BE INFORMED FIRST

BE INFORMED FIRST Welcome Guys! these is one of the best page that you must follow on facebook. we work for better BE INFORMED FIRST
ON TELEGRAM, FACEBOOK AND ON YOUTUBE

በሲዳማ ክልል ወንጌላውያን አቢያተክርስቲያን ካውንስልና በQullaambe Tv  መካከል  የጋራ መግባቢያ ሰነድ በትላንትናው እለት ህዳር 21/2017 ዓም በሀዋሳ ከነማ ተካሄደ። ዘርፈ ብዙ ስ...
04/12/2024

በሲዳማ ክልል ወንጌላውያን አቢያተክርስቲያን ካውንስልና በQullaambe Tv መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በትላንትናው እለት ህዳር 21/2017 ዓም በሀዋሳ ከነማ ተካሄደ።

ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያለው ቁላምቤ ተሌቪዥን እንደ አንድ ትልቅ ሚዲያ ለመቋቋም እና ብዙ ስራዎችን ለመስራት ከሚመለከታቸው አካላት እና ተቋማት ጋር የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ትላልቅ ስራዎችን በመፈፀም ላይ ይገኛል።

በእለቱም የካውንስሉ የቦርድ ሰብሳቢ ፓስተር #ዮሴፍ ዮቶና እና የቁላምቤ ተሌቪዥን ስራ አስኪያጅ ወጣቱ ባለራዕይ መስራች #ሲሳይ ጢሞቲዎስ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

ቁላምቤ ቲቪ 👇👇
11545
45000
H

የአርቲስት ሰላም ተስፋዬ መልዕክት"እግዚአብሔር ሁሌም መሀሪ፣ ይቅርባይ፣ አዛኝ ነው። እሱን አምናቹ መቼም እንደማታፍሩ እኔ ምስክር ነኝ።በዚህ ሰዓት በምንም ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ...
05/09/2023

የአርቲስት ሰላም ተስፋዬ መልዕክት

"እግዚአብሔር ሁሌም መሀሪ፣ ይቅርባይ፣ አዛኝ ነው። እሱን አምናቹ መቼም እንደማታፍሩ እኔ ምስክር ነኝ።
በዚህ ሰዓት በምንም ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላቹ። እኔ እርግጠኛ ሆኜ ምነግራቹ ሁሉንም ነገራቹ እሱ ላይ በእምነት ጣሉ አያሳፍራቹም።
ይሄን ነገር post ያረኩበት ምክንያት
- አንደኛ እግዚአቢሄር ይሄ ምስክርነት ስለሚገባው ነው።
- ሁለተኛ ሰው እሚያልፈበትን አናውቅም እና እርስ በርሳችን መልካም እንሁን።
- ሌላ ደሞ ሁሌ ምቾቴን፣ ደስታየን ብቻ ማሳየት ስለማልፈልግ እና ለብዙ ሰው ትምህርት ሊሆን ይችላል በሚል ነው ።
ከፈጣሪ ውጭ ማንምላይ እምነት አታድርጉ።
ይሄ የተፈጠረው ከ3 ወር በፊት ነው።
ለመመስከር ያበቃኝ እግዚአቢሄር የተመሰገነ ይሁን!"

06/08/2023
ምስሉ ይናገራል አሉ...🤭የእናንተን ድምጽ ግን ለማን?1 ,      2    ወይም  3
08/07/2023

ምስሉ ይናገራል አሉ...🤭
የእናንተን ድምጽ ግን ለማን?
1 , 2 ወይም 3

  መንግስት ከሸለመ አንተንና እንደ አንተ ያሉትን ነው!       ጥብቅናም ከቆሜ እንደዛው!ህሊናውን ሽጦ ከነጻነት ሀገር ባርነትን መርጦ ተገስቶና ተረግጦ የሚኖር ሰው ለሀገሩ ልማት ደፋ ቀና...
31/01/2023


መንግስት ከሸለመ አንተንና እንደ አንተ ያሉትን ነው! ጥብቅናም ከቆሜ እንደዛው!

