
23/07/2024
እንደ ATM ያለ ገንዘብ የማይንቀሳቀሱት የዘመኑ ዘማሪዎች ፣ በክፍያ የሚገባው የመዝሙር ኮንሰርትና የሆቴል ቤት ዝንቦች።
=========================================
ከሶስት ሳምንት በፊት ሊደረግ የነበረዉ የመዝሙር ኮንሰርት ( የሙዚቃ ብንለዉ ይቀላል ) ይህ ዝግጅት ሊደረግ ታስቦ የነበረዉ በጊዮን ሆቴል ነበረ። ችግሩ በጊዮን ሆቴል መደረጉ አይደለም ፤ በእርዳታ ስም … በስመ ክርስትና እግዚአብሄርን ለማምለክ በክፍያ የሚገባበት ኮንሰርት ማዘጋጀት አንድም እግዚአብሄርን አለመፍራትና ህዝበ ክርስቲያኑን መናቅ ነው። የሆኑ ግሩፖች እንደፈለጉ እየተነሱ ህዝቡንስ እስከመቼ ነዉ የሚያሞኙት?
ለእኔ እነዚህና መሰሎቻቸው የATM ማሽኖች ናቸው ያለ ብር የማይጮሁ ያለ ብር የማይተነብዩ ናቸው። ከጅምሩም Gion ሆቴል ላይ ለምን ማዘጋጀት ተፈለገ? የዘፈን ኮንሰርት አይደል or festivals። በጣም ያልጠበኲትና ያስደነገጠኝ ደግሞ በጣም የማከብራቸዉና ብዙ ምእመን የተባረከባቸዉ እንደ ዘማሪ ወርቅነህ አላሮና ዘማሪ እንዳለን መመልከቴ ነዉ 🥹
First of all በእርዳታ አስታኮ ሆቴል አዳራሽ ተከራይቶ ከምእመኑ የመግብያ ማስከፈል ምን ይሉታል? የተሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪውን የትኛው አካል ነው የሚቆጣጠረው? ይህንን ፕሮግራም በአብያተ-ክርስቲያናት እንደ መካነ-ኢየሱስ ፣ ቃለ-ህይወት ፣ ሙሉ-ወንጌል ባሉ ሰፋፊ Church ውስጥ ለምን ማድረግ አልተፈለገም? የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትስ ይህንን ተግባር ከማውገዝ ስለምን ተቆጠቡ?
ዘመን አፈላሽና የሀሰተኛ ነብያት ቸርች አዳማቂዎች እንደ ይሳቅ ሰዲቅ ፣ አቤኔዘር ፣ ይትባረክ እና መሰሎቻቸዉ ያለ ብር የማይንቀሳቀሱ የATM ማሽኖች ፣ ከትልልቅ ሆቴሎች ወንበሮች ላይ የማይጠፉ የሆቴል ቤት ዝንቦች ……… ናቸወ። ታርጌታቸዉ በትላልቅ ሆቴሎች ላይ የሚያገኙትን ባለ ሀብቶች ና ዲያስፖራዎችን ነው ፤ በተለይ ደግሞ ሴቶችን ታርጌት ያደርጋሉ። እንደ Sheraton, Kaleb, Saro Maria, Harmony, Haile Grand እና Mado ሆቴሎች ላይ አታጣቸውም።
ከሴቶች በላይ ይኳኳላሉ። ትክክለኛ መንፈሳውያን ቢሆኑ ኖሮ ከሰኞ-ከሰኞ ቸርች ላይ ይገኙ ነበር ነገር ግን they are money 💰 💵 minded ! ታርጌታቸው በሀብታም ሰርጐች ላይ ከ50 ሺ የማያንስ ገንዘብ እየተቀበሉ የሰርግ ስራ መስራት ነው ፤ እሱንም የተመረጡ ሆቴሎች ካልሆነ በስተቀር ቀጥረውም አይመጡም። በጣም የሚገርመው አብዛኛው የዘመኑ ዘማሪዎች ሁለተኛ ትዳራቸው ላይ ያሉና ከትዳራቸዉም ውጪ በዉስልትና የወለዱ ናቸው።
ብዙ ሰዉ ስላላወቀ ቀኑ ተራዝሟል የተባለለትን በክፍያ የሚገባበትን የመዝሙር ኮንሰርት ቢደረግ እንኳን ባለመግባት አጉል ልምምድን እናስቀር። ቅልጥም ባገኙበት የሚጮሁ ዘማሪ ተብዬዎችን አደብ እናሲዝ። ተጨማሪ ሚስጥራቸዉን ደግሞ በYouTube በቪዲዮ ከሰሞኑ እከሰታለው። ዝም ያልነዉ ስለማናውቅ አይደለም 🙈🙉🙊