
13/02/2024
መራዊ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ለቀን ሥራ በጠዋት ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ 18 ሲቪሎችን ጨምሮ በርካታ ሌሎች ሰዎች በመርአዊ ከተማ ውስጥ ጥር 20/2016 በመንግስት ሀይሎች ተገድለዋል ብሏል።
በእለቱ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚጠሩት) መካከል ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ውጊያ ተካሂዶ እንደነበርም ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል።
ከቀናት በፊት የሆስፒታል ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ባጋራሁት አንድ መረጃ የሟቾች ቁጥር 157 ገደማ መሆኑን አቅርቤ ነበር።
በነገራችን ላይ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ለማቅረብ እጅግ የሚዘገንን የሞቱ ሰዎችን የሚያሳይ አንድ አጭር ቪድዮ እየተሰራጨ ይገኛል። ስፍራው በትክክል መርአዊ ከተማ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
ይህን ጉግል ማፕ በመጠቀም ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን ቪድዮው ላይ የሚታየውን ዘንባባ (1)፣ ቅያስ መንገድ (2)፣ በመሰራት ላይ ያለ ህንፃ (3) እና እናት ባንክ (4) ያለበትን ህንፃ በማየት ማመሳከር ይቻላል (ምስሉን ይመልከቱ)።
በድጋሜ ነፍስ ይማር።