጸሙት ነገር አለመኖሩን ለፖሊሶች አስረድተዋል፡፡

በሁኔታው እና ባዩት ነገር ግራ የተጋቡት ፖሊሶች ከመጅሊስ ተደዉሎ፣ "መጅሊሱ እየተረበሸ እንደሆነና ድንጋይም ወደ ህንጻው እየወረወራችሁ እንደሆነ ነው የተነገረን፣ ነገር ግን ያየነው ነገር የተለየ ነው ለማንኛዉም ቢሮ ዉስጥ ገብተን ደዉሎ የጠራንን አካል እናናግራለን!" በማለት ወደ መጅሊሱ ቢሮ ቢዘልቁም ሁሉም ቢሮዉን ዘግቶ መሰወሩን እና የሚያነጋግራቸው አካል ሊያገኙ አለመቻላቸዉን ገልጸዋል፡፡

ፖሊሶቹም በማያያዝ ሃጃጆቹ ጥያቄያቸዉን በአግባቡ እንዲያቀርቡ በተረፈ ግን መጅሊሱ ግቢ ዉስጥ በዚህ ሁኔታ ብዙ መቆየቱ ምናልባት ሌላው ወገን ችግር ሊፈጥርባቸው እንደሚችል በመግለጽ ተሰናብተዋቸው መሄዳቸዉን የዉስጥ ምንጮቻችን አድርሰዉናል፡፡

ዝርዝር መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል

02/07/2022

ሱዳን

የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀቁ።ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 25/2014 አ አከዒድ እስከ ዒድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸውና እንግዶችም ...
02/07/2022

የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀቁ።

ሠላም፣ ቲቪ፣ ሰኔ 25/2014 አ አ

ከዒድ እስከ ዒድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸውና እንግዶችም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መግባት እንደሚጀምሩ ተገለጸ።

የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ቀጣይ ክፍል የሆነው ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸውና እንግዶችም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መግባት እንደሚጀምሩ ተገለጸ።

ጥሪውን እንዲያስተባብር የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቀጣዩ ምዕራፍ ከኢድ እስከ ኢድ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲጀመር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት የብሔራዊ ኮሚቴው ሴክሬታሪያት የሆነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የብሔራዊ ኮሚቴው ጣምራ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በተገኙበት ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው።

በውይይቱ ወቅት ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ከዕቅድ አፈጻጸምና ከባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አንጻር በነበሩ አፈጻጸሞች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ ከመጀመሪያው ዙር መወሰድ ያለባቸው ተሞክሮዎችም በዝርዝር ቀርበዋል።

ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛና የማጠቃለያ ምዕራፍ በርካታ የዳያስፖራ አባላትና ሁለተኛ ትውልድ ልጆቻቸው ዕረፍት በሚሆኑበት ጊዜ መከናወኑ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸውና ዳያስፖራውን በስፋት የሚያሳትፉ መርሀ ግብሮች መቀረጻቸው ጥሪውን በስኬት ለማከናወን የሚረዱ ጉዳዮች መሆናቸውም በውይይቱ ወቅት ተጠቅሷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የብሔራዊ ኮሚቴው ጣምራ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድና የሴክሬቴሪያቱ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ በፊት ከተካሄዱ ጥሪዎች የተገኙ ተሞክሮዎችን ታሳቢ በማድረግ ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ሁለተኛ ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይም ጥሪው የሚያጠነጥንባቸውና ስትራቴጂያዊ የሆኑ ማህበረ-ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎች እንዲሳኩ እንዲሁም በዕቅድ የተያዙ ተግባራት በውጤታማነት እንዲከናወኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ጥሪውን ተከትሎ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ እንግዶች ወደ ሀገር ቤት መግባት የሚጀምሩ ሲሆን፣ የተዘጋጁ ዝርዝር መርሀ ግብሮችም ከቆይታ በኋላ ይፋ የሚሆኑ ይሆናል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት

የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube 👉👉https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook👉👉https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram👉👉
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL

Address

Addis Ababa
2198

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Selaam Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share