
04/08/2025
#ሀሺሽ የተሰኘ አደንዛዥ እፅ ተያዘ።
በድሬዳዋ ከተማ ወረዳ 05 ስር የሚገኙ በተለያዩ አከባቢዎች ላይ በተደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን አምስት ኪሎግራም የሚመዘን ሀሺሽ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እፅ እና ከጉዳዩ ጋር የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋሉን በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀዋል ።
በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ሰላም ወርቁ ለድሬዳዋ ፖሊስ ሚድያ እንደገለፁት ''ሀሺሽ ካናቢስ" የተሰኘው አደንዛዥ እፁ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን አምስት ኪሎግራም የሚመዘን ሀሺሽ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እፅ እና ሁለት ተጠቃሚ ግለሰቦች እና አንድ አከፋፋይ በአጠቃላይ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሶስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየጠራ መሆኑን አስታውቀዋል ።
ለአዳዲስ መረጃዎች እነዚህን ገፃቻችንን ይቀላቀሉ ‼️
👇
https://www.facebook.com/neude.samuele Facebook
https://www.facebook.com/worldcrimelovenews/
Telegram https://t.me/+UMxAEL-P7HqFB06G