12/06/2026
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እውነቱን ይፋ አደረገች!
"ስለእኔ ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ በቀረቡ ዜናዎች ላይ አንድ መረጃ ላካፍላችሁ እወዳለሁ። በሐኪሜ ትዕዛዝ መሠረት የመውለድ አቅሜን (ፈርቲሊቲ) ለማሻሻል ሌትሮዞል (letrozole) የተባለውን ተጨማሪ መድኃኒት ወስጄ ነበር።
በአሁኑ ወቅት እርግዝናዬ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ ልጄ እንደተወለደም በፍጥነት ወደ ስፖርቱ እመለሳለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ለአድናቂዎቼ በሙሉ ለምትሰጡኝ ፍቅር አመሰግናለሁ፣ ሁላችሁንም ናፍቄአችኋለሁ።
በተጨማሪም የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ላሳየኝ መረዳትና ድጋፍ አድናቆቴን እገልጻለሁ።"
ጉዳፍ ፀጋይ ደስታ