ህሊናውን ሽጦ
ከነጻነት ሀገር ባርነትን መርጦ
ተገስቶና ተረግጦ የሚኖር ሰው ለሀገሩ ልማት ደፋ ቀና ያለን ፣የሰራን ፣ትጉህና ሀገር ወዳድ ጀግናን ስም ማጠልሸት አይችልም!

የሀገርን ሀላፊነት በከፍተኛ ብቃት የተወጣው እንጅነር ታከለ ኡማ ክብር እንጂ ውርደት አይገባውም ፤ የንቀት ቃላት ተናጋሪውን ያስንቁ ይሆናል እንጂ ሀገርና ህዝቦቿ ማን እንደሰራላት ማን እንደ በደላት ውለታንም አትረሳም።
አላዋቂዎች ቢተቹህም ውዷ እናት ሀገርህ ኢትዮጵያ ግን ታመሰግንሃለች!

BE INFORMED FIRST

One thing I’ve learned is that God doesn’t always work on our timetable. In fact, He rarely does. But in a single moment...
28/01/2023

One thing I’ve learned is that God doesn’t always work on our timetable. In fact, He rarely does. But in a single moment, God can change your life! All throughout Scripture, we see examples of how God was working behind the scenes and instantly turned things around for His people. Scripture tells us He is the same yesterday, today and forever, which means if He did it for them, He can instantly turn things around for you, too!

You may be going through some difficulty today, but be encouraged because your times are in God’s hands. Trust that He has your best interest at heart. He wants to pour out His favor. He wants to take you further than you dreamed possible and work in your life in ways beyond what you have ever imagined. And while you’re waiting, don’t try to figure everything out. That’s only going to frustrate you.

Let this truth sink down into your heart today. Resist discouragement by speaking His Word over your future. Keep standing, keep hoping and keep believing because He is working behind the scenes. Have faith because your times are in His hands, and He will lead you in the life of victory He has for you!

©Double Portion Ministry

🗣  ☝️አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረ...
25/01/2023

🗣

☝️አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

🤷‍♂ ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

🙏አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል!

መልካም ቀን ተመኘንላችሁ😘
🙏❤️❤️❤️🙏⛴⛴⛴
BE INFORMED FIRST

"የልጄ ፀጉር እያየነው ረገፈ😭😭😭"  #ካንሰር‼️ይህች አንጀት የምትበላ ህፃን   ትባላለች!4ዓመቷ ነው!ከአንድ ዓመት በፊት ቦሌ አራብሳ የሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ከት/ቤት መጥታ ለመቀመጥ ስት...
23/01/2023

"የልጄ ፀጉር እያየነው ረገፈ😭😭😭" #ካንሰር‼️

ይህች አንጀት የምትበላ ህፃን ትባላለች!4ዓመቷ ነው!ከአንድ ዓመት በፊት ቦሌ አራብሳ የሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ከት/ቤት መጥታ ለመቀመጥ ስትሞክር ድንገት ትወድቃለች!!

መቆምና መቀመጥ ሲያቅታት እናትና አባት ተደናግጠው ወደ አቤት ሆስፒታል ሲወስዷት"ምንም የለባትም ህፃን ስለሆነች ነው"ተብሎ በማስታገሻ ቆየች!!ሁለት ወር የራስምታት ማስታገሻ የታዘዘላትን ፓራስታሞል ወሰደች!ምንም ለውጥ የለም!ሲቲ ስካን እና MRI ተነሳች ምንም አልተገኘም!!

ከቀናት በኋላ አንገቷ ስር ቁስል ሲወጣባት ለድጋሚ ምርመራ አቤት ሆስፒታል ሄዱ!!ናሙናዋ ተወስዶ ስትመረመር የደም ካንሰር ምልክት እንደሚያሳይና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በአስቸኳይ እንዲሄዱ ተነገራቸው!!ደነገጡ‼️ያልጠበቁትና ያላሰቡት ዱብዳ ገጥሟቸው ኬሞ በአስቸኳይ ትጀምር ተባሉ!!

