Mihret Teshome

Mihret Teshome Don't watch today, stand on today and watch tomorrow ❤✌❤✌❤✌❤✌❤

ኢትዮጵያ የብሄሮች እና ብሔረሰቦች ሃገር እንጂ የፅንፈኞች መፈንጫ አይደለችም!ኢትዮጵያዊያን ህብረብሔራዊ አንድነታቸዉን እና በእዉነተኛ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ተከባብረዉ እና ተቻችለ...
08/12/2022

ኢትዮጵያ የብሄሮች እና ብሔረሰቦች ሃገር እንጂ የፅንፈኞች መፈንጫ አይደለችም!

ኢትዮጵያዊያን ህብረብሔራዊ አንድነታቸዉን እና በእዉነተኛ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ተከባብረዉ እና ተቻችለዉ በጋራ እየኖሩ ያሉ ህዝቦች ናቸዉ። ይህ ህብረብሔራዊ አንድነት ፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት በፅንፈኞች አይደናቀፍም! በተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ይከስማል።

ታላቋን ሀገር በታላላቅ ሀሳቦች ይበልጥ እናተልቃት እንጂ ፤ በሀሳብ አንሰን፣ በወሬ ኮስሰን ሀገራችንን አናኮስሳት‼️       ጠ/ሚ አብይ አህመድ
29/11/2022

ታላቋን ሀገር በታላላቅ ሀሳቦች ይበልጥ እናተልቃት እንጂ ፤ በሀሳብ አንሰን፣ በወሬ ኮስሰን ሀገራችንን አናኮስሳት‼️
ጠ/ሚ አብይ አህመድ

ጀግናን ማስታወስ እና መዘከር አዲስ ጀግና ይፈጥራል ። 👉👉 #ተመረቀበልደታ ክ/ከተማ የሚገኘው የሌትናል ኮ/አብዲሳ አጋ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተመረቀ።ት/ቤቱ የአዲስ አበባ ...
22/11/2022

ጀግናን ማስታወስ እና መዘከር አዲስ ጀግና ይፈጥራል ።

👉👉 #ተመረቀ
በልደታ ክ/ከተማ የሚገኘው የሌትናል ኮ/አብዲሳ አጋ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተመረቀ።

ት/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ቡዜና አብዱል ቃድር፣ አርበኞች፣ ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ፣የሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።

የሌ/ኮ አብዲሳ አጋ መታሰቢያነት የተሰራ ሀውልትም ተመርቋል።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ጀግናውን ተጋድሎ የሚያሳይ ዶክመንተሪ ፊልም ለእይታ ቀርቧል።

ብሩህ ዘመን ለኢትዮጵያ ይሆናል
19/11/2022

ብሩህ ዘመን ለኢትዮጵያ ይሆናል

"ኢትዮጵያ 9.5 ሚልዮን ህጻናትን በቀን 2 ጊዜ በመመገብ ታስተምራለች። ይህ ትልቅ ስራ ነዉ፤ በኑሮ ዉድነት ምክንያት ከትምህርት የሚቀር ትዉልድ መኖር የለበትም። ይህንን አጠናክረን እንቀጥላ...
15/11/2022

"ኢትዮጵያ 9.5 ሚልዮን ህጻናትን በቀን 2 ጊዜ በመመገብ ታስተምራለች። ይህ ትልቅ ስራ ነዉ፤ በኑሮ ዉድነት ምክንያት ከትምህርት የሚቀር ትዉልድ መኖር የለበትም። ይህንን አጠናክረን እንቀጥላለን!!"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል።በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወ...
14/11/2022

የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል።

በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦

- በነገው ዕለት 25 ሺህ 791 የ40/60 እና 20/80 ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።

- በነገው እጣ 146 ሺህ 892 እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በቂ ቁጠባ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ።

- በነገው እጣ አወጣጥ ነባርና በ2005 ዓ.ም በባለሶስት መኝታ ቤት የተሰሩ 300 ቤቶችም ይተላለፋሉ።

- በእጣ አወጣጡ ላይ ከዚህ ቀደም የገጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ አዲስ የእጣ አወጣጥ ስርዓት ተዘርግቷታ።

- የመረጃ ማጥራት እና ማደራጀት ስርዓቱ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ተከናውኗል።

- የእጣ ማውጫ መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ያለማው ሲሆን ከፌደራል ተቋማት እና ከከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

- የእጣ አወጣጡ በቆጣቢዎች የቅድመ ግምገማ ወይም የእጣ አወጣጥ ሙከራ የተካሄደበት ነው።

- ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱም በቴሌቪዠን ይተላለፋል።

ሰላም የብልፅግና ቀዳሚ መርህ !!ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጫፍ ጫፍ በግጭቶች እና አለመረጋጋት ተወጥራ ከቆየች በኋላ በለውጡ ሃይልና በመላው ህዝባችን ከመጣው ለውጥ በኋላ ሲፈጠር ...
12/11/2022

ሰላም የብልፅግና ቀዳሚ መርህ !!

ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጫፍ ጫፍ በግጭቶች እና አለመረጋጋት ተወጥራ ከቆየች በኋላ በለውጡ ሃይልና በመላው ህዝባችን ከመጣው ለውጥ በኋላ ሲፈጠር ቀዳሚ እና ቋሚ አጀንደው ቀጣይነት ያለው ሰላም ማረጋገጥ ነው።

ይህንንም ለማሳካት የለውጡ አመራር እስካሁን ያለፈበትን የሰላም ጉዞ ምን እንደሚመስል ለአብነት ያህል ብንመለከት የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ በወቅቱ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የነበረበት የሱማሌን ክልል በመጎብኘት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አከናውነዋል። በመቀጠልም ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ከህዝቡ ጋር ውይይት አከናውነዋል። በሁለቱም ክልሎች እና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እንዲሁም በውጭ ሀገራት በነበራቸው ጉብኝት ወቅት የህዝቡን አቀባበልና ደስታ ሁሉም የሚያስታውሰው ነው።

በአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ እስከ አጎራባች ሀገራትም ሆነ ሌሎች የሩቅ ሀገራት ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ሰላማዊ ግንኙነት ፓርቲያችን ገና ከውልደቱ ጀምሮ ነበር አፅንኦት ሰጥቶ ሲሰራ እና ውጤትም ሲያስመዘግብም የነበረው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የማይገባት የሰላም እጦት አጋጥሟታል። የገጠመን የሰው ህይወትና የቁሳቁስ ኪሳራ እጅግ ከባድ ነበር። አሁን ያ ሁሉ አልፎ ወደ ላቀ ሰላም እየተንደረደርን እንገኛለን። በተቀናጀ ርብርብ ሁሉ አቀፍ ሰላምን ለማሳካት ደግሞ የሁሉም ወገኖች በጎ ትብብር የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በፓርቲያችን የሚመራው መንግሥት ዘላቂ ሰላም በሀገራችን ሰፍኖ የምናልመው ሀገራዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ ነፃና ገለልተኛ የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ጭምር መንግስታዊ እገዛ ሲያደርግ መቆየቱም ይታወሳል። አሁንም ሆነ ወደፊት ለሀገራችን ፍቱን መድሃኒት በሁሉም ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ሰላምን እውን ማድረግ ስለሆነ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ፓርቲያችን ዛሬም እንደ ትላንቱ የሁል ጊዜ የሰላም ጥሪውን ያቀርባል።

ሰላም ለኢትዮጵያ !!

ኢትዮጵያ በአንድነት ትቀጥላለች።
11/11/2022

ኢትዮጵያ በአንድነት ትቀጥላለች።

ለጦርነት የበረታው ጉልበታችን ለሰላም መዛል የለበትም!!✍️በአብዲ ኬከሰሞኑ በመንግስትና በህወሃት መካከል የተፈረመው ስምምነት፤ በአለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ገሚሱ በተስፋ፤ ገሚሱ በጥርጣ...
10/11/2022

ለጦርነት የበረታው ጉልበታችን ለሰላም መዛል የለበትም!!

✍️በአብዲ ኬ

ከሰሞኑ በመንግስትና በህወሃት መካከል የተፈረመው ስምምነት፤ በአለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ገሚሱ በተስፋ፤ ገሚሱ በጥርጣሬ የተወሰኑት ደግሞ በትጋት እየመለከቱት ነው፡፡

ዋናዎቹ ባለቤቶችና ገፈት ቀማሾቹ ኢትዮጵያዊያን ግን በዚህ ስምምነት ብዙ ተስፋ አድርገዋል፤ ደስም ብሎዓቸዋል፡፡ እዚህ አዲስ አበባ ያለውን ስሜት ሁላችንም እያየነው ስለሆነ ከወደ መቀሌስ ያለው ስሜት ምን ይመስል ይሆን የሚል የማወቅ ጉጉት ነበረኝ፡፡

ከሰሞኑ በተለያየ ሚዲያ፤ ከጸጥታ መዋቅሩና ከሌሎች አካላት የምሰማው ነገር *ይህ ስምምነት ወደ መሬት የመውረድ እድል አለው* ብዬ ተስፋ እንዳደርግ አድርጎኛል፡፡

እንደ አዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ሁሉ መቀሌም ዋና መነጋገሪያዋ የሰላም ስምምነቱ ነው አሉ፡፡ ነዋሪዎች ጦርነት የሚያቆም ስምምነት በመደረሱ በደስታና በትልቅ ተስፋ እየተጋገሩበት ነው እየተባለ ነው፡፡

ይህ ትልቅ ዜና ነው፤ እየተሰማ ያለው የሰላም ፍላጎትና የከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመር በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት የሚኖረው አስተዋጽዖ ቀላል አይደለም፡፡
ትራግራይ ቲቪም ላይ እየታየ ያለው መሻሻል የሚበረታታ ነው፡፡ አሁንም ቀስ በቀስ በስምምነቱ መሰረት ከአሉታዊ ፕሮፓጋንዳ ሙሉ በሙሉ ተላቆ ለሰላሙ አወንታዊ ሚና ወደ መጫወት ይመጣል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

በኬኒያ ናይሮቢ እየተካሄደ ያለው፤ የስምምነት ትግበራ ሂደት ውይይትም ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ መረጃ አለኝ፡፡ የትጥቅ መፍታትና ሌሎች ጉዳዮች ዝርዝር እቅድ እየተዘጋጀ ነው፡፡
ለጦርነት የበረታው ጉልበታችን ለሰላም መዛል የለበትምና እንበርታ ማለት ፈልጋለው!!

08/11/2022

የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች የአዛዦቻቸውን ፍቃድ ሳይጠይቁ ግንኙነት ማድረግ ጀምረዋል:: የህወሓት ታጣቂዎች መከላክያ ሰራዊት ያለለት ቦታ በመምጣት ምግብ ይበላሉ ሲጋራ ይወስዳሉ የሞቱ ወንድሞቻቸውን በአንድነት ይቀብራሉ::

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከEMS ጋር ባደረጉት ቆይታ የተናገሩት

"ገንዘብ ብናቀብል ሚዲያ ብናቀብል የጦር መሳሪያ ብናቀብል ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብላችሁ ብዙ የደከማችሁ የቅርብና የሩቅ አገራት፤ ኢትዮጵያ የማትፈርስ፣ የጸናች፣ የምትበለጽግ የአፍሪካ ፈርጥና ...
04/11/2022

"ገንዘብ ብናቀብል ሚዲያ ብናቀብል የጦር መሳሪያ ብናቀብል ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብላችሁ ብዙ የደከማችሁ የቅርብና የሩቅ አገራት፤ ኢትዮጵያ የማትፈርስ፣ የጸናች፣ የምትበለጽግ የአፍሪካ ፈርጥና ኩራት ነች።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mihret Teshome posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mihret Teshome:

Share

አቢቹ - The man

በአንድ ዓመት ውስጥ ከግምትም ከትንቢትም በላይ የሆነውን ተዓምር ስላሳያችሁን፣ የለማውን ቡድን አባላት በሙሉ አቻ የሌለው ምስጋና ይድረሳችሁ! እንንኳን አደረሳችሁን! እንኳን አሻገራችሁን!