01/01/2024
ሀይማኖታዊ ንጽጽር ...3
📜 "ሰው ሁሉ ሲወለድ ሙስሊም" ነው ? እና ጥምቀት እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ-ነገሮች
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜"ሰው ሁሉ ሲወለድ ሙስሊም
ነው" የሚለው ንግግር ሀሰት ነው ምክንያቱም: ሀይማኖት... .ከእምነት.. ብቻ ሳይሆን .... ከዕውቀትም ...ጋር የተገናኘ ነው።📜📜
📜ይሁንና ዕውቀትን ለጊዜው እረስተን ስለ እምነትና ተአምር ብናወራ እንኳን ሰው እንደተወለደ ሙስሊም ተደርጎ በተአምር የሚፈጠር ከሆነ ህጻናት እንደተወለዱ ከመጮህ ይልቅ ለምን ....በአምላክ ተአምር...."አላህ አክበር" በማለት አይናገሩም?
📜ስለ ተመሳሳይ ነገር ስናወራ ኢሳ (ኢየሱስ) በህጻንነቱ በአላህ ተአምር እንደተናገረ በቁርአን ተጽፏል:(3:46):- «በሕፃንነቱና በከፈኒሳነቱ ሰዎቹን ያነጋግራል፡፡ ከመልካሞቹም ነው» (አላት)፡፡
📜ሀይማኖት ስንል የአይሁድ ሀይማኖት :ክርስቲያን: ሙስሊም:ሂንዱ:ቡዲዝም ወዘተ ማለታችን ነው።
📜ገና የተወለዱ ወይም ትንሽ ሳምንታት ያስቆጠሩ ህጻናት እናቶቻቸው ካለማመዷቸው ፈልገው መጥባትን ከመሳሰሉ ያለፈ ልምምድ የተገኘ ዕውቀት አይኖራቸውም።ህጻናት ከፍ እያሉና እያደጉ ሲመጡ ስለ ነገሮች ያላቸው እምነት እያደገ ይመጣል:ደግሞም ከአካባቢያቸው ከሚሰሙት እና ከሚያዩት እንዲሁም ከሚነካኩት ነገር እየተለማመዱ: እየተማሩ እውቀት እያገኙ በዕውቀት እያደጉ ይመጣሉ።📜ሀይማኖት ምን እንደሆነ የሚያውቁት ያን ጊዜ ነው።
📜እምነትና እውቀት የተያያዘ ነው።ስለ አንድ ነገር ...አውቀህ ልታምን... ትችላለህ:ለምሳሌ ሰዎች ማርስ የምትባለው ፕላኔት ላይ ስፔስ ክራፍት ማሳረፋቸውን የሚያሳይ ትክክለኛ ቪዲዮ ካየህ በኋላ ...በማወቅህ... ይህ ነገር በሰው ልጅ አቅም የተቻለ መሆኑን ....ታምናለህ.....።
📜ወይም ስለ አንድ ነገር ከውጤቱ አስቀድመህ ....በማመንህ... ቀጥሎ ስለዚያ ነገር በዝርዝር ...ልታውቅ... ትችላለህ።ለምሳሌ:መንጃ ፈቃድ ልታወጣ እንደምትችል እና ሹፌር ልትሆን እንደምትችል አስቀድመህ ...ታምናለህ:....ከዚያም የመንጃ ፈቃድ ትምህርት ዕውቀት እና ልምምድ ይኖርህና መኪና እንዴት ማሽከርከር እንዳለብህ ...ታውቃለህ።
📜እምነትና እውቀት ባብዛኛው ተያያዥ ናቸው።አንዱ ሌላውን እየቀደመም ይመጣል።ሀይማኖተኛ ለመሆን
እውቀትና እምነት ሁለቱም አብረው መገኘት አለባቸው።📜📜📜የሰው ልጅ ሲወለድ እምነት አብሮ ይፈጠራል (ያ ሀይማኖት አይደለም):ህጻኑ ሲያድግም ስለ ነገሮች ያለው እምነት እያደገ ይሄዳል።📜📜📜
📜ህጻናት ሀይማኖት ካላቸው ወላጆች ሊወለዱ ይችላሉ ነገር ግን አድገው ክፉና ደግ እስከሚለዩ ድረስ.... ሀይማኖታቸው.... ይህ ነው ማለት አይቻልም።ገና የተወለዱ ህጻናት ስለሀይማኖትም ይሁን ስለማንኛውም ነገር ያውቃሉ ብለን መናገር ብንጀምር የሚያስቅ ነገር ከመሆን የዘለለ አይሆንም።
📜እምነት ከሀይማኖት ጋር ብቻ የተያያዘ እንዳልሆነ እናውቃለን:ታክሲ ተሳፍረን የምንከፍለው የምንፈልገው ቦታ እንደሚያደርሰን ስለምናምን ነው:ስራ ተቀጥረን የምንሰራው ደሞዝ ይከፈለናል ብለን ስለምናምን ነው:ቤት የምንሰራው እንኖርበታለን ብለን ስለምናምን ነው እና ወዘተ።እንደዚህ አይነት ብዙ እምነቶቻችንን መጠቃቀስ እንችላለን።