እንደ እኩዮቿ ስትቦርቅና ስትስቅ የነበረችው የማርያም ደከመችባቸው፣ጉሊት የምትሰራው እናትና ላዳ ሹፌር የነበረው አባት ስራ አቆሙ!ቤት ኪራይ መክፈል እስኪያቅታቸው ተጨነቁ!!

ወደ ውጭ ሄዳ ታክማ ለመምጣት ከ1,500,000ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ሲያውቁ የበለጠ ግራ ገባቸው!እናንተ ደጋጎች እባካችሁን ምን እናድርግላችሁ? ምን እናግዛችሁ?እያልን ተስፋ እንስጣቸው🙏ምንም ማድረግ ካልቻልን ቢያንስ #እየፀለይን #ሼር በማድረግ ህፃኗን እናድንላቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት በአባት ስም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-1000034719962
አዋሽ ባንክ-01320185936400
አቢሲኒያ-68595398
#ስልክ
0911933141-ሞገስ(አባት)
0984710191-አዳነች(እናት)

15/01/2023

ዛሬ! ሁኔታ ይህን ባይነገር
ሰውም በክፋት ከጠላት ቢያብር
ትናንት አብሮ ከጎንህ የቆመ
መዝለቅ ሲሳነው እውነቱን ከጣለ
ማን? ምንም ብል!
እውነት
ይሄ ነው!
ኢየሱስ ብቻ
ብቻውን ጌታ ነው!!

BE INFORMED FIRST

እንዴት ይሄ ይሆናል⁉️የአስራ ሶስት (13) አመት ህፃን አስገድዶ ከደፈራት በኋላ መረጃን ለማጥፋት ወንዝ ውስጥ ሊጥላት የሞከረው ግለሰብ 3 አመት ከዘጠኝ (9) ወር ብቻ በእስር እንድቀጣ ተ...
31/12/2022

እንዴት ይሄ ይሆናል⁉️

የአስራ ሶስት (13) አመት ህፃን አስገድዶ ከደፈራት በኋላ መረጃን ለማጥፋት ወንዝ ውስጥ ሊጥላት የሞከረው ግለሰብ 3 አመት ከዘጠኝ (9) ወር ብቻ በእስር እንድቀጣ ተወሰነ ፍትህ እንፈልጋለን እያሉ ነው ቤተሰብ።

👉ይድረስ ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች
👉ይድረስ ሴቶችና ህፃናት መብት ተሟጋቾች
👉ይድረስ መላው ኢትዮጵያን ሴት ህፃናት መብት እንዳይገፈፍ ለሚትፈልጉ ሁሉም

ይህ ድርጊት በሲዳማ ክልል ሁላ ወረዳ የተከሰተ ስሆን ሞተረኛው ዳንኤል ዳንቃሞ እና ሞተረኛው ዮሐንስ ጫላ የሚባሉ ግለሰቦች ድርጊቱን የፈፀሙ ሲሆን አንድት የአስራ ሶስት አመት ልጅ ህዳር 12/2015 12:00 pm ሀንቆሞልቻ የሚባል ገጠር ዘመድ ልትጠይቅ በሞተረኛው ዳንኤል ዳንቃሞ መሄድ ትጀምራለች። ሞተረኛው ዳንኤል ዳቃሞ ህፃኗ የዘመዶቿ አካባቢ ለይታ የማይታወቅ መሆኗን ከአወቀ በኋላ ለጎደኛው ዮሐንስ ጫላ ጋር message መንገድ እንድጠብቀው ልከው ህፃኗን አፍኗት ይዘዋት ሄደው ጋታማ የሚባል ቦታ ለሁለት አንድ ማታ ሙሉ አስገድደው ደፍሯታል።

ይህንን ድርጊት ከፈፀሙት በኋላ መረጃን ለማጥፋት ፈልገው ከማለዳ 11:30 ይዘዋት ወጥተው ዬማ የሚባል ትልቅ ገደላማ ወንዝ ውስጥ ሊጥሏት እየሞከሩ እያለ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ሲደርሱባቸው ጥለው ይጠፋሉ።

