Eftan News

Eftan News Accurate information for the public!

29/03/2025
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ።(ኢፍታን ኒውስ፤ ጥር 24/2016 ዓ.ም -  አዲስ አበባ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን ፣ 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰ...
02/02/2024

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ።

(ኢፍታን ኒውስ፤ ጥር 24/2016 ዓ.ም - አዲስ አበባ)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን ፣ 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በአማራ ክልል የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ለመቀበልና ለማፅደቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1299/2015 ለማራዘም የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።

ምክር ቤቱ ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ ሲያካሂድ የውሳኔ ሀሳቡን ረቂቅ ያቀረቡት የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በአዋጁ መራዘም አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ማቅረባቸውን ተከትሎ የምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 5/2016 ሆኖ በ ሁለት ተቃውሞ ፣ በሦስት ድምፀ ታዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ ለቀጣይ አራት ወራት እንዲራዘም አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መራዘም ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የስራ ዘመንን ለማራዘም የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ የውሳኔ ቁጥር 6/2016 ሆኖ በ2 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከዓለም 93ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ያለ ቪዛም 44 አገራት መግባት ያስችላል ተባለ።(ኢፍታን ኒውስ፤ ጥር 19/2016 ዓ.ም -  አዲስ አበባ)የዓለም የጉዞ ሰነድ ተቀባይነትን...
28/01/2024

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከዓለም 93ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ያለ ቪዛም 44 አገራት መግባት ያስችላል ተባለ።

(ኢፍታን ኒውስ፤ ጥር 19/2016 ዓ.ም - አዲስ አበባ)

የዓለም የጉዞ ሰነድ ተቀባይነትን አስመልክቶ ቁጥራዊ መረጃና ደረጃን የሚያወጣው ሄንሌይ የተሰኘው ፓስፖርት መለኪያ ተቋም የ2024 የሀገራት ፓስፖርት ጥንካሬ ኢትዮጵያን 93ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዘ ሰው ያለ ቪዛ ወደ 44 ሀገራት መጓዝ እንደሚችልም ሄንሌይ የፓስፖርት መለኪያ ተቋም አስታውቋል።

ያለ ቪዛ ቀጥታ የሚገባባቸው ሀገራት ባርባዶስ፣ ቤኒን፣ ቦሊቪያ፣ ኩክ ደሴቶች፣ ዶምኒካ፣ ሃይቲ፣ ኬንያ፣ ላኦስ፣ ማዳካስካር፣ ማላዳቪስ፣ ኑዬ፣ ፕላዩ ደሴቶች፣ ፊሊፒንስ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ሲናጋፖር፣ ስሪላንካ፣ ሴንት ቪንሴንትና ግሬኔድስ፣ ሱሪናሜ፣ ጋምቢያ በመዳረሻ ቪዛ (ቪዛ ኦን አራይቫል) የሚገባባቸው ሀገራት ናቸው።

በተጨማሪም ባንግላዴሽ፣ ቡሩንዲ፣ ካምቦዲያ፣ ኬፕ ቭርዴ፣ ኮሞሮስ ደሴቶች፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ጋና፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኢራን፣ ማካዎ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞሪሽስ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒካራጉዋ፣ ናይጄሪያ፣ ሳሞዋ፣ ሲሸልስ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሴንት ሉሺያ፣ ታይላንድ፣ ቲሞርሌስት፣ ቶጎ፣ ታቩሉ እና ዚምባቡዌንም እንደሚያጠቃልል መረጃው ያመለክታል።

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ካውንስል አባል የመሆን መብት አላት - ሰርቫይቭ ዘ ኒውስ(ኢፍታን ኒውስ፤ ሕዳር 8/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የባ...
18/11/2023

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ካውንስል አባል የመሆን መብት አላት - ሰርቫይቭ ዘ ኒውስ

(ኢፍታን ኒውስ፤ ሕዳር 8/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት የሕልውና ጉዳይ ነው ማለታቸውን ተከትሎ የባሕር በር ጉዳይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያነቱ አሁንም ቀጥሏል።

በዚህ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሀተታ ያስነበበው ሰርቫይቭ ዘ ኒውስ (Survive the News) የተሰኘ የውጭ ሚዲያ፥ "ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ካውንስል አባል የመሆን መብት አላት" ሲል ፅፏል።

የቀይ ባሕር ካውንስል የተቋቋመው በቀይ ባሕር ቀጠና ያሉ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ እና የፀጥታ ጉዳይን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት መሆኑን ዘገባው ያትታል።

አጠቃላይ ንግዷን በቀይ ባሕር በኩል የምታካሂድ እና ከቀይ ባህር 60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ካውንስል ማግለል ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ሰርቫይቭ ዘ ኒውስ በጉዳዩ ላይ ያስነበበው ሰፋ ያለ ጽሁፍ ያመለክታል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ካውንስል ማግለል ምክንያታዊ አለመሆኑን ለማሳየት ዘገባው የአርክቲክ ካውንስልን ልምድ አጋርቷል።

የአርክቲክ ካውንስል ከአርክቲክ ውቅያኖስ ጋር የማይዋሰኑትን ስዊድን እና ፊንላንድን የካውንስሉ ሙሉ አባል አድርጓል።

ከዚህ ባሻገር ከውሃው አካል በ9 ሺህ ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙት ቻይና እና ህንድም በአርክቲክ ካውንስል በታዛቢ አባልነት መካተት ችለዋል።

ከዚህ አኳያ ከቀይ ባሕር 60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን ቢያንስ የቀይ ባሕር ካውንስል ታዛቢ አባል አለማድረግ ግርምትን ይፈጥራል ይላል ትንታኔ ጽሁፉ።

ያም ሆነ ይህ ለቀይ ባሕር በቅርብ ርቀት የምትገኝ እና በዓለም ደረጃ ከፍተኛ የሕዘብ ቁጥር ካላቸው ሀገራት ተርታ የምትመደበውን ኢትዮጵያን ያገለለ የቀይ ባሕር ካውንስል የታለመለትን ግብ አይመታም ሲል ዘገባው ጽሁፉን ያጠቃልላል። (EBC)

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eftan News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Eftan News:

Share