
15/09/2025
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጠናዊ ትስስርን ይፈጥራል ---ደይሊ ሳባህ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ልማት ከማፋጠኑም ባሻገር ቀጠናውን ይበልጥ ያስተሳስራል ሲል ደይሊ ሳባህ ጽፏል፡
" ግድቡ የተራቀቀ የምህንድስና ውጤት ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ ምልክት ነው ፤ ከፍ ሲልም ምስራቅ አፍሪካን አንድ የማድረግ እምቅ አቅም ያለው የባንዲራ ፕሮጀክት ፡፡ "
ቀጠናዊ ውህደትን በማቀጣጠል በአባይ ተፋሰስ ሀገራት ዘንድ የትብብርና የመተማመን በርን ይከፍታልም ነው ያለው ጋዜጣው፡፡
ኢትዮጵያዊያን የማንንም እርዳታ ሳይጠይቁ በራስ አቅም የገነቡት ታላቁ የህዳሴ ግድብ መላው አፈሪካን ይበልጥ አንድ ያደርጋልም ብሏል ፤ደይሊ ሳባህ፡፡
ግድቡ የኢትዮጵያዊያንን በተፈጥሮ ሀብታቸው የመጠቀም የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ያለው ደይሊ ሳባህ ፤ኢትዮጵያዊያን አንድ ሲሆኑ የሚሳናቸው ምንም ነገር እንደሌለም አስነብቧል።
"ደይሊ ሳባህ" በሀገረ -ቱርክየ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየታተመ የሚሰራጭ ዕለታዊ ጋዜጣ ነው።
አህመድ መሀመድ