📜እነዚህ እምነቶቻችን ናቸው።ነገር ግን እነዚህ እምነቶቻችን ሀይማኖቶቻችን አይደሉም።
📜በነዚህና በመሳሰሉ ነገሮች እንድናምን የሚያደርገን እምነት የተገኘው በህይወት ከአካባቢያችን ልምምድ እና በተፈጥሮ አብሮን ከተፈጠረ እምነት ነው።
📜📜📜📜ሰው ሲፈጠር በነገሮች ሊያምን የሚይል ፍጡር ተደርጎ ነው :ነገር ግን እንደተወለደ ሀይማኖት ይዞ አይወለድም።ስለዚህም ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነው ማለት ግዙፍ ውሸት ነው።📜📜📜📜
📜ህጻናትን የሚያጠምቁ ክርስቲያን ቤተሰቦች ህጻናትን ሲያጠምቁ በጥምቀት እነርሱ ወላጆች አምነው...ለእግዚአብሔር ይለዩታል/ይሰጡታል/ ።ይህ ከወላጆች እምነት አንጻር ነው።ወላጆች በእምነታቸው መሠረት ለክርስቲያንነት ለእግዚአብሔር ለየነው ይላሉ።ከህጻኑ እምነት አንጻር:ህጻን በመሆኑ ምክንያት ስለዚያ ሀይማኖታዊ ጥምቀት ምንም የሚያምነው እና የሚያውቀው ነገር የለም።
📜 ያልተጠመቀና ክርስቲያን ያልሆነ ሁሉ ሀይማኖቱ የግድ ሙስሊም ነው?
አንዳንድ ሙስሊም እንደዚህ ይታለላል።ሆኖም አንድ ሰው የክርስትናን እምነት ሳያምንና ሳይጠመቅ ቢሞት : በዚህ ሀይማኖት ሳይጠቃለል ሞተ: ማለት እንጂ የግድ ሙስሊም ነበር ማለት አይደለም።እንዲህ አይነት ሰው ሀይማኖት አልባ ወይም በሆነ ባዕድ አምልኮ የሚያምን ሊሆን ይችላል።📜የክርስቲያን ቤተሰብ ህጻናት ቢጠመቁም ባይጠመቁም ከፍ እስከሚሉ እና ነፍስ እስከሚያውቁ ድረስ ስለሀይማኖት የሚያውቁት ነገር የላቸውም።📜ህጻናት ሳይጠመቁ ቢሞቱ ያው ሳይጠመቁ/ቤተሰቦቻቸው ....ለእግዚአብሔር... ሳይለዩአቸው ...ሞቱ ማለት እንጂ "ሙስሊም ነበሩ/ሀይማኖታቸው ሙስሊም ነበር ብሎ መናገር ከተራ ቀልድ ያለፈ አይሆንም።
📜📜ሌላው በሙስሊሞች የሚቀርበው ንግግር እስልምና ማለት "መሰጠት"/መታዘዝ/ ስለሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት የጥንት ነብያት ሁሉ ሙስሊሞች ናቸው የሚል ነው።ቁርአንም በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት ነብያት ሙስሊሞች ነበሩ ይላል:ለምሳሌ አብርሃም/ኢብራሂም/ :3:67። 📜ይህ ሀሰት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ነብያትን ወደ እስልምና የመስረቅ ዘዴ ነው።📜 ማስረጃዎች ቢያስፈልጉ:-
2.1 መታዘዝ የሚለው ቃል እና ጽንሰ ሀሳብ የእስልምና ሀይማኖት ከመታወቁ ብዙ አመታት በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ ይገኛል:(ዘዳ.27:10,ዘዳ.30:2 ,ኢሳ.1:19,)ስለዚህ እውነታው የእስልምና ሀይማኖት ይህን የመታዘዝ ጽንሰ ሀሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ መውሰዱ እና የራሱ ...ብቻ...አድርጎ ለማሳየት መሞከሩ ነው።📜ይህን የሀሰት ንግግር በሌላ ምሳሌ ብናየው እኔ ጋርም ሌሎች ሰዎች ጋርም ያለን አንድ ነገር ....የኔ መለያ ብቻ ...አድርጎ መቁጠር ማለት ነው።📜"መታዘዝ" የመጽሐፍ ቅዱስ :የአይሁድ እንዲሁም የክርስትና ሀይማኖት መለያ ነው።ለነገሩ የትኛውም አምልኮ መታዘዝን ይፈልጋል። ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ የተዘረዘሩት 10ቱ ትዕዛዛት አላማቸው ያው መታዘዝ እንደሆነ ግልጽ ነው(ዘጸ.20)።📜በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለ መታዘዝ ነው ለነብያት በዋናነት ሲናገር የነበረው።ክርስቶስ በፍቅር እንድንታዘዘው ይፈልጋል(ማር.12:30)
