
14/07/2025
ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎች ላይ የመጠጥ ውሃ የማዳረስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማከናወን ከዛኪር ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎች ላይ የመጠጥ ውሃ የማዳረስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው፤ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራው በአጭር ጊዜ በጥራት እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያድግ ገልጸዋል፡፡
የዛኪር ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መሃመድ ሀሰን በበኩላቸው ቁፋሮውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ስራውን እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል፡፡
ከ144 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ በአራት ወር ከግማሽ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በሳልሃድ ወረዳ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች እና በዱሁን ወረዳ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች የሚቆፈሩ ይሆናል፡፡
ፕሮጀክቱ በብሄራዊ የዋን ዋሽ ሮግራም የባለብዙ መንደር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ፕሮጀክት አከል ነው።
የማማከር ስራውን ሚሊኪ ኮንሰልቲንግ እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል፡፡