ይህች ጨቅላ ህፃን እነኝህ የቤተክርስቲያን ሰዎቹ ያለችበት በስልክ ደውለው ለአባቷ ይነግረዋል። አባቷም ይህ ድርጊት ከሆነ ቀን ጀምረው ወደ ፍርድ ቤት የተመላለሱ ቢሆንም የሁላ ወረዳ ፍርድ ቤት ዋና ወጀለኛው ዳንኤል ዳንቃሞን ሶስት እመት ከዘጠኝ ወር ብቻ በእስር እንድቀጣ ወስኗል።

ፍትህ ህፃናት ሴቶች

 !!ይድረስ፦- ለኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ- ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት- ለኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል- ለሰላም ሚኒስቴር ዛሬ የኢ...
21/12/2022

!!

ይድረስ፦
- ለኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ
- ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት
- ለኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
- ለሰላም ሚኒስቴር

ዛሬ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቦርድ ደረጃ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰሞኑን ባቀረበች ጥያቄ ዙሪያ ስብሰባ አድርገው ነበር። በስብሰባው ላይ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኒቱን ያስተማረው ትምህርት ላይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፥ ካልጠየቀ ግን፦
- ከሰላም ሚኒስቴር ላይሰንሱ እንደሚሰረዝ
- ሚዲያው እንደሚዘጋ
- እስር እንደሚጠብቀው የተወያዩ ሲሆን የዛሬው ዋናው አጀንዳ በዋናዎቹ አመራሮች ታይቶ የሚወሰን ለነገ ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የእምነት ተቋምን ሰደበ የሚል ክስ ቀርቦበታል። በእውነት ተሳድቧልን? ቪዲዮውን መመልከት ይቻላል። የጠቀሰው ከቤተ እምነቱ እዕዋልድ መጽሐፍት ነው። መጽሐፍ የእነርሱ ካልሆነ ስም አጥፍቷልና በዚያ ሊጠየቅ ይችላል። ከዚያ ውጪ በየ አደባባዩ የሚሸጥና በቤተክርስቲያኒቱ አሳታሚነትና አከፋፋይነት የታተመን መጽሐፍ ላይ ምላሽ መስጠት በምንም መንገድ ወንጀል አይደለም። ያደረገው ትክክል አይደለም እንኳ ቢባል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተለያዩ መምህራን የወንጌል አማኞችን ሲሰድቡ እና ሁሌም በሚዲያቸው ሲያንቋሽሹ ለምን ዛሬ አገልጋይ ዮናታን ላይ የተወያዩበትን ጉዳይ አላደረጉም? የወንጌል አማኞች ስለ ወንጌል የሚደረግ መገፋትን በደስታ እንቀበላለን። ነገር ግን ፍትሃዊ ያልሆነ አድልዎ ግን አግባብነት የሌለው ነው።

ከጀርባው የተለየ አጀንዳ ከሌለው በቀር አገልጋይ ዮናታን ያስተማረው እና ትክክል አይደለም ያለው ከራሳቸው መጽሐፍ ጠቅሶ ነው እነርሱም ማድረግ ያለባቸው ትክክል አይደለህም ካሉ በመጽሐፍ ቅዱሱ ማስረዳት ነው። በቃ። ሌላው ደግሞ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስራ ሁሉንም እምነቶች እኩል ለአገር አንድነት አያይዞ መስራት እንጂ ለአንደኛው አድልቶ ሌላኛውን መጫን አይደለም።

የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች በዚህ ጉዳይ የመጨረሻውን ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባል። የወንጌል አማኞች ከ ሰላሳ ሚሊዮን በላይ ናቸው ነገሩ በአንድ አገልጋይ ዮናታን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን መላውን የወንጌል አማኞች ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል። በሌላ መረጃ እንገኛለን። አገራችንን ሰላም ያድርግልን።

ይቅርታ- ይህ ጽሑፍ ቅድሚያ ሲለጠፍ የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ያልነው በስህተት ሲሆን ትክክለኛው የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ነው።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BE INFORMED FIRST posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share