ያለበለዚያ የእርሱ ነን ብንል ትርጉም የለውም።
📜📜መታዘዝ ከሚለው ቃል ጋር አብሮ ለአንድ አምላክ የሚለውን አብረን ብናየው.....ለአንድ አምላክ መታዘዝ እና.... አንድ አምላክን ማምለክ....በመጀመሪያ የተጠቀሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው (ዘዳ.6:4)።📜በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው አንድ አምላክን ማምለክ ማለት የእስልምና ሀይማኖት ማለት አይደለም።እንደ ዘዳ.6:4ን የመሳሰሉ ጥቅሶች በተጻፉ ወቅት(የዛሬ 3,400 አመታት አካባቢ) የእስልምና ሀይማኖት ሽታውም አልነበረም።📜በነዚያ ዘመናት ከሀይማኖት ጋር አቻ የሆነ ስም ለመጥቀስ ቢያስፈልግ "ሙሴ"(የታላቁን መሪ ስም) የሚለውን ቃል መጠቀም ይቻላል።📜የጥንት ነብያት በእነዚያ ጊዜያት የነበረውን የአምልኮ ስርአት የ"ሙሴ" በማለት ይጠሩት ነበር (ነህምያ 1:7)።ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን የነበረውን የአምልኮ ስርአት በአጠቃላይ" ሙሴና ነብያት" በማለት ያመለክት ነበር(ሉቃ.16:31)።"ሙሴና ነብያት" የሚለውን ከሀይማኖት ስም አቻ አድርጎ ማየት ይቻላል።📜የጥንት የአለም ታሪክን ብንመለከት በብሉይ ኪዳን በተለይ ከንጉስ ሰለሞን ሞት በኋላ ዘሮቻቸው በሌሎች ዘንድ "አይሁድ" እየተባሉ ይጠሩ ስለነበር (አስቴር 3:6) የ"ሙሴና ነብያትን" እምነት የሚከተሉ የአይሁድ ሀይማኖት ተከታዮች እየተባሉ ይጠሩ ነበር።ይህ በመጽሐፍ ቅዱስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪም ባሉ የጥንት መጽሐፍት ይታወቃል።📜ቀጥሎም ከክርስቶስ ጋር ተያይዞ በኋላ የክርስትና እምነት ተመሰረተ።📜የእስልምና ሀይማኖት የተመሠረተው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ570 ዓ.ም በተወለደው በመሀመድ ነው።እውነታው ይህ ቢሆንም ሙስሊሞች እና ቁርአን እስልምና ቀድሞም በጥንት የመጽሐፍ ቅዱስ ነብያት ዘመን እንደነበር ይናገራሉ:ሆኖም እላይ ካልናቸው ነጥቦች በተጨማሪ ከእስልምናው መስራች መሀመድ በፊት የእስልምና ሀይማኖት ስለመኖሩ የሚያረዳ አንድም አርኪዮሎጂያዊ/የስነ ምድር ቁፋሮ/ ግኝት የለም።የተገኙት የስነ ምድር ቁፋሮ ማስረጃዎች በጥንት ዘመን በርካታ አይነት አምልኮዎችን ያሳያሉ።ስለ እስልምና አጀማመርም ከመሀመድ ልደት በኋላ ያለው ነው። እውነታው
📜ይህን ጉዳይ ("መታዘዝ"/"መሰጠት") እስልምና ነው የሚለውን ንግግር/) እንደ ሙስሊሞች አስተሳሰብ/logic/ ብንወስደው ከጥንት ዘመን ጀምሮ በሜሶጶታሚያ:ባቢሎኒያ:ግብጽ:ግሪክ:ህንድ:ከነአን:ኢራን:መካ:እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የጣዖት አምልኮዎች እንደነበሩ የአርኪዮሎጂ ሳይንስ ያስረዳል።አምላኪዎቹም ለጣዖቶቹ ..
