04/07/2024
ትንሹ የ13 ዓመት ልጅ ሲሆን የአቡነ ጴጥሮስ አገልጋይ ነው፣ በአቡነ ጴጥሮስና በካሳ ልጆች መሃልም መልዕክት አመላላሽ ነው፡፡ ከአቡነ ጴጥሮስ ጋር መለየት የማይፈልግ የልጅ አርበኛ ነው፣ በማጎሪያ ቤት ውስጥ ግራዚያኒና ጥቁር ሸሚዝ ለባሾች እህቱን ድንበሬን አሰቃይተውበት ልቡ ያቄመ ልጅ ነው፣ አቡነ ጴጥሮስ ለግራዚያኒ እንዳይንበረከኩ በቅዳሴ የሚያግዛቸው ዲያቆን ነው፣ አቡነ ጴጥሮስ ሲረሸኙ፣ አስተኳሹን-ቪቶሪዮ ሙሶሊኒንና ጥቁር ሸሚዝ ለባሾቹን አቁስሎ ወደ ጫካ የገባ አርበኛ ነው፡፡
Tinishu is a 13 year old diakon and a disciple of Abune Petros. His heart is wounded and he wants to avenge his sister, Dinbere, who was tortured by Graziani and the black shirt fascists in a concentration camp. He wants Abune Petros not to give in to Graziani’s ultimatum, free himself from prison and join the patriots. When Abune Petros is martyred, Tinihu conspired to kills the the commander-in-chief of the firing squad-Vitorio Mussolini and runs into the woods to join the patriots.