
09/01/2021
ጥር 1 ቀን 2013
ላለፉት 45 አመታት የህወሀት መራሽ እኩይ ሴራ ፊታውራሪ የነበረውን የከሃዲያን አለቃ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ዘጠኝ የአፍራሽ ቡድኑ አመራሮች ዛሬ በህግ ወደሚዳኙበት ስፍራ ደርሰዋል ።
የጥፋት ተልዕኮ ቡድኑ መሪና ስምሪት ሠጪው አቶ ስብሃት ነጋ /አቦይ ስብሐት/ ሠው ሊደርስበት በማይችልበት የተከዜ በረሃ የዝንጀሮ ገደል በሚባል ቦታ ተሸክመው ቢደብቁትም ፣ ጀግናው ሠራዊታችን ከተደበቀበት በረሃ በቁጥጥር ስር አውሎ ተሸክሞ ማውጣቱ ይታወሳል ።
ብ/ጀነራል ተስፋዬ በመግለጫቸው እንዳሣወቁት ዛሬ ሠራዊታችን ባደረገው ኦፕሬሽን አቦይ ስብሃትን ጨምሮ ሌ/ኮ አፀዱ ሪች ፣ ኮ/ል ክንፈ ታደሠ ፣ኮ/ል የማነ ካሕሳይ ፣ አቶ አስገደ ገ/ክርስቶስ ፣ አቶ አምደማርያም ተሠማ ፣ ኮማንደር በረሄ ግርማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የሜ/ጀነራል ሀየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችው ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ከገደል ላይ ወድቃ መሞቷ መረጋገጡን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል ።
መለክ በቃሉ ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ መለክ በቃሉ