መታዘዝ/መሰጠት/ የግድ ነበረባቸው:..እና የመታዘዝ ጽንሰ ሀሳብ በመኖሩ እንደሙስሊሞች እምነት እነዚያ የጣዖት አምልኮዎች እስልምና ነበሩ ማለት ነው።
📜በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ የነበሩ ነብያት ኢየሱስን ጨምሮ ሙስሊም ነበሩ የሚለውን የሙስሊሞች ንግግር ውድቅ የሚያደርገው ዛሬ ሙስሊሞች ለእምነታቸው የሚጠቀሟቸው የግማሽ ጨረቃ እና የኮከብ ምልክቶች ናቸው።📜📜አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ነብይ ለእምነቱ ምልክት ግማሽ ጨረቃ እና ኮከብን አልተጠቀመም።📜 📜ግማሽ ጨረቃንና ኮከብን ስለተጠቀመ የመጽሐፍ ቅዱስ ነብይ በመጽሐፍ ቅዱስ አናነብም:በአርኪዮሎጂ/ስነ ምድር ቁፋሮም/ሳይንስም አልተገኘም።
📜በተቃራኒው ግን በጥንት ዘመን የነበሩ ....የተለያዩ የጣዖት አምልኮዎች የጨረቃን እና የኮከብ ምልክትን እንደ አምላክ ...ተጠቅመውባቸዋል።
📜ይህም የሚያሳየው እስልምና 🕋ከጣዖት አምልኮ ጋር እጅጉን የተዛመደ መሆኑን ነው:-
📜📜 ከጨረቃ ጋር የተያያዘ አምልኮ
የእስልምና አምነት ከጨረቃ እና ኮከብ ጋር እጅጉን የተቆራኘ ነው።የሙስሊም እምነት አምልኮ እና መገለጫ
ከሆኑት ጨረቃና ኮከብ ጋር የተያያዙ በጥንት ዘመን በርካታ የጣዖት አምልኮዎች ነበሩ:- ለምሳሌ
1. ናና/ሲን/ሱኤን/ በመባል ይታወቅ የነበረው የጥንት ሜሶጴታሚያ /ሱሜር/አካድ/አሲሪያ/ባቢሎኒያ/አራም/ ህዝቦች የጨረቃ አምላክ የነበረ ሲሆን መለያው የአሁኑ የሙስሊሞች እምነት ምልክት ...ግማሽ ጨረቃ(Crescent moon) ነበር
2. ኮንሱ: የጥንት ግብጻውያን የጨረቃ አምላክ ሲሆን ራሱ ላይ ሙሉ ጨረቃ እና
የግማሽ ጨረቃ ምልክት ነበረበት
3.የጥንት ግሪክች የጨረቃ አምላክ ሰሊኔ በመባል ይታወቃል
4.ሶማ(ቻንድራ): የሂንዱ የጨረቃ አምላክ ነው
5.ማንጋ: ዞሮአስተሪያን ተብሎ የሚታወቀው የጥንት ኢራናውያን እምነት
የጨረቃ አምላክ ነው
6.ሁባል: የሙስሊም ነብይ መሀመድ የጎሳ ዘሮች (ቁረይሾች) በካባ ሲያመልኩት የነበረው የጨረቃ አምላክ ነው
*** የሚከተሉትን ሊንኮች በመጫን ሙሉ መረጃዎቹን ያንብቡ
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Sin_(mythology)
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Khonsu
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Selene
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Chandra
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Mah
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Hubal
📜📜 አንድ አምላክን ብቻ አመልካለሁ ማለት ጣዖት ላለማምለክ ማረጋገጫ አይሆንም 📜📜
በመጽሐፍ ቅዱስ የጥንት ዘመን እስራኤላውያን ማምለክ ያለባቸው አንድ አምላክ ብቻ እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሯቸዋል( ምሳሌ ጥቅሶች:- ዘዳ.6:14,ዘዳ.29:18,ኢሳ.36:20,1ኛቆሮ.8:5):ይህም በወቅቱ በእስራኤላውያን ዙሪያ የነበሩ ህዝቦች በአብዛኛው በብዙ ጣዖታት አማልክት የመልኩ የነበረ በመሆኑ ነው።📜ነገር ግን አንድ አምላክን ማምለክ የግድ ፈጣሪን ማምለክ አይደለም።📜📜አንድ አምላክ ጣዖትንም ማምለክ አለና።📜📜ወደ ቁርአንም እንደ ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ አንድ አምላክን ብቻ የማምለክን ሀሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወስዷል።
📜ሙስሊሞች እኛ አንድ አምላክን ብቻ ነው የምናመልከው በማለት ይናገራሉ:ይህ ጉዳይ በቁርአንም ትኩረት ተሰጥቶታል።መሀመድም በመካ ይገኙ ከነበሩት 360 ጣዖታት አንዱን ብቻ በማስቀረት ሌሎቹን እንዳጠፋ ታሪክ እና አርኪዮሎጂ ሳይንስ ይናገራል።
📜ነገር ግን ታሪክ እና አርኪዮሎጂ ሳይንስ እንደሚያስረዳው መሀመድ ሌሎቹን በመካ ዙሪያ ይመለኩ ከነበሩት 360 ጣዖታት መካከል አንዱን ብቻ በማስቀረት ሌሎቹን አጥፍቷል:-
..📜 የመሀመድ አያት አብዱል ሙጣሊብም "ሁባል" የተባለ ጣዖትን በመካ ያመልክ እንደነበር እና መሀመድን ወደ ሁባል እንደወሰደው እና መሀመድን ለሁባል እንደሰጠው በሁለት የሙስሊሞች ሀዲሳት (ኢብን ሀሺም እና ጠበሪ ) የተጠቀሰ ነው:-
(Ibn Hisham 37 & Tabari Vol 5: pg 271)"
📜አንድ አምላክን ስለማምለክ (Monotheism) ስናወራ እላይ እንዳልነው ይህ የግድ እውተኛውን አንድ አምላክ /ፈጣሪ/ብቻ የሚያሳይ አይደለም። "አምላክ" ማለት የሚመለክን ነገር/ህላዌ
/ የሚያመለክት ነው።ፈጣሪን አምላክ ልንል እንላለን:አንድን የሚመለክ ጣዖትንም አምላክ ልንል እንችላለን።
በጥንት ዘመን አንድ አምላክን ብቻ የሚያመልኩ ሰዎች ነበሩ:ለምሳሌ "አክሄናቴ"/Akhenate/በመባል የሚታወቀው የጥንቱ የግብጽ ፈርዖን ....በአንድ አምላክ ብቻ... የሚያምን ንጉስ ነበር።ያ አምላክ ግን "አቴን"/Aten/የተባለ የጸሀይ ምስል ነበር።ሌላ ምሳሌ ዞሮአስተርያኒዝም/Zoroasteriasm/ የተባለው የጥንት ኢራናውያን አምልኮ ነው።ዞሮአስተርያኖች በአንድ አምላክ ብቻ ነው የሚያምኑት:አምላካቸውም አሁራ ማዝዳ/Ahura Mazda/ በመባል ይታወቃል። ምንጭ:-
https://www.worldhistory.org/article/1454/monotheism-in-the-ancient-world/
📜እናም እስልምና በአንድ አምላክ ማመንን ስለሚነግረን ብቻ ጅማሬው በፈጣሪ ላይ የተመሠረተ ነው ማለት አይቻልም።እላይ እንዳልነው መሀመድ ሌሎቹን ሲያጠፋ አንድ ጣዖት/አምላክ/ብቻ አስቀርቶ ነበር።አያቱም መሀመድን..... ሁባል ወደ ተባለ ወደ አንድ አምላክ..... ብቻ ወስዶት ነበር።
Sin (/ˈsiːn/) or Suen (Akkadian: 𒀭𒂗𒍪, dEN.ZU[1]) also known as Nanna (Sumerian: 𒀭𒋀𒆠 DŠEŠ.KI, DNANNA[2]) was the Mesopotamian god representing the moon. While these two names originate in two different languages, respectively Akkadian and Sumerian, they were